አቶ ደሣለኝ ሲሳይ እና ወ/ሮ ድማም ተክሉ የሰ/መ/ቁ፡-196963

አቶ ደሣለኝ ሲሳይ እና ወ/ሮ ድማም ተክሉ የሰ/መ/ቁ፡-196963

የሰበር አቤቱታ የቀረበው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት የሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በሚል ነው፡፡ አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ እና 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ከባለቤቴ አቶ አዘነ በየነ ጋር የባንክና የዕቁብ ዕዳ ስለነበረብን በቡራዩ ከተማ ዉስጥ የነበረንን ቤት በቀን 24/08/1999 ዓ/ም በተደረገ ዉል ሽጠን በሱሉልታ ከተማ ቁምቡሬ በተባለ ቦታ በካርታ ቁጥር ሱል/243/2005 ሆኖ የሚታወቀዉን ቤት የአሁን 2ኛ ተጠሪ ልጃችን ስለሆነ በስሙ ከአቶ ዳዊት አለሙ ላይ ገዝተናል፡፡ ይሁን እንጂ ባለቤቴ በሞት ሲለይ አመልካች ቤቱን ስለያዘብኝ ቤቱንና ሰነዱን እንዲያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡……………..

ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ ማኅበር እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሰ/መ/ቁ 196340

ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ ማኅበር እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሰ/መ/ቁ 196340

ጉዳዩ የኮንስትራክሽን ሥራ ዉል አፈጻጸም መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ የተጀመረዉ አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረተዉ ክስ ነዉ፡፡በግራ ቀኙ መካከል በቀን 10/05/2008ዓ/ም የመገጭ ግድብ የዉሃ ማማ የመሰረት ምሰሶ ጉድጓድ ቁፋሮ ግንባታ ሥራ ዉል ተደርጓል፡፡የግንባታ ዉሉ ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ(ተ.እ.ታ) ጨምሮ ብር 57,500,9200.00 ነዉ፡፡ጠቅላላ የዉል ሁኔታዎች የዉሉ አካል እንዲሆን ስምምነት ተደርጓል፡፡ተጠሪ ብር 11,500,184.00 ለአመልካች ቅድመ ክፍያ ፈጽሟል፡፡አመልካች ግንባታዉን በ360 ቀናት በማጠናቀቅ ለተጠሪ ለማስረከብ ግዴታ ገብቷል፡፡ተጠሪ የግንባታ ሥራ ቦታ ለአመልካች በቀን 29/06/2008ዓ/ም አስረክቧል፡፡ሆኖም ግንባታዉ የዘገየዉ የግንባታ ሥራዉ በሚከናወንበት ወቅት በሃገሪቱ በተለይ በአማራ ክልል ጎንደርና አካባቢ በተነሳዉ የሕዝብ አመጽ በተፈጠረ ሁከት መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀበት ጊዜ ስለነበር ከቀን 30/12/2008ዓ/ም እስከ ቀን 14/02/2009ዓ/ም ለ79 ቀናት የግንባታ ሥራዉ ተቋርጧል ……………..

ወ/ሮ መቅደስ ወልደማርያም እና አቶ ታምሩ በቀለ የሰ/መ/ቁ. 196128

ወ/ሮ መቅደስ ወልደማርያም እና አቶ ታምሩ በቀለ የሰ/መ/ቁ. 196128

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች ተቃዋሚ ሲሆኑ ተጠሪ የስር አፈጻጸም ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ ከወ/ሮ ኤደን ወንድይፍራው እና ኤድሰን ካርጎ ኃ/የተ/የግል ማሕበር ጋር ተከራክረው ገንዘብ እንዲከፈላቸው በመወሰኑ ምክንያት ውሳኔውን ለማስፈጸም የአፈጻጸም ክስ አቅርበዋል…………………..

እነ ወ/ሮ የጌራወቅ አንጋጋው እና የካ /ክ/ከ ወረዳ ዐ6 አሰተዳደር የሰ/ መ/ቁ 195656

እነ ወ/ሮ የጌራወቅ አንጋጋው እና የካ /ክ/ከ ወረዳ ዐ6 አሰተዳደር የሰ/ መ/ቁ 195656

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከተማ ይዞታ የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 251ዐዐ7 በቀን ሰኔ 15/2ዐ12 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሥር ፍ/ቤቱን ውሳኔ በማጽናት የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ያደረገበትን ትዕዛዝ በመቃወም  እንደሚከተለው ቀርቧል…………….

አቶ ሙሉጌታ ሲሳይ እና አቶ ጌትነት አለማየሁ የሰ/መ/ቁ 193443

አቶ ሙሉጌታ ሲሳይ እና አቶ ጌትነት አለማየሁ የሰ/መ/ቁ 193443

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች በቀን 28/11/2012 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 83577 በቀን 09/11/2011 ዓ.ም እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 243422 በቀን 01/07/2012 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ በስር ፍርድ ቤት ሲጀመር የአሁን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ ከሳሾች ነበሩ………………….

First1314151618202122Last