እነ አቶ መርጋ ከበደ፣ አቶ አበራ ከበደ እና ጠ/ዮሴፍ አመንቴ የሰ-መ-ቁ-189155

እነ አቶ መርጋ ከበደ፣ አቶ አበራ ከበደ እና ጠ/ዮሴፍ አመንቴ የሰ-መ-ቁ-189155

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 48351 በቀን 01/09/2011 ዓ.ም የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 30573 በቀን 06/07/2011 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የሰጠውን ውሳኔ፤ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 313390 በቀን 29/01/2012 ዓ.ም እንዲሁም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 319820 በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በመሻራቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የተጀመረው በስር የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት ክስ ሲሆን ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡……..

እነ ወ/ሮ ወርቄ ከበደ እና ወ/ሮ ዘነበች ይመር የሰ/መ/ቁ 192028

እነ ወ/ሮ ወርቄ ከበደ እና ወ/ሮ ዘነበች ይመር የሰ/መ/ቁ 192028

ሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች በቀን 01/07/2012 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፌደራል

መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 132828 በቀን 06/10/2010 ዓ.ም እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት

በመ/ቁ 219424 በቀን 28/05/2012 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁን 1ኛ አመልካች ተከሳሽ፤ እንዲሁም 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ጣ/ገብ ነበሩ፡፡

ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው ተጠሪ በቀን 24/09/2007 ዓ.ም ባቀረቡት ክስ በጻፉት አቤቱታ በአራዳ

ክ/ከተማ የሚገኝ የቤ.ቁ 200 የሆነ መኖሪያ ቤት በወላጅ አባቴ አቶ ይመር ስም ያለኝ ሲሆን አባቴ በመሞቱ ወራሽነቴ ተረጋግጦ ማስረጃ ተሰጥቶኛል፤ ተከሳሽ የእህቴ ልጅ ሚስት በመሆኗ ቤቱን ይዛ እየተጠቀመችበት ትገኛለች፣ በአሁን ግዜ ቤቱን ስለምፈልገው እንድታስረክበኝ ብጠይቃት ፈቃደኛ ባለመሆኗ ቤቱን እንድትለቅ እና እንድታስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል………

 

ህፃን ሒዳያ አማን መሀመድ እና አመተበል መሃመድ የሰ-መ-ቁ 185175

ህፃን ሒዳያ አማን መሀመድ እና አመተበል መሃመድ የሰ-መ-ቁ 185175

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 86183 በቀን 17/05/2011 ዓ/ም እንዲሁም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 2301172 በቀን 19/02/2012 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው፡፡ ክርክሩ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረው የአሁን አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ ሲሆን የአሁን ተጠሪ 1ኛ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡የአመልካች ሞግዚት በቀን 14/06/2010 ዓ/ም ባቀረቡት ማመልከቻ የህፃን ሒዳያ አማን ወላጅ አባት በቀን 21/05/2010 ዓ/ም በሞት የተለዩ ሲሆን የወራሽነት ውሳኔ በማቅረብ የሟች የውርስ ሀብት እንዲጣራ የውርስ አጣሪ እንዲሾም ጠይቀዋል፡፡ፍ/ቤቱም የሟች ውርስ እንዲጣራ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ የአሁን ተጠሪ እና ሰነያ መሀመድ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ የውርስ አጣሪ ውርሱን አጣርቶ ሪፖርት እንዲያቀርብ ባዘዘው መሰረት በቀን 26/02/2011 ዓ/ም ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ግራቀኙም አስተያየታቸውን አቅርበዋል፡፡በተለይም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-34360 ኦ.ሮ የሆነውን ተሽከርካሪ በተመለከተ የውርስ አጣሪ ባጣራው መሰረት የቀረበው ማስረጃ ተሽከርካሪው በሟች ስም የሚገኝ ቢሆንም ለ1ኛ ጣልቃገብ /የአሁን ተጠሪ/ተሽከርካው ሟችን ጨምሮ ቤተሰባቸውን እንዲረዳ እንዲሁም ለ1ኛ ጣልቃገብም ሀብት እንዲሆን የተገዛ ተሽከርካሪ እንደሆነና ገንዘቡንም ከአረብ ሀገራት በመሰራት ካገኘሁት ገቢ የተገዛ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በበኩላቸው ይህን ክደው ተከራክረዋል፡፡.............

እነ ወ-ሮ ፈይዛ ከማል አወል፣አቶ አብዲ አህመድ መሀመድ እና አቶ ካህሳይ ተስፋዝጊ የሰ-መ-ቁ 184601

እነ ወ-ሮ ፈይዛ ከማል አወል፣አቶ አብዲ አህመድ መሀመድ እና አቶ ካህሳይ ተስፋዝጊ የሰ-መ-ቁ 184601

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ን/ስ/ላ/ምድብ በኮ.መ.ቁ 88409 በ16/2/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ.መ.ቁ 222352 በ19/11/11ዓ.ም በሰጠው ብይን/ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት በ11/2/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የን/ስ/ላ/ ምድብ 4ኛ ፍ/ብሄር ችሎት በ1ኛ ተጠሪ ላይ ጋብቻቸው በፍ/ቤት በ23/4/07ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ በፍቺ መፍረሱን ተከትሎ ባቀረቡት የጋራ ንብረት ክፍፍል ክስ አከራካሪውን የሰ.ቁ ኮድ A-13872 ያሪስ መኪና ዋጋው ብር 550‚000 የሚያወጣ እና ሌሎች ንብረቶችን የእቁብ ገንዘብን ጨምሮ በመዘርዘር ንብረቶቹ የጋራችን ስለሆኑ እኩል እንድንካፈል እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት መልስ በጋብቻ ውስጥ እያለን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ቀበሌ 13 የቤት ቁጥር 069 በአቶ መሃመድ ይማም ዳኝነት በአቶ እንድሪስ አለሙ ጸሀፊነት በአቶ ወንድሜነህ አለሙ ይሰበሰብ የነበረው እቁብ በ29/4/04ዓ.ም ደርሶኝ ለትዳራችን ጥቅም ያዋልኩት ሲሆን፤ ይህን እቁብ መክፈል ባለመቻሌ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ፍ/ብሄር ችሎት በመ.ቁ 38976 ክስ ቀርቦብኝ ገንዘቡን እንድከፍል በ30/4/05ዓ.ም ተወስኖብኝ ከነወጪና ኪሳራ ብር 149‚365.95 እንድከፍል በመገደዴ አመልካች ያካፍለኝ በማለት ያቀረበችውን የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን መኪና ሸጬ እዳውን ከከፈልኩኝ በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ለትዳር ጥቅም ስለዋልኩት ጥያቄው አግባብ አይደለም በማለት ተከራክረው እንዲሁም በሌሎች ንብረቶችም ላይ መልስ የሰጡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራቀኙን በቃል ካከራከረ በኋላ ግራቀኙ በጋብቻ እያሉ የጋራቸው የሆነ እዳ ነበር ወይስ አልነበረም? አከራካሪውን የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን መኪና ግራቀኙ በትዳር እያሉ ተሸጦ ለጋራ እዳ ክፍያ እና ለትዳር ጥቅም ውሏል ወይንስ አልዋለም? የሚለውን እና ሌሎች ንብረቶችን በተመለከተ የተለያዩ ጭብጦችን በመያዝ፤ አከራካሪውን መኪና በተመለከተ ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ትእዛዝ በመስጠት ምላሽ ከቀረበለት በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የጋራ እዳን በተመለከተ 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በጋብቻ እያለን ለደረሰብኝ እዳ መክፈል ባለመቻሌ በፌ/መ/ደ/ፍቤት አራዳ ምድብ ችሎት በመ.ቁ 38976 በ30/4/05ዓ.ም ከወጪና ኪሳራ ጭምር ብር 149‚365.95 እንድከፍል ተወስኗል ያሉትን በተመለከተ እዳው የመጣው ባልና ሚስት በጋብቻ አብሮ እያሉ ስለመሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ እዳው የጋራቸው ነው በማለት ከወሰነ በኋላ ከላይ የተገለጸውን ገንዘብ እንዲከፈል የተወሰነው በ30/4/05ዓ.ም በመሆኑ ለዚህ እዳ መኪና ተሸጠ የተባለው በ2007ዓ.ም ነው፤ 1ኛ ተጠሪ መኪናው በእዳ ተይዞ ተገዶ ለመሸጡ ሆነ ገንዘቡ ከመኪና ሽያጭ ለመከፈሉ ምንም ማስረጃ አላቀረበም፤ እዳው ከተከፈለም እዳው የመጣው በጋብቻ እያሉ በመሆኑ በጋብቻ አብረው እያሉ እንደተከፈለ የሚቆጠር በመሆኑ መኪና ተሸጦ ተከፈለ በማለት 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክር ባለመቀበል፤ የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን ያሪስ የቤት መኪና አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በጋብቻ እያሉ ያልተሸጠ እና ለጋራ እዳም ሆነ ለትዳር ጥቅም ያለመዋሉ ከመረጋገጡም በላይ 1ኛ ተጠሪ ተሸጧል ሲል ቢከራከርም መኪናው ከመሸጡ በፊት በፍ/ቤት በ13/2/07ዓ.ም የታገደ መሆኑን 1ኛ ተጠሪም የሚያውቀው በመሆኑ፤ ለመሸጡ የንፋስ ስልክ ላፍቶ የመንገድና ትራንስፖርት የሰጠው መረጃ ታማኝነት የሌለው እና ውድቅ የተደረገ በመሆኑ ቢሸጥ እንኳን አስቀድሞ በፍ/ቤቱ የታገደ በመሆኑ ተገቢነት የለውም በማለት፤ በ1ኛ ተጠሪ እጅ የሚገኘው የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን ያሪስ የቤት መኪና የአመልካች እና የ1ኛ ተጠሪ የጋራ ንብረታቸው ነው በማለት፤ ክፍፍሉን በተመለከተ ከተስማሙ አንዱ ለሌላው ግምቱን በመስጠት ያስቀረው፤ በዚህ ካልተስማሙ መኪናው በሀራጅ ተሸጦ ገንዘቡን እኩል እንዲካፈሉ በማለት በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 90 መሰረት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ሌሎች ንብረቶችን በተመለከተም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡………….

እነ ወ-ሮ ሐመልማል ታመነ ወ-ሮ የምስራች ተካ እና አቶ ክፍሌ ተካ የሰ-መ -ቁ 184335

እነ ወ-ሮ ሐመልማል ታመነ ወ-ሮ የምስራች ተካ እና አቶ ክፍሌ ተካ የሰ-መ -ቁ 184335

አመልካች ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 07508 ሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችሎት በመዝገብ ቁጥር 07390 ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ፍርድ እና ውሳኔ ማፅናቱ መሠረታዊ የህግ ስህተት ነው በማለት በሰበር ለማሳረም ያቀረቡትን ቅሬታ ለመመርመር መዝገቡ ለችሎት ቀርቧል።ጉዳዩ የውርስ ንብረት እንዲጣራ የቀረበ ክርክር ሆኖ ክርክሩ በተጀመረበት የሼይ ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በከሳኝነት ፣ በሰበር ክርክሩ የሌሉት አቶ ፍቃዱ ተካ በተከሳሽነት እና አመልካች እና ሌሎች በሰበር ክርክሩ ተካፋይ ያልሆኑት 3 ሰዎች በጣልቃ ገብነት ተከራክረዋል። 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት የውርስ ይጣራ አቤቱታ ከሥር ተከሳሽ ጋር ከሟች አቶ ተካ ከበደ የሚወለዱ መሆኑንና አባታቸው ጳጉሜ 1 ቀን 2009 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ገልጸው በህይወት በነበሩበት ወቅት በሚዛን ከተማ ህብረት ቀበሌ ኮንዶሚንዬም ፊት ለፊት ከመንገድ በታች ያለው አንድ ክፍል ቤት ከይዞታው ጭምር እንዲሁም ሌሎች በሟቹ የተፈሩ ናቸው የሚሉትን ንብረቶችን በመዘርዘር የውርስ ንብረቶቹን ሌሎች በእጃቸው ይዘው የሚገለገሉበት መሆኑን ገልፀው ድርሻቸውን ማግኘት እንዲችሉ የውርስ አጣሪ ተሹሞ የውርስ ሀብቱ እንዲጣራ ፣ ወራሾች እንዲለዩ እና ንብረቶቹ በአጣሪው እንድተዳደሩ እንድወሰን አመልክቷዋል። የሥር ተከሳሽ ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ መሆኑን መዝገቡ የሚያስረዳ ሲሆን በአማራጭ በፍሬ ነገሩ ላይ ባቀረቡት መልስም በክሱ ውስጥ መብት እና ጥቅም ያላቸው አመልካች እና ሌሎች ሰዎች ስላሉ በፍርድ ቤቱ ጥር ወደ ክርክሩ እንዲገቡ ፤ የውርስ አጣሪ እንዲሾም ፤ የውርስ ንብረቱ የወራሾች የጋራ ሆኖ በሟች በመታሰቢያነት በቅርስነት እንዲቆይ ፤ ለሟች ተስካር ፣ የሙት ዓመት እና ሌሎች ወጪዎች እንድሁም ዕዳም ካለ እንድጣራ ጠይቋል። አመልካች እና ሌሎች ከውርስ ሀብቱ መብት አለቸው የተባሉትን አራት ሰዎች በፍርድ ቤቱ ጥሪ ወደ ክርክሩ ገብተው ከሥር ተከሳሽ ጋር የሚመሳሰል መልስ መስጠታቸውን ፍርድ ቤቱ  መዝግቧል። ፍርድ ቤቱ የውርስ አጣሪ የሾመ ቢሆንም የሟች ውርስ ሀብት በአግባቡ አልተጣራም በማለት ሪፖርቱ ውድቅ በማድረግ ግራ ቀኙ ወደ ክርክሩ እንድገቡ አድርጓል። የሥር ተከሳሽ በሚዛን ከተማ ህብረት ቀበሌ ኮንዶሚንየም ሰፈር ያለው ቤት በሟች ስም አለመመዝገቡ ፣ የሟች ቀለበቶች በእሱ እጅ አለመኖራቸውን ፣ ለሟች አርባ እና የተለያዩ ወጪዎች ተጣርተው ቀርበው ክፍፍል እንድደረግ ጠይቋል። ጣልቃ ገቢዎችም ተመሳሳይ ክርክር ማቅረባቸው በፍርዱ ላይ የተመላከተ ሲሆን የሥር ከሳሽም በጽሁፍ ክርክራቸው የጠየቁትን ዳኝነት በማንሳት መከራከራቸው ተመላክቷል።……….

First1415161719212223Last