አቶ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም እና አቶ ነጋሽ ያደቴ አባይነህ ነጋሽ ሰ.መ.ቁ.200968

አቶ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም እና አቶ ነጋሽ ያደቴ አባይነህ ነጋሽ ሰ.መ.ቁ.200968

ይህ የእርሻ መሬት የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.251106 ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል ዉስጥ ግብር እየገበርኩበት ያለዉን ሁለት ቀርጥ (አዋሳኝ በመጥቀስ) የእርሻ መሬት ይዞታዬን የካቲት ወር 1989 ዓ.ም ባደረግነዉ ዉል ለጊዜያዊ ችግሬ መዋያ ብር 7000 (ሰባት ሺህ) ከተከሳሽ ተቀብዬ መሬቱን ለተከሳሽ የሰጠሁ፣ ገንዘቡን ስመልስለት ደግሞ መሬቱን ሊመልስልኝ የተስማመን ሲሆን፣ ተከሳሽ ገንዘቡን ተቀብሎኝ መሬቱን እንዲያስረክበኝ ፈቃደኛ ስላልሆነ፣ ተከሳሽ ገንዘቡን ተቀብሎኝ የእርሻ መሬቱን እንዲያስረክበኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡……………..

 

 

መ/ር ሲራጅ መሀመድ እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሰ/መ/ቁ፡-200948

መ/ር ሲራጅ መሀመድ እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሰ/መ/ቁ፡-200948

ጉዳዩ ከውል ውጭ ኃላፊነትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነዉ፡፡የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን የአሁኑን አመልካች ጨምሮ ሌሎች 4 ሰዎች ላይ ባቀረበው ክስ ንብረትነቱ ከተከሳሾች የአንዳቸው ወይም የሁሉም የሆነ የሠ/ቁ.1-06754 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ በ25/04/2006ዓ.ም በኮልፈ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 4 አለም ባንክ አከባቢ ተጠሪ የመድን ሽፋን የሰጠውን የሰ/ቁ.4-01850ኢ.ት የሆነውን ተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት አድርሷል፡፡ተጠሪ ከደንበኛው ጋር ባለው ውል ስምምነት ለደረሰው ጉዳት ብር 19,250.00 ለደንበኛው ከፍሏል፣ስለሆነም ተከሳሾች ገንዘቡን እንዲተኩ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡አመልካች በበኩሉ አደጋ አድራሹን ተሽከርካሪ በ2005 ዓ.ም ለአቶ ጉግሳ ይልማ በመሸጥ መኪናውን ያስረከብኩት ስለሆነ ደረሰ ስለተባለው ጉዳትም የማውቀው ነገር የለም፣በእኔ ላይ የቀረበው ክስ አለአግባብ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል፡፡ሌሎች ተከሳሾች መልስ አላቀረቡም ቀርበውም አልተከራከሩም ተብሎ የታለፈ መሆኑን መዝገቡ ያሣያል፡፡…………………..

ሕዳሴ ቴሌኮም አ/ማ እና እነ አቶ ገዛኸኝ ለማ የሰ/መ/ቁ፡200929

ሕዳሴ ቴሌኮም አ/ማ እና እነ አቶ ገዛኸኝ ለማ የሰ/መ/ቁ፡200929

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ተከሳሾች ሆነው ተከራክረዋል፡፡ አመልካች ያቀረበው ክስ 1ኛ ተጠሪ የአመልካች የሽያጭ ሠራተኛ ሆነው ሲሰሩ በውስጥ ኦዲት በሚደረግበት ጊዜ ብር 204,250.00 በጉድለት ስለተገኘ ገንዘቡን እንዲከፍሉ፤ 2ኛ ተጠሪም የ1ኛ ተጠሪ ዋስና ተያዥ በመሆናቸው እስከ 100,000.00 በአንድነትና ነጠላ ኃላፊነት እንዲከፍሉ የሚል ነው፡፡ 1ኛ ተጠሪ የሠጡት መልስ ገቢና ወጪውን ያልለየ፣ ከመቼ እስከመቼ የተደረገ ኦዲት ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም፡፡ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ይደረግልኝ ብለዋል፡፡ 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው ጉድለት የለም፣ ዋስ የሆንኩት 1ኛ ተጠሪ የመስመር ሠራተኛ እያለ ነው፤ ልጠየቅ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡………….

 

አይካ አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አቶ ኢብራሒም አይዶግዱ የሰ/መ/ቁ፡-200687

አይካ አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና አቶ ኢብራሒም አይዶግዱ የሰ/መ/ቁ፡-200687

 ጉዳዩ የስራ ዉል መቋረጥ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው ኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ከመዝገብ እንደሚታዉ ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ውስጥ የምግብ ባለሙያ ሁኜ በቀን 28/04/2000 ዓ.ም በወር 2500 ዶላር ደመወዝ ተቀጥሬ እየሰራሁ እያለ በቀን 22/08/2011 ዓ.ም ያለጥፋት ከህግ ውጪ ውልህን ጨርሰሀል በማለት ከስራዬ አሰናብቶኛል፣ስለዚህ ስንብቱ ህገ ወጥ ነዉ ተብሎ የአገልግሎት ክፍያ፣የካሳ ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ፣ ክፍያ የዘገየበት እና ለአውሮፕላን ቲኬት በአጠቃላይ 41,264.33 ዶላር ወይም በኢትዮጵያ ብር 1,190,477.44 ከ10% የጠበቃ አበል ጋር እንዲከፈልኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡አመልካች በበኩሉ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የተደረገው የስራ ስምምነት ለተወሰነ ጊዜ ለአንድ አመት የሚቆይ ሆኖ ውሉ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ሊቋረጥ እንደሚችል ተስማምተናል፣ተጠሪ ተቀጥሮ ሲሰራበት የቆየው የስራ መደብ ላይ የኢትዮጵያ ዜጋ በብቃት ሊሰሩ የሚችሉት ነው፡፡ለአንድ የውጪ ዜጋ ደግሞ ፈቃድ የሚሰጠው የሀገር ውስጥ ሰራተኞች ግንዛቤ እና ልምድ እስከሚያገኙ ብቻ ነው፡፡ስለዚህ የሀገር ውስጥ ዜጎች መስራት እየቻሉ የውጭ ዜጋ መስራት የለበትም፡፡ውላችን ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ ሲሆን የውጭ ዜጋ ሆኖ ተጠሪ ላልተወሰነ ጊዜ መስራቱ ከህግ ውጪ በመሆኑ ውሉ የተቋረጠው በህግ አግባብ በመሆኑ የተጠየቀው ክፍያ ሊከፈለው አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡……………..

የወ/ሮ ሐቢባ ሸምሱ ስሩር እና አቶ ቴዎድሮስ ገብሩ ብዛ ሰ.መ.ቁ.200482

የወ/ሮ ሐቢባ ሸምሱ ስሩር እና አቶ ቴዎድሮስ ገብሩ ብዛ ሰ.መ.ቁ.200482

ይህ የፍቺ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች እና የአሁን ተጠሪ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.251802 ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከተጠሪ ጋር ግንቦት 12 ቀን 2001 ዓ.ም በግብጽ ሀገር ጋብቻ ፈጽመን አብረን ሲንኖር ህጻን ሊና ቴዎድሮስ የተባለችዉን ልጅ የወለድን ቢሆንም ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ግንኙነታችን ተቋርጦ በጋብቻ መቀጠል ስላልቻልን ጋብቻችን እንዲፈርስልን በማለት ዳኝነት ጠይቃለች፡፡

የአሁን ተጠሪ በዚህ ክስ ላይ ባቀረበዉ መልስ ከአመልካች ጋር ጋብቻ አልፈጸምንም፣ በጋብቻ ሰነዱ ላይም አልፈረምኩም፣ አመልካች ጋብቻ እንደሌላቸዉ ስለመሆኑ ማስረጃ ተሰጥቷል፤ በግብጽ አገር ጋብቻ የሚፈጸመዉ በፍ/ቤት ነዉ፤ ከአመልካች ጋር በነበረን የግብረ ስጋ ግንኙነት የተጠቀሰችዉን ልጅ ከመዉለዳችን ዉጭ በጋብቻም ሆነ ጋብቻ ሳይፈጽም እንደባልና ሚስት አለመኖራቸዉን ገልጸዉ ጋብቻ በሌለበት የቀረበዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል፡፡………………….

First1011121315171819Last