ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ሲ/ር ፈለጉሽ ዳርጌ የሰ/መ/ቁጥር 217220

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ሲ/ር ፈለጉሽ ዳርጌ የሰ/መ/ቁጥር 217220

ተጠሪ ለአስተዳደር ፍርድ ቤቱ መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የይግባኝ ቅሬታ በአመልካች ዩኒቨርሲቲ ክሊኒክ ክፍል ኃላፊ በመሆን እየሰራሁ እያለ በ2006 ዓ.ም ነጻ የትምህርት እድል አግኝቼ ተምሬ ከጨረስኩ በኋላ በ2009 ዓ.ም ወደ ሥራ ተመልስሼ አመልካችን ምደባ ስጠይቅ በሥነ-ምግብ የሥራ መደብ ላይ እንድሰራ በሰኔ 09 ቀን 2009 ዓ.ም የተጻፈ የምደባ ደብዳቤ ተሰጥቶኛል፡፡ ነገር ግን የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር የሥራ መደቡ ስለሌለ ሊያሠራኝ እንደማይችል ሲገልጽልኝ ይህንኑ ለሰው ሀብት አስተዳደር ክፍል ወዲያውኑ ያሳወኩ ቢሆንም በህዳር 03 ቀን 2012 ዓ.ም በተጻፈ የጥሪ ማስታወቂያ በሥራ ላይ ላልተገኘሁበት ማስረጃ አቅርቢ ተብያለሁ፡፡ እኔም ሥራ መስራት ያልቻልኩት የሥራ ምደባ ስላልተሰጠኝ መሆኑን ብገልጽም ከታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ደመወዜ እንዳይከፈለኝ ታግዷል፡፡ በመሆኑም የሥራ ምደባ እንዲሰጠኝ እና ደመወዜ እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…….

ብርሃን አለም ጠ/አለባቸው ጊዳ እና በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ ክልል የቀጠና ሁለት አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሰ.መ.ቁ. 217202

ብርሃን አለም ጠ/አለባቸው ጊዳ እና በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ ክልል የቀጠና ሁለት አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሰ.መ.ቁ. 217202

ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ተጠሪ ሰኔ 11 ቀን 2013 ዓ.ም የጻፈው የዕግድ ደብዳቤ አመልካች በምፈልገው የእምነት ቦታ በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ውስጥ አምልኮ የማምለክ መብቴን የሚጋፋ በመሆኑ በኢ.ፌ.ድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 27(3) መሰረት ዕግዱ ህገወጥ ነው ተብሎ እንዲወሰንልኝ ሲሉ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ መልከም ንባብ…….

ወ/ሮ አለምነሽ ከፈለኝ እና አቶ ዳዊት አበራ የሰ.መ.ቁ.216626

ወ/ሮ አለምነሽ ከፈለኝ እና አቶ ዳዊት አበራ የሰ.መ.ቁ.216626

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ አባቴ አቶ አበራ ገ/ሚካኤል ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ በመሆኑ የሟች ልጅ መሆኔንና ወራሽነቴን በፍ/ቤት ያረጋገጥኩኝ ሲሆን፤ ከሳሽ ባደረብኝ ሕመም ምክንያት ሰርቼ ለማግኘት የማልችል በመሆኑ አባቴ ቀበል ሊሰጠኝ ግዴታ ያለበት ሆኖ ሳለ፤ በ6/8/2008 ዓ.ም ባደረገዉ ግልጽ ኑዛዜ ከሳሽ በዝምታ ከዉርስ በመንቀል ተከሳሾች በቀር ሌላ ወራሽ የለኝም የሚንቀሳቀስ እና የማይንቀሳቀስ ንብረቴን 1ኛ ተከሳሽ እስከ ሕልፈተ ሕይወቷ ድረስ ለብቻዋ እንዲትጠቀምበት እና ከእርሷ እልፈት በኋላ ለ2ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ሜላት አበራ ገ/ሚካኤል እንዲተላለፍ የተናዘዘዉ ከሕግና ከሞራል የሚቃረን በመሆኑ እንዲሻርልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ መልከም ንባብ…….

ወ/ሮ ማርታ ጎቤቦ እና እነ አቶ በቀለ አቤሮ የሰ/መ/ቁ. 216561

ወ/ሮ ማርታ ጎቤቦ እና እነ አቶ በቀለ አቤሮ የሰ/መ/ቁ. 216561

ጉዳዩ የውል ይፍረስልኝ የዳኝነት ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት ሃዲያ ዞን የሴሞ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ እኔ እና 1ኛ ተጠሪ ባልና ሚስት ስንሆን የጋራ ንብረታችን የሆነውን በሸቻና ሮማ ቀበሌ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ በቀለ አቤሮና ተካሽ፣ በምስራቅ ወዕሎሮ አቤሮ እንዲሁም በምዕራብ መንገድ ከሚያዋስኑት 2.8 ሄክታር የእርሻ መሬት ውስጥ 1000 ካሬ ሜትር የሚሆነውን 1ኛ ተጠሪ በቀን ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በተፃፈ ውል በመሬቱ ላይ አራት ክፍል ቤት እንዳለው እና አመልካችም በሌለሁበት በውሉ ላይ እንደፈረምኩ በማስመሰል በብር 80,000.00 ለ2ኛ ተጠሪ የሸጠለት በመሆኑ ውሉ ፈራሽ ነው ተብሎ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡መልከም ንባብ…….

አቶ አፈንዲ አብዲ እና የኢትዬጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን አዳማ ቅርንጫፍ የሰ/መ/ቁ 216415

አቶ አፈንዲ አብዲ እና የኢትዬጵያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን አዳማ ቅርንጫፍ የሰ/መ/ቁ 216415

አመልካች ባቀረቡት ክስ ፕራዶ ላንድክሩዘር መኪና የሰሌዳ ቁጥር 2-08636 ኦሮ የሻንሲ ቁጥር JTEBX9FJOBKO47153 እና የሞተር ቁጥር 0991742TR የሆነ በአቶ ዑመር አብዱራህማን አህመድ በሚባል ሰው ተመዝግቦ የሚታወቅ በቀን 02/11/2011 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭና ግዥ ውል ገዝቼ ኦርጅናል የመኪና ሰነድ በእጄ አስገብቼ ሙሉ ውክልና ሰጥቶኝ እየተጠቀምኩበት ነው፡፡ ይህ መኪና የአስመጪነት ፈቃድ ባለው ሰው አቶ መላኩ ወ/ግዬርጊስ በሚባል በህጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገባና ለአቶ ዑመር አብዱራህማን የተሸጠ ሲሆን ህጋዊ የሆነ የባለቤትነት ማስረጃ ያለው ነው፡፡ ይሁንና ተከሳሽ በቀን 02/01/2012 ዓ.ም በህጋዊ መንገድ ገዝቼ እጄ ያስገባሁትን መኪና በህገወጥ መልክ የገባ ነው በማለት የወሰደብኝ በመሆኑ ተጠሪ መኪናውን መያዙ ህገወጥ ነው ተብሎ እንዲለቀቅልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልከም ንባብ…….

First1011121315171819Last