እነ ቤተልሄም ጌቱ አለሙ እና የፌ/ጠ/ ዐቃቤ ህግ የሰ.መ.ቁ. 203654 እነ ቤተልሄም ጌቱ አለሙ እና የፌ/ጠ/ ዐቃቤ ህግ የሰ.መ.ቁ. 203654 የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ በሐረሪ ህዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መ.ቁ. 05450 የካቲት 01 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠውን ብይን፤ በማጽናት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መ.ቁ. 00159 የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡ ጉዳዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በሐረሪ ህዝብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካቾች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- የሙስና ወንጀል አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 31(1) እና (2) በመተላለፍ አመልካቾች የእምነት ማጉደል ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው፡፡ የአሁን አመልካቾች ክሱን በሚመለከት ያቀረቡት መቃወሚያ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 78(2)፤ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማደራጀ አዋጅ ቁጥር 322/96 አንቀጽ 2 እና በአዋጅ ቁጥር 434/97 መሰረት ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለውም፤ አመልካቾች እምነት አጉድለዋል የተባለበት የግል የጤና አገልግሎት ከሚሰጥ ድርጀት ጋር በተያያዘ እንጂ የመንግስት መስሪያ ቤት ወይም የመንግስት የልማት ድርጅት ባለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 881/2007 ስር ክስ ሊቀርብ አይገባም በማለት ከክሱ በነፃ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡………
ብሩክ አስፋው እና የፌደራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ የሰ/መ/ቁጥር 203603 ብሩክ አስፋው እና የፌደራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ የሰ/መ/ቁጥር 203603 ጉዳዩ አመልካች በኢትዮጵያ የፖሊስ ሰራዊት ላይ እንዳይፈፀም የተከለከለን ድርጊት በመፈፀሙ የወንጀል ክስ ቀርቦበት ጥፋተኛ ተብሎ በእስራት እንዲቀጣ ከተወሰነበት በኋላ የይግባኝ አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜው ስላለፈበት ይግባኙን ጊዜው ካለፈ በኋላ እንዲያቀርብ እንዲፈቀድለት ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ያቀረበ ቢሆንም የማቅረቢያ ጊዜው ያለፈውን ይግባኝ ለመቅረብ የሚያስችል በቂ ምክንያት አልቀረበም ተብሎ ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ተብሎ እንዲታረምለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነው፡፡………..
አቶ ገመቹ ቤኩማ እና የሔና ፋርም ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሰበር መ/ቁ/ 203210 አቶ ገመቹ ቤኩማ እና የሔና ፋርም ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሰበር መ/ቁ/ 203210 ጉዳዩ አመልካች ያቀረበዉ ጊዜ ያለፈበት ይግባኝ ማስፈቀጃ ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ በተጠሪ ሆቴል ውስጥ ተቀጥሬ እየሰራሁ እያለ ያለጥፋት የስራ ውል ስለአቋረጠብኝ የስራ ስንብት ክፍያዎች እንዲከፈለኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ በሰጠዉ መልስ አመልካችን አላሰናበትንም ይልቁንም አመልካች ካለበት ዕዳ ለመሸሽ ሲል ስራውን ለቆ በመሄዱ ተጠሪ ላይ ጉዳት ደርሷል በማለት ተከራክረዋል፡፡…….
ወ/ሮ ዲዮን ማክፋርላን እና ላየን ኸርት አካዳሚ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁ. 202879 ወ/ሮ ዲዮን ማክፋርላን እና ላየን ኸርት አካዳሚ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁ. 202879 ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን አመልካች በቀን 07/01/2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ ተጠሪ እኔ ባለሁበት የስራ መደብ ላይ በተመሳሳይ ለሚሰሩ ሰራተኞች የሐምሌ እና የነሐሴ ደሞዝ ሲከፍል ለእኔ ግን የሚገባኝ ክፍያ ባለመክፈል በፈፀመው ህገ-ወጥ ተግባር ሞራሌ የተነካ በመሆኑ ያልተከፈለኝን የሁለት ወር ደሞዝ፣ የስራ ስንብት ክፍያ ፣ ካሳ፣ ክፍያ በተገቢው ጊዜ ውስጥ ባለመክፈሉ ቅጣት እና የዓመት እረፍት ክፍያ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው ተከራክረዋል፡፡…………..
እነ ወ/ሮ ከበቡሽ ቡሎየ እና አቶ መንግሥቱ ባለህ ሰ/መ/ቁ. 202681 እነ ወ/ሮ ከበቡሽ ቡሎየ እና አቶ መንግሥቱ ባለህ ሰ/መ/ቁ. 202681 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች የስር ከሳሾች ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ በተጠሪ የንግድ ሥራ በልብስ ስፌት፣ በልብስ እጅ ሥራና ዝምዘማ የሥራ መደብ ተቀጥረን ስንሰራ ነሀሴ 28 ቀን 2011 ዓ/ም ከሕግ ውጭ በቃል ከሥራ አሰናብቶናል፡፡ የሥራ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ስለሆነ የአገልግሎት ክፍያ፣ ካሣ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የዓመት ዕረፍት፣ ትርፍ ሰዓት የተሰራበት ክፍያ እንዲሁም ክፍያው ለዘገየበት ቅጣት እንዲከፈላቸው እና የሥራ ልምድ እንዲሰጣቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡………..