አቶ በድሩ አባገላን እና የሟች አቶ አባድጋ አባጎጃም ወራሾች የሰ.መ.ቁ.200480 አቶ በድሩ አባገላን እና የሟች አቶ አባድጋ አባጎጃም ወራሾች የሰ.መ.ቁ.200480 ይህ የእርሻ መሬት ክርክር የተጀመረዉ በየም ልዩ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.14976 በ1/9/2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ በሟች አባቴ አቶ አባገላን አባጊቤ እጅ ለ56 ዓመታት የቆየን ባህር ዛፍ ይዞታ ከዚህ ቀደም በመ.ቁ.09921 ላይ ባህር ዛፍ የሟች አባቴ ነዉ ተብሎ የተወሰነዉ የዉርስ ይዞታዬን በጉልበት ስለያዘብኝ የአሁን ተጠሪ ይዞታዉን እንዲለቅልኝ፣ የወደመዉን ንብረት ግምትና በክሱ ምክንያት የወጠዉን ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብት እንዲጠበቅልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡……………..
አቶ ታሪኩ ዮናስ እና ዳንጎቴ ኢትዮጵያ ሲምንቶ ፋብሪካ የሰበር መ/ቁ/200247 አቶ ታሪኩ ዮናስ እና ዳንጎቴ ኢትዮጵያ ሲምንቶ ፋብሪካ የሰበር መ/ቁ/200247 ጉዳዩ የአሰሪና ሠራተኛ የስራ ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩበት ነዉ፡፡አመልካች 02/06/2012 ዓ.ም ባቀረበው ክስ ተጠሪ በሰው ኃይል አስተዳደር የሥራ ዘርፍ በደብዳቤ ቁጥር DI-HR-009-14 ሕዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም በወር ደመወዝ ብር 7,100 የቀጠረኝ ሲሆን የሥራ ብቃት ምዘናዬ ከፍተኛ ስለሆነ በተለያየ ጊዜ እድገት ሰጥቶኝ በመጨረሻ በወር ደመወዝ ብር 29,980.14 እየሰራዉ እያለ ታህሳስ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ያለአንዳች ጥፋት ከስራዬ ስላሰናበተኝ በአዋጅ ቁ/1156/2011 መሰረት ወደ ስራዬ እንዲመልሰኝ ወይም ካልመለሰኝ የተለያዩ ክፍያዎች በድምሩ ብር 435,711.34 እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ በቀን 12/06/2012 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ አመልካች ከፍተኛ የኦፊሰር ስራ ዘርፍ እና የድርጅታችን የሰው ኃይል መመሪያ ኃላፊ በመሆን ሲሰራ ቆይቷል፣ሃላፊነቱ ሥራ አስኪያጅ የሆነ ሰው ደግሞ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 3(2ሐ) መሰረት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መክሰስ ስለማይችል ክሱ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ እንዲሆን ጠይቋል፡፡……………..
ወ/ሮ ህብስት ምሕረቴ እና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ የሰ/መ/ቁ. 200178 ወ/ሮ ህብስት ምሕረቴ እና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ የሰ/መ/ቁ. 200178 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኛ የነበሩ ሲሆን በወንጀል ተጠርጥረውና ተከሰው የነበረ ሲሆን በኋላም ከወንጀል ክሱ በፍርድ ቤት በነጻ በመሰናበታቸው ወደሥራ ለመመለስ አመልክተዋል፡፡ መሥሪያ ቤቱ በሰው ኃይል አስተዳደር ደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 41 መሠረት በወንጀል ተጠርጥሮ ሥልጣን ባለው አካል በእስር ላይ የነበረና እስከ ሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ከወንጀል ነጻ መሆኑ ተረጋግጦ ወደሥራ ካልተመለሰ አገልግሎቱ ይቋረጣል በሚል በግልጽ የተቀመጠ በመሆኑና አመልካች በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ጥያቄውን ያላቀረቡ በመሆኑ ተቀብለን መድበን ለማሰራት አንችልም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል፡፡………….
እማሆይ አዛል አይናለም እና አቶ ምህረት በላይ የሰ/መ/ቁ.200144 እማሆይ አዛል አይናለም እና አቶ ምህረት በላይ የሰ/መ/ቁ.200144 ጉዳዩ የስጦታ ውል እንዲፈርስ የቀረበ ክስ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ እንዲሁም የቡሬ ወረዳ መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ጽ/ቤት 2ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡የአመልካች ክስ ይዘት ባጭሩ ለተጠሪ ያደረግሁለት የሥጦታ ውል በመንፈስ ልልነት እና በዕድሜ የገፋሁ አቅመ ደካማ በመሆኔ ምክንያት ከፈቃዴ ውጭ ህጉን ሳይከተል ያደረግሁት በመሆኑ እና በስር 2ኛ ተከሳሽ ከአሁኑ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር የስጦታ ውሉን ያፀደቀ በመሆኑ የስጦታ ውሉ ይፍረስልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ ባቀረበዉ መልስ አመልካች በፈቃዷ ስጦታውን ያደረገችለት መሆኑን እና ክሱ የቀረበው የአመልካች ልጆች ከቅን ልቦና ውጭ በሆነ ሁኔታ መሬቱን ለመውሰድ በማሰብ ነዉ፤የስጦታ ውሉ የሚፈርስበት የህግ ምክንያት የለም በማለት ተከራክረዋል፡፡……………….
እነ ወ/ሮ ከጆ ሆዕለሞ እና አቶ ብርሃኑ ሸንቆ የሰ/መ/ቁ. 199518 እነ ወ/ሮ ከጆ ሆዕለሞ እና አቶ ብርሃኑ ሸንቆ የሰ/መ/ቁ. 199518 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት የሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት የአፈጻጸም ተከሳሾች ሲሆኑ ተጠሪ ደግሞ የአፈጻጸም ከሳሽ ነበሩ፡፡ ለአፈጻጸም መነሻ የሆነው አመልካቾች ሁለት ጥማድ የይዞታ መሬት ለቀው ለተጠሪ እንዲያስረክቡ ተብሎ የተሠጠው ውሳኔ ነው፡፡…………