ወ-ሮ ተሚማ ሬድዋን በሽር እናአቶ በድሩ ሰማን፣አቶ ደሊል በድሩ የሰ-መ-ቁ 179231

ወ-ሮ ተሚማ ሬድዋን በሽር እናአቶ በድሩ ሰማን፣አቶ ደሊል በድሩ የሰ-መ-ቁ 179231

ጉዳዩ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት በሆነ ንብረት ላይ ይገባኛል የሚለው ሰው በአንደኛው ተጋቢ ላይ ብቻ ክስ አቅርቦ ተከሣሹም  ንብረቱ የከሣሽ ነው ሲል አምኖ መከራካሩን ተክተሎ በክሱ መሰረት ከተወሰነ በኋላ ሌላኛው ተጋቢ የመቃወም አቤቱታ ሲያቀርብ ብቻውን ተከሻስ የነበረው ተጋቢ  ቀደም ሲል ያቀረበውን ክርክር ሣይለውጥ በመቀጠሉ የተወሰነው የንብረቱ ክፍል የተጋቢዎች የጋራ ሃብት መሆኑ ቢረጋገጥም በክርክሩ ያመነው ተጋቢ ድርሻ ለከሣሽ ወገን እንዲተላለፍለት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ተብሎ እንዲታረም የቀረበን የሰበር አቤቱታ ይመለከታል፡፡……….

እነ ኡባህ በዲሪ ከ ኡመር ዩሱፍ ዶላል የሰ-መ-ቁጥር 190350

እነ ኡባህ በዲሪ ከ ኡመር ዩሱፍ ዶላል የሰ-መ-ቁጥር 190350

ጉዳዩ የጫት ሽያጭ ውልን መሰረት ያደረገ የእዳ ይከፈለኝ ክስን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፋፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካቾች እንደየቅደም ተከተላቸው ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ ባቀረቡት ክስ ከአመልካቾች ጋር ባለን የጫት ንግድ ግንኙነት መነሻነት ጫቱን ቦንባስ አምጥቼ እያስረከብኳቸው ስንሰራ ቆይተናል፡፡ አመልካቾች ውሉን በራሳቸው ያቋረጡ ሲሆን ያለባቸውን የጫት ገንዘብ እዳ ብር 2,088,000 (ሁለት ሚሊዮን ሰማንያ ስምንት ሺ) እንዲከፍሉኝ ሽማግሌዎች ብልክባቸውም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው እና እዳው በሰነድ የተመላከተ ስለሆነ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 284 መሰረት በተፋጠነ ስነ ስርዓት ገንዘቡን እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

ወ-ሮ ትዕግስት ዓለሙ ቢ-አ-ኤ-ካ ኃ-የተ-የግል ማሕበ የጉባ ወረዳ አስተዳደር ጽ-ቤት፣የጉባ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ፣መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ-ቤት የሰ-መ-ቁ. 161449

ወ-ሮ ትዕግስት ዓለሙ ቢ-አ-ኤ-ካ ኃ-የተ-የግል ማሕበ የጉባ ወረዳ አስተዳደር ጽ-ቤት፣የጉባ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ፣መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ-ቤት የሰ-መ-ቁ. 161449

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ በጉባ ወረዳ ማንኩሽ ቀበሌ 10 ሄክታር የእርሻ መሬት በ1987 ዓ/ም ተመርቼ በሕጋዊ መንገድ የያዝኩትን 1ኛ ተጠሪ ፈቃድ ሳያወጣ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ትክና ካሣ ሳይከፍሉኝ ያላግባብ የይዞታ መሬቴን ለ1ኛ ተጠሪ በ2008 ዓ/ም ስለሰጡብኝ የ2008/2009 ዓ/ም የምርት ዘመን ያጣሁት የሰሊጥ ምርት ብር 115,000.00፣ ማሳ ለማዘጋጀት ያወጣሁት ብር 40,000.00፣ የማፈናቀያ ካሣ ብር 115,000.00 እና 10 ሄክታር ትክ የእርሻ መሬት እንዲሰጡኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ ያቀረበው መልስ ካሣና ትክ አስተዳደሩ የሚሰጠው እንጂ 1ኛ ተጠሪን አይመለክትም፡፡ በኢንቨስትመንት በሕጋዊ ፈቃድ የተሰጠኝ ስለሆነ ልጠየቅ አይገባም ብሏል፡፡ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው መሬቱን የሠጠው የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ እንጂ እኛ አይደለንም፡፡ ካሣው የተጋነነ ነው፡፡ ብር 40,000.00 መሬቱን ለማጽዳት ስለመውጣቱ ማስረጃ አልቀረበም፡፡ ለ21 ዓመት መሬቱ ስለታረሰ የሚጸዳ ነገር የለውም፡፡ መሬቱን የሠጠው ቢሮ በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ይታዘዝልን ብለዋል፡፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ  በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ታዞ ባለመቅረቡ ጉዳዩ በሌለበት ታይቷል፡፡..........

 

እነ ወ-ሮ ዘነበች ወንድሙ እና አቶ መስፍን ወንደሙ የሰ.መ.ቁ.185729

እነ ወ-ሮ ዘነበች ወንድሙ እና አቶ መስፍን ወንደሙ የሰ.መ.ቁ.185729

ይህ የዉርስ ንብረት ክርክር የተጀመረዉ በደቡብ ክልል ጊዲኦ ዞን በይርጋጨፌ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካቾች የሥር የመቃወም ተጠሪዎች፣ የአሁን ተጠሪ የሥር የመቃወም አመልካች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.75750 ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።………

እነ ወ-ሮ ጀማነሽ ቀነኒ፣አቶ አሰፋ ሸቡ እና ወ-ሮ ብርቱካን ሸቡ የሰ-መ-ቁጥር 177205

እነ ወ-ሮ ጀማነሽ ቀነኒ፣አቶ አሰፋ ሸቡ እና ወ-ሮ ብርቱካን ሸቡ የሰ-መ-ቁጥር 177205

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች ግንቦት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የደቡብ ብ/ብ/ህ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 11920 የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ እና የደቡብ ብ/ብ/ህ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 12667 ግንቦት 5 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልን በማለት ቅሬታቸውን በማቅረባቸው ነው፡፡ ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልን ይገባል የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤት የከተማ ማዘጋጃ ቤቱ አጣርቶ ገልጾ እያለ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከቀበሌ ጠይቆ በዚሁ ተመስርቶ የሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም፡፡ የውርስ አጣሪው ከሳሽ 12,000 ብር የተቀበለች መሆኑን ጭምር ከሪፖርቱ ጋር ሰነዱን አቅርቦ እያለ እና ድርሻዋን መውሰዷ ተረጋግጦ እያለ በድካሚ ትካፈል ተብሎ መወሰኑ ተገቢ ባለመሆኑና የተጠሪ ክስም በይርጋ ውድቅ መሆን ስገባ መታለፉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚልነው፡፡.........

First148149150151153155156157