አቶ አበበ አድገህ እና እነ ወ/ሮ ዘሪቱ ደርሰህ የሰ/መ/ቁ፡- 199400 አቶ አበበ አድገህ እና እነ ወ/ሮ ዘሪቱ ደርሰህ የሰ/መ/ቁ፡- 199400 ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ዉል መኖሩ በተካደ ጊዜ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚገባዉን ዉል አይነት የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካች በምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ ከ1ኛ ተጠሪ እና ከተራ ቁጥር 2-5 ድረስ የተጠቀሱ ተጠሪዎች አባት ከሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ ጋር በቀን 13/10/1987 ዓ/ም በተጻፈ የቤት ሽያጭ በደንበጫ ከተማ ዉስጥ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰዉን ስፋቱ 5 ሜትር በ10 ሜትር ወይም 50 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራ በሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን 32 ዚንጎ የቆርቆሮ ቤት በብር 10,000.00 ሽጠዉልኛል፡፡ገንዘቡን በእለቱ ተረክበዉ የሽያጭ ዉሉን በደንበጫ ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት አስገብተነዉ በፋይሉ ዉስጥ ይገኛል፡፡ቤቱን በግዥ ያገኘሁ ስለመሆኑ በተለያዩ ጊዜ የታመነ እና የተረጋገጠ ቢሆንም አሁን ላይ በቤቱ ለመጠቀም ስፈልግ የተለያዩ ተግባራትን እንዳላከናዉንና የቤቱ ስመ ሀብት በስሜ ዞሮ እንዳይመዘገብ ተጠሪዎች ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ስለሆነም ተጠሪዎች በሚመለከተዉ አካል ፊት ቀርበዉ የቤቱን ስመ ሀብት በስሜ እንዲያዛዉሩልኝ እንዲወሰንልኝ፡፡ዉሉ የሚፈርስበት ምክንያት አለ ከተባለም ቤቱ በአሁኑ ጊዜ የሚያወጣዉን የዕለት ዋጋ ብር 200,000.00 እንዲከፍሉኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ...........................
አቶ አክሉሉ ካሕሳይ እና አኪር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-198891 አቶ አክሉሉ ካሕሳይ እና አኪር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-198891 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበር፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር ጥር 25 ቀን 2005 ዓ/ም በተደረገ የመኪና ኪራይ ውል ስምምነት መሠረት የሠሌዳ ቁጥር 3-83597 አ.አ. የሆነ ተሽከርካሪ ለ10 ወራት ከ15 ቀናት ለሰራው ብር 346,500.00 ተጠሪ መክፈል ሲገባው ብር 100,000.00 ብቻ ከፍሎ ቀሪ ገንዘብ ስላልከፈለ ብር 246,500.00 ከሕጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡……………..
አቶ ወርቁ ኃይለመስቀል እና አቶ ከበደ ደስታየሰ/መ/ቁ፡-198805 አቶ ወርቁ ኃይለመስቀል እና አቶ ከበደ ደስታየሰ/መ/ቁ፡-198805 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ከሟች አባታቸው አቶ ደስታ አድማሱ በውርስ የሚተላለፍ የሚንቀሳቀስ እና በዚህ ችሎት ደረጃ አከራከሪ ሆነ የቀረበውን የገጠር እርሻ መሬት አመልካች ለቀው እንዲያስረክቧቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ አመልካች ስለመሬቱ ያቀረቡት መልስ ይዞታው የሟች ደስታ አድማሱና የባለቤቱና የአመልካች አያት የሆኑት የወ/ሮ እህተጊዮርጊስ ኃይለጊዮርጊስ ሲሆን አያቴ ወራሽ ስለሆን የሟች ደስታ አድማሱን ድርሻ በኑዛዜና በሥጦታ አስተላፈውልኛል፡፡ በድጋሜ ከልጆቹ ጋር መሬቱን አውርሰውኛል፡፡ የሟች ደስታ ድርሻ ሊተላፍልህ አይችልም ቢባል እንኳን የአያቴ የቤተሰብ አባል ስለሆንኩ ግማሽ ድርሻውን ተጠሪ ሊጠይቁኝ አይገባም ብለዋል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ…………….
አቶ ወንድማገኝ ታደሰ አጋር የጥበቃ አገለግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የሠ/መ/ቁጥር 198669 አቶ ወንድማገኝ ታደሰ አጋር የጥበቃ አገለግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የሠ/መ/ቁጥር 198669 ጉዳዩ የስራ ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካች በሐረር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ተጠሪ ለጥበቃ ስራ ከቀን 01/02/2010 ዓ/ም ጀምሮ በወር ብር 1,293.00 ደመወዝ እየከፈለ ሊያሰራቸዉ ቀጥሯቸዉ እስከ ቀን 13/02/2011 ዓ/ም ድረስ እየሰሩ ቆይተዉ በስራ መመዝገቢያ ላይ ፈርሜ የተረከብኩት ጥበቃ ቀጠና ውጪ ሌላ ቀጠና ላይ ሄደህ የጥበቃ ሥራ እንዲሰሩ ሲያዛቸዉ በሥራ መመዝገቢያ ላይ ፈርሜ የተረከብኩት ጥበቃ ቀጠና ላይ ችግር ቢፈጠር ተጠያቂ እሆናለሁ በማለታቸዉ ብቻ በቀን 13/02/2011 ዓ/ም ከሥራ እንዳሰናበታቸዉ ገልጸዉ ሥንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ ተብሎ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የተለያዩ ክፍያዎችን በድምሩ ብር 22,487.08 ተጠሪ እንዲከፍላቸዉ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል…………...
እነ ወ/ሮ መሠለች ደስታ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ቢሮ የሰ/መ/ቁ.193168 እነ ወ/ሮ መሠለች ደስታ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ቢሮ የሰ/መ/ቁ.193168 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች የስር ከሳሾች ሲሆኑ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ተከሳሽ እና ተጠሪ የመቃወም አመልካች ነበሩ፡፡አመልካቾች በዚህ ችሎት ደረጃ ተከራካሪ ባልሆነው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 582 በሆነ ይዞታ ያላቸው ካርታ እንዲያስተካክልና የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ሲሉ የጠየቁት ዳኝነት በፍርድ ቤቱ ውደቅ በመደረጉ ይግባኝ አቅርበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን ተመልክቶ አመልካቾች በዕጃቸው በሚገኘው 783.82 ካሬ ሜትር ይዞታ በመሆኑ ካርታውን እንዲያስተካክልና የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ወስኗል፡፡………………..