አቶ ረዲ አህመድ እና ወ-ሮ መኪያ ሀሰን የሰ-መ-ቁ 175719 አቶ ረዲ አህመድ እና ወ-ሮ መኪያ ሀሰን የሰ-መ-ቁ 175719 ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.223910 በ10/8/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረዉ ጋብቻ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ ጋብቻችን በፍቺ እንዲፈርስ ወስኗል። ስለሆነም አመልካች እና ተጠሪ በጋራ የፈራነዉ በሱሉልታ ከተማ ልዩ ስሙ ድሬ ጀርባ የሚገኘዉ የቤት ቁጥር 632 SUL 2.1 የሆነዉ በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት እንዲንካፈል እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል። የአሁን ተጠሪ በዚህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ ይህን ቤት ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበረን ጋብቻ ከተቋረጠ በኋላ ተጠሪ ከግለሰብ ገንዘብ ተበድሬ የተሰራ ስለሆነ የጋራ ንብረት ሳይሆን የግል ንብረቴ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል።………
አመልካች፡አባይ ባንክ አ.ማ ውል ሐዋላ ገንዘብ አመልካች፡አባይ ባንክ አ.ማ ውል ሐዋላ ገንዘብ በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ በሃዋላ የተላከ ገንዘብ ባንኩ ለማይገባ ሰው ከፍሏል በሚል ባንኪ ሃላፊ መደረጉን የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ፣የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡መዝገቡ የሚያሳየው የተጠሪ የክስ ምክንያት እ.ኤ.አ በ10/12/2018 ወይም እ.ኢ.አ በ 10/04/2011 ዓ.ም ከሊባኖስ ሀገር እህቱ በአሰሪዋ በአቶ ኤልያስ ኢልሀበር አማካኝነት በዌስተርን ዩኒየን ገንዘብ መላኪያ አማካኝነት 765 የአሜሪካን ዶላር ወይም በወቅቱ ምንዛሪ ብር
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግስት ከ ቴክኒካል ትሬድንግ ኃየተየግማህበር፣ ወራሽ የሌለዉ ሀብት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግስት ከ ቴክኒካል ትሬድንግ ኃየተየግማህበር፣ ወራሽ የሌለዉ ሀብት ይህ ወራሽ የሌለዉ የዉርስ አክስዮን ድርሻ ክርክር የተጀመረዉ በፌዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.167717 ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ።
እነ የናዝሬትና አርሲ ሳሙና ፋብሪካ ኃየተየግማህበር ከ እነ አቶ ሚሊዮን መኮንን ፣ የማህበር አባልነት ጥያቄ እነ የናዝሬትና አርሲ ሳሙና ፋብሪካ ኃየተየግማህበር ከ እነ አቶ ሚሊዮን መኮንን ፣ የማህበር አባልነት ጥያቄ ይህ የማህበር አበልነት ክርክር የተጀመረዉ በአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካቾች የሥር ተከሳሾች፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር ከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዲዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካቾች የፌዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.169919 በ12/07/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።
እነ ወ/ሮ አያልነሽ ፈንቴ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ተካ የሰ-መ-ቁ182110 እነ ወ/ሮ አያልነሽ ፈንቴ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ተካ የሰ-መ-ቁ182110 አመልካች ለዚህ ችሎት ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ/ም ባቀረቡት አቤቱታ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 62378 መጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት ማስረጃ ሳይሰማ አመልካች የሟች ሚስት አይደሉም በማለት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍርድ ቤቱም በመዝገብ ቁጥር 194677 መጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት ያቀረቡትን አቤቱታ በመሰረዙ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅሬታ አቅርበው ችሎቱም በመዝገብ ቁጥር 148513 የሰበር አቤቱታቸውን የሰረዘው ሆኖ እያለ እና የአሁን ተጠሪ በሰበር መዝገብ ቁጥር 152523 ባቀረቡት ቅሬታ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፊት የተሰጠን ውሳኔን ጠቅሶ ግራ ቀኙ የሟች ሚስቶች አይደሉም በማለት የሰጠውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በመሻር በማስረጃ ተጣሪቶ እንዲወሰን ወደ ሥር ፍርድ ቤት መልሶት እያለ ፤ ይህ ውሳኔ ለአመልካችም ተፈፃሚነት ሊኖረው ሲገባ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ስላላቀረብሽ ውሳኔውን እንደተቀበልሽ ይቆጠራል በማለት ከክርክሩ እንዲወጡ በማድረግ ተጠሪ ብቻ ሚስትነታቸውን እንዲያረጋግጡ መደረጉ የእኩልነት መርህን የሚጥስ ነው በማለት ብይኑ ተሽሮ ሚስት መሆናቸውን በማስረጃ ማረጋገጥ እንዲችሉ እንዲወሰንላቸው ጠይቋል።………….