የእነ አምሳሉ አበራ እና አሻግሬ አበራ የሰ-መ-ቁ195361

የእነ አምሳሉ አበራ እና አሻግሬ አበራ የሰ-መ-ቁ195361

.   የእነ አምሳሉ አበራ  እና አሻግሬ አበራ የሰ-መ-ቁ195361 ጉዳዩ የገጠር መሬት ዉርስ ይመለከታል፡፡ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በእስቴ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን በአሁኑ ተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ ሲሆን ይዘቱም በፍ/ቤቱ በመ/ቁ 0482874 በቀን 06/10/2010 ዓ/ም የሟች አያቶቼ አቶ አበረ ፋንቴ እና እማሆይ ፀሓይ ካሳ ወራሽነት አረጋግጨ እያለ ተጠሪም የልጅ ልጆች ሁነን እያለ የሟች መሬቶችን ብቻውን ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በመያዝ አላካፍልም ስላለኝ የሟች አያቶቼን የይዞታ መሬት ድርሻዬን እንዲካፈለኝ ውሳኔ ይሰጥልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ የሰጠው መልስ ባጭሩ አመልካች የአያታችን መሬት መጠየቅ የሚችለው ወላጆቹ ሙተው ከሆነ ነው፤አባቱ እያለ ተተኪ ወራሽ ሊሆን ስለማይገባ እና የቤተሰብ አባል ያልሆነና በውርስ ላይም ያልጠየቀ እንዲሁም ሟች አቶ አበረ ፈንቴ የሞተዉ በ1995 ዓ.ም ስለሆነ አመልካች መብት የጠየቀዉ በ2010 ዓ.ም ስለሆነ ይህ ጊዜ ሲቆጠር 15 ዓመት በመሆኑ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) መሰረት በ3 ዓመት ይርጋ መብቱ ቀሪ ሆኗል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን በአማራጭ አመልካች የቤተሰብ አባል አይደለም ከአያታቸው ጋር አላደገም በማለት ክሱ ዉድቅ እንዲደረግ መከራከሩን መዝገቡ ያሳያል፡፡……

እነ ሻለቃ ሰብሪ ቶፊቅ መሐመድ እና ሌ/ኮ/ል አለሙ ጌትነት አባተ የሰ-መ-ቁ 183941

እነ ሻለቃ ሰብሪ ቶፊቅ መሐመድ እና ሌ/ኮ/ል አለሙ ጌትነት አባተ የሰ-መ-ቁ 183941

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥር 16 ቀን 2011 በዋለው ችሎት በመዝገብ ቁጥር 72043 የሰጠው ፍርድ እና ውሳኔ እንዲሁም ይህን ፍርድ እና ውሳኔ በማፅናት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ፍርድ እና ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት በሰበር እንድታረም አመልካች መስከረም 19 ቀን 2011 ዓ/ም ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ያስቀርባል ተብሎ መዝገቡ ለችሎት ቀርቧል። 

ጉዳዩ የተጀመረው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በ2ኛ ተከሳሽነት ፣ ተጠሪ በከሳሽነት፣ የኡዴ የጋራ የመኖሪያ ቤት ኃ/የተ/የሕ/ሥራ ማህበር በ1ኛ ተከሳሽነት ፣ የአቃ/ቃ/ክ/ከ/ንግድ እና ኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤት በ3ኛ ተከሳሽነት ተከራክረዋል፡፡ የሥር ከሳሽ በክሳቸው ፣ ቀደም ሲል የኢፌዴሪ አየር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ አባል ሆነው ከሌሎች 11 የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን የሥር 1ኛ ተከሳሽ የሆነው የኡዴ የጋራ የመኖሪያ ቤት ኃ/የተ/የሕ/ሥራ ማህበር በ1997 ዓ/ም መስርተው የመዋጮ ገንዘብ በዝግ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ አድርገው በአቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ክልል ውስጥ ለቤት መስሪያ ቦታ በማህበሩ ስም ተረክበው ፤ ማህበሩ ቦታውን ተረክቦ ወደ ግንባታ ከመግባቱ በፊት ተጠሪ በ2001 ዓ/ም በወንጀል ተከሰው የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው በእስር ላይ እያሉ የቤቱን ጉዳይ እንዲከታተሉላቸው ወንድማቸው አቶ ቢንያም ጌትነትን ወክለው እያለ ፤ ተጠሪ ግዴታቸውን አልተወጡም በማለት የሥር 1ኛ ተከሳሽ ማስጠንቀቂያ ያወጣ ቢሆንም ተወካያቸው ማስጠንቀቂያው ተነስቶ ተጠሪ ግዴታቸውን ተወጥተው በአባልነታቸው እንዲቀጥሉ ያቀረቡትን ጥያቄ እና የሥር 3ኛ ተከሳሽ ድርጊቱ ተገቢ ስላልሆነ ቆሞ በአባልነታቸው እንዲቀጥሉ የጽፉትን ደብዳቤ ባለመቀበል ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን በመስጠት ተጠሪ ከአባልነት በማሰናበት አመልካችን መተካቱ ፤ የሥር 3ኛ ተከሳሽም መተካካቱ ተገቢ አለመሆኑን እያወቀ ከሥር 1ኛ ተከሳሽ ጋር ተባባሪ በመሆን በጋዜጣ በማውጣት ተጠሪ መብታቸውን እንዲያጡ ያደረገ በመሆኑ የሥር 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች አመልካችን ከማህበሩ አሰናብተው ተጠሪን ወደ አባልነት በመመለስ መብታቸውን እንዲያስከብሩላቸው ጠይቀዋል፡፡……

እነ ወ-ሮ ባህጃ ሳላህ፣ወ-ሮ ፎዚያ መሀመድ እና ወ-ሪት ምስራ አግዛ የሰ-መ-ቁጥር 184798

እነ ወ-ሮ ባህጃ ሳላህ፣ወ-ሮ ፎዚያ መሀመድ እና ወ-ሪት ምስራ አግዛ የሰ-መ-ቁጥር 184798

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካቾች ጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 84261 ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ እና የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 239167 ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታቸውን በማቅረባቸው ነው፡፡ ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ በስር ፍ/ቤት ያቀረብነው ክስ ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ የእናቷን ውክልና መሰረት በማድረግ ውርስ እንዲጣራ አድርጋ ያከራከረንን ቤት ወደ እናቷ ስም ያዛወረች በመሆኑ ይሰረዝልን የሚል ሆኖ እያለ በውርስ ህግ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1000(1) መሰረት ክሳችንን በይርጋ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን የሚል ነው፡፡………..

አቶ አሰፋ በላይ፣ የጅማ ከተማ ወረዳ 1 ፖሊስ ጽ/ቤት ዋና ሳጅን ወጋየሁ አሊ እና የጅማ ከተማ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሰ-መ-ቁ 183680

አቶ አሰፋ በላይ፣ የጅማ ከተማ ወረዳ 1 ፖሊስ ጽ/ቤት ዋና ሳጅን ወጋየሁ አሊ እና የጅማ ከተማ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሰ-መ-ቁ 183680

ይህ የጉዳት ካሳ ክርክር የተጀመረዉ በጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር 1ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች፣ እንዲሁም በዚህ ክርክር ተካፋይ ያልሆኑትን ሌሎች ሶስት የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.300905 በ11/10/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች ባቀረቡት ክስ አመልካች የቡና አምራችና ነጋዴ በመሆናቸዉ ቡና ከየቡ ከተማ ካለኝ መጋዘን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ስላነሰኝ የወረዳዉን ቡናና ሻይ ባለስልጣን በአፍ በማስፈቀድ 54 ኬሻ ቡና ከጅማ ከተማ 17 ኪ.ሜ ርቅት ላይ ወደ ምትገኘዉ የቡ ከተማ በመጓጓዝ ላይ ሳለሁ የይለፍ ፍቃድና ቡናዉ ቡናዉ በፕሎምፕ መታሸግ በማያስፈልግበት ሁኔታ ያስፈልጋል በማለት የአሁን 1ኛ ተጠሪ አባላት ሲይዙኝ የአሁን 2ኛ ተጠሪ በኮሚቴ ለጉዳዩ በፍጥነት መወሰን ሲገባዉ ባለማድረጉ የያዙትን ቡና ዋጋና በገንዘቡ እስከ አሁን ብሰራበት ኖሮ ትርፉን፣ መኪናዉ ቆሞ ላጣሁት የቀን ገቢና የጠበቃ አበል እንዲከፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል።  የአሁን ተጠሪዎች በዚህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ በኦሮሚያ ቡና ጥራት ቁጥጥርና ንግድ አዋጅ ቁ.160/2006 አንቀጽ 23 ቡናን ለማጓጓዝ የይለፍ ወረቀት እንደሚያስፈልግ፤ በቡና አዋጅ ቁጥር 602/2000 ህገ ወጥ የሆነን ቡና በመያዝ ለሚመለከተው አካል የቀረበ በመሆኑ፤ በፌደራል ደንብ ቁ.159/2001 አንቀጽ 22 (2) (ለ) ህገ ወጥ ተብሎ ለተያዘ ቡና ቅሬታ ማቅረብ የሚገባው ለሚመለከተው አካል እንጂ ለፍ/ቤት አይደለም፤ በአዋጅ ቁጥር 1051/2009 አንቀጽ 19 (7) ከአቅጣጫ ውጪ እያጓገዘ በመሆኑና በፕሎምፕም ያልታሸገ በመሆኑ በህገ ወጥ የሚጓጓዝን ቡና በህጋዊ መንገድ የያዙ በመሆኑ ልንከሰስ አይገባም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና በአማራጭ ክርክር አቅርበዋል።………….

እነ አቶ መርጋ ከበደ፣ አቶ አበራ ከበደ እና ጠ/ዮሴፍ አመንቴ የሰ-መ-ቁ-189155

እነ አቶ መርጋ ከበደ፣ አቶ አበራ ከበደ እና ጠ/ዮሴፍ አመንቴ የሰ-መ-ቁ-189155

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 48351 በቀን 01/09/2011 ዓ.ም የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 30573 በቀን 06/07/2011 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የሰጠውን ውሳኔ፤ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 313390 በቀን 29/01/2012 ዓ.ም እንዲሁም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 319820 በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በመሻራቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የተጀመረው በስር የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት ክስ ሲሆን ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡……..

First146147148149151153154155Last