አቶ መሃሪ አለምሶም እና የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤሕግ የሰ.መ.ቁ 218822 አቶ መሃሪ አለምሶም እና የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤሕግ የሰ.መ.ቁ 218822 የአሁን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአሁን አመልካች ላይ ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 693(1)ን በመተላለፍ በቀን 20/03/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በሀዋሳ ከተማ መሃል ክፍለ ከተማ ንጋት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ልዩ ቦታው አረብ ሰፈር በሚባልበት ከግል ተበዳይ ሉቻ ተክሉ የምትነግድበት ሥራ ቦታ ድረስ በመሄድ በኦሮሚያ ክልል እና ሲዳማ ክልል የቢሮ ዕቃዎች ለማስገባት ጨረታውን ስላሸነፍኩ ብር ቸግሮኛል በጋራ እንሰራለን ብር አበድሪኝ በማለት በተለያየ ቀን ዕቃዎችን ለመግዛት ብሎ በካሽ እና በአካውንት የወሰደውን ብር በንግድ ባንክ በሁለት ግዜ እንዲከፈል ሲል ቼክ ቁጥር BC19664274 በሆነው 1,600,000 (አንድ ሚሎዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ቀን 30/3/2013 ዓ.ም ጽፎ የሰጠ በመሆኑ እንዲሁም በቼክ ቁጥር BC19664275 በሆነው 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) በቀን 15/4/2013 ዓ.ም ጽፎ በመስጠት በአጠቃላይ ብር 3,100000 (ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ብር) የሚሆን በአመልካች ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ ውስጥ በቂ ገንዘብ እንደሌለ አጣርቶ መረጃ የተሰጠ በመሆኑ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በማዘዙ ተከሷል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…….
ማልድ የትምህርት ድጋፍ ሰጪ ኃ/የተ/የግ/ማህበርበ እናወ/ሪት ብሔር ዮናስ የሰ/መ/ቁ. 218123 ማልድ የትምህርት ድጋፍ ሰጪ ኃ/የተ/የግ/ማህበርበ እናወ/ሪት ብሔር ዮናስ የሰ/መ/ቁ. 218123 ጉዳዩ የተጀመረውም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ባቀረበችው ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከመስከረም 04 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 27,000.00 እየተከፈለኝ በመምህርነት፣ በረዳት አስተዳዳሪነት በልዩ ፍላጎት ዲፓርትመነት የአስተዳደርና ትምህርት ድጋፍ ሰጪ ኃላፊ የስራ መደብ በመሪነት፣ እንዲሁም ሰላሳ በመቶ የሚሆነውን አስተዳደራዊ ስራ እየሰራሁ ያለበቂ ምክንያት የስራ ውሌን ያቋረጠ በመሆኑ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ አመልካች ልዩ ልዩ ክፍያዎች እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡ አመልካች በበኩሉ ተጠሪ የልዩ ፍላጎት ዲፓርትመንት የአስተዳደርና ትምህርት ድጋፍ ሰጪ ኃላፊ የስራ መደብ በመሪነት እንዲሁም ሰላሳ በመቶ የሚሆነውን አስተዳደራዊ ስራ ሲሰሩ የቆዩ የስራ መሪ በመሆናቸዉ የስራ ክርክር ችሎት ጉዳዩን አይቶ የመወሰን የስረ ነገር ስልጣን የለውም የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል፡፡መልካም ንባብ…….
ስንታየሁ የግል 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና እነ አቶ ይርጋ ባይችሉ የሰ/መ/ቁ. 217836 ስንታየሁ የግል 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና እነ አቶ ይርጋ ባይችሉ የሰ/መ/ቁ. 217836 ጉዳዩ የግል የስራ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በደብረማርቆስ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ በአመልካች ትምህርት ቤት በመምህርነት ተቀጥረዉ በመስራት ላይ እያሉ ከነሐሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ አመልካች ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ እንዳይገቡ በመከልከልና ወደ ፖሊስ ሄዳችሁ ከሳችሁኛል በሚል ምክንያትም ማስጠንቀቂያ ሳይሰጣቸዉ ከስራ እንዲሰናበቱ ያደረገበት አግባብ ህገ ወጥ መሆኑን ጠቅሰዉ አመልካች ወደ ስራ እንዲመልሳቸዉ፣ ወደ ስራ የማይመለሱበት ምክንያት ካለም የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፍላቸዉ እንዲሁም ለስራ ግብርና ለጡረታ በሚል ከደመወዛቸዉ ሲቀንስ የነበረዉን ለሚመለከታቸዉ አካላት ገቢ እንዲያደርግ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ……
ዳሽን ባንክ አክስዬን ማህበር እና የኢትዬጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፤የኢትዬጵያ ብሔራዊ ባንክ የሰ/መ/ቁ 217557 ዳሽን ባንክ አክስዬን ማህበር እና የኢትዬጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፤የኢትዬጵያ ብሔራዊ ባንክ የሰ/መ/ቁ 217557 ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው ከሳሽ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ ተከሳሽ በቀን 19/02/2012 ዓ/ም እና በቀን 04/02/2013 ዓ.ም የሰጠው አስተዳደራዊ ውሳኔ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በአዋጅ ቁጥር 1183/2012 አንቀጽ 48 መሰረት ውሳኔው እንዲከለስ በማለት ጠይቋል፡፡ተከሳሽ በሰጠው መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎችንና የፍሬ ነገር ክርክሩን አቅርቧል፡፡ ባቀረበው መቃወሚያ ተከሳሽ ለጣ/ገብ በ04/02/2013 ዓ.ም የጻፈው ደብዳቤ ተከሳሽ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ ቋሚ መመሪያ እስኪወጣ ድረስ በማለት የሰጠውን መመሪያ ለማብራራት የተጻፈ ደብዳቤ እንጂ አስተዳደራዊ ውሳኔ አይደለም፡፡ በቀን 19/02/2012 ዓ.ም የወጣው መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1183/12 ከመውጣቱ በፊት የወጣ ስለሆነ አዋጁ በመመሪያው ላይ ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም፡፡ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለውም፡፡ በተጨማሪም ከሳሽ ተከሳሽ በሰጠው ውሳኔ ቅሬታውን በአዋጅ ቁጥር 1183/12 አንቀጽ 51 መሰረት ለተከሳሽ ተቋም የቅሬታ ማስተናገጃ አካል ያላቀረበ ስለሆነ ከሳሽ የተከሳሽን አስተዳደራዊ መፍትሄዎች አሟጦ ያልጨረሰ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለውም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ……..
እነ አቶ ሰለሞን እሸቱ እና ሰዓዳ ጌቱ እና ጓደኞቻቸው ሻወርና መፀዳጃ ህ/ሽ/ማህበር የሰ/መ/ቁ 216384 እነ አቶ ሰለሞን እሸቱ እና ሰዓዳ ጌቱ እና ጓደኞቻቸው ሻወርና መፀዳጃ ህ/ሽ/ማህበር የሰ/መ/ቁ 216384 ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው በስር ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት ክስ የተጠሪ ማህበር መስራች አባል መሆናቸውን ገልፀው ነገር ግን ማህበሩ 1ኛ አመልካችን የካቲት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ፣ 2ኛ አመልካችን መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሁም 3ኛ አመልካችን የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ከማህበር አባልነት አሰናብቷል:: በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ውስጠ ደንብ መሰረት ማህበሩ ፈጽማችኃል ያላቸውን ተግባሮች ያልፈፀምን ሲሆን ተፈጽመዋል ቢባል እንኳን ከአባልነት እንደሚያሰናበቱ አልተደነገገም፡፡ በመሆኑም ስንብቱ ህገወጥ በመሆኑ ተከሳሽ ማህበር ወደ አባልነታችን እንዲመልሰን እንዲወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ………