አቶ አርላንዶ ማንድሪሊ እና ወ/ሮ አንጀሊና ሞሮኒ የሰበር መዝገብ ቁጥር 216364

አቶ አርላንዶ ማንድሪሊ እና ወ/ሮ አንጀሊና ሞሮኒ የሰበር መዝገብ ቁጥር 216364

ጉዳዩ ትዳር በፍቺ ውሳኔ መቋረጥን ተከትሎ የቀረበ የንብረት ክርክርን የሚመለከት ሆኖ  ተጠሪ የካቲት 12 ቀን 2010 ዓ/ም ባቀረቡት አቤቱታ በአቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ውስጥ የሚገኝ ቁጥሩ 156(1) የካርታ ቁጥሩ 93081(1) የሆነ በ1786 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ያረፈ ጂ + 1 የሆነ ፣ አስራ አመስት የሚከራዩ ሱቆች ያሉት ፣ ከላይ አሥር መኖሪያ ክፍሎች ያሉት  ፤ እንዲሁም በጊቢው ውስጥ የተሰራ ትልቅ መጋዘንና የተለያዩ እስቶሮችን እንዲያካፍለኝ በማለት ላቀረቡት ክስ አመልካች በሰጡት ምላሽ ፤ ተጠሪ በክሳቸው ውስጥ ያመለከቱት ቤት የአመልካች እናት በ1958 ዓ/ም 3900 ካ.ሜ ይዞታ ጋር ገዝተው 1786 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ያረፈውን የካርታ ቁጥር 93081(1) የሆነውን ቤት ሐምሌ 29 ቀን 1983 ዓ/ም ተደርጎ በውልና ማስረጃ በተመዘገበ የስጦታ ውል የተላለፈላቸው የግላቸው መሆኑን እና በዚሁ ቤት ምድር ቤት የሚከራዩ አምስት ክፍል ሱቆች ፣ የመኖሪያና የድርጅት ቤቶች ፣ ትልቁ መጋዘን ፣ ቆርቆር በቆርቆሮ የተሰሩ እስቶሮችንም በጋራ አላፈራንም በማለት ተከራክረዋል፡፡መልካም ንባብ……..

አቶ ዉድነህ መንገሻ እና የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት አካባቢ ደን እና አየር ንብረት ለዉጥ ቁጥጥር ባለስልጣን፤የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ፐብሊክና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ የሰ/መ/ቁጥር 215534

አቶ ዉድነህ መንገሻ እና የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት አካባቢ ደን እና አየር ንብረት ለዉጥ ቁጥጥር ባለስልጣን፤የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ፐብሊክና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ የሰ/መ/ቁጥር 215534

ጉዳዩ የመንግስት ሠራተኛ የደረጃ ዕድገት አሰጣጥን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልላዊ መንግስት ስቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ በ1ኛ ተጠሪ መስሪያ ቤት የአካባቢ ጥበቃ አየር ንብረት ለዉጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የስራ መደብ ላይ ተወዳድረዉ ምደባ ከተሰጣቸዉ በኋላ የ2ኛ ተጠሪ መስሪያ ቤት እንስፔክሽን ጉዳዩን ያለስልጣኑ አይቶ የተሰጣቸዉን ምደባ ሰርዞ ለሌላ ግለሰብ የሰጠ መሆኑን ጠቅሰዉ የእንስፔክሽኑ ዉሳኔ እንዲሻርላቸዉ የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡ ተጠሪዎች ለአቤቱታዉ በሰጡት መልስ 1ኛ ተጠሪ የአመልካችን የዳኝነት ጥያቄ ደግፎ የተከራከረ ሲሆን፣ 2ኛ ተጠሪ በበኩሉ መደቡ በጄኢጄ መሠረት ለቀጥተኛ የስራ ልምድ 100% ዋጋ የሚሰጥ ሲሆን በዉድድሩም አመልካች የነበራቸዉ ቀጥተኛ የስራ ልምድ 9 ዓመት ከ1 ወር ከ17 ቀን ሲሆን ከአመልካች ጋር የተወዳደሩት ሌላ ግለሰብ ከ10 ዓመት በላይ ቀጥተኛ የስራ ልምድ ያላቸዉ መሆኑ በመረጋገጡ የ2ኛ ተጠሪ እንስፔክሽን ክፍል በህግ በተሰጠዉ ስልጣን መሠረት የአመልካችን ምደባ በመሰረዝ የሰጠዉ ዉሳኔ በአግባቡ መሆኑን ጠቅሶ ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ…..

ወ/ሮ ታሪኳ ቶሎሳ እና እነ ወ/ሮ ኢትዮጵያ ግርማ የሰ/መ/ቁ. 215531

ወ/ሮ ታሪኳ ቶሎሳ እና እነ ወ/ሮ ኢትዮጵያ ግርማ የሰ/መ/ቁ. 215531

ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ክስ የቀረበበት ቤት ከ1ኛ-5ኛ ተጠሪዎች በውርስ የሚገባቸው ንብረት ነው በማለት 6ኛ ተጠሪ ቤቱን ለቀው እንዲያስረክቡ ወስኗል፡፡መልካም ንባብ…..

እነ ጋሊ አባሳንቢ እና በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤሕግ የሰ.መ.ቁ 215250

እነ ጋሊ አባሳንቢ እና በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤሕግ የሰ.መ.ቁ 215250

ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኮንታ ልዩ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካቾች እና በስር 1ኛ ተከሳሽ ላይ በስር ፍ/ቤት አሻሽሎ ያቀረባቸው ክሶች ሰባት ሲሆኑ ይዘታቸውም እንደነሚከተለው ቀርቧል መልካም ንባብ……..

First1112131416181920Last