ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 ወ/ሮ በላይነሽ ኩምሳ እና ግብርና ሚኒስቴር የሰ.መ.ቁ 260594 የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለአመልካች በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/2 በ4/11/2015ዓ.ም በተጻፈ በቁጥር ማዕ/ሠ831በ/1/1 በ9/10/2015 በተጻፈ የምደባ ደብዳቤ ላይ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ውስጥ በደረጃ XVIII በመደብ ማስታወቂያ ቁጥር 13/ግብ-1094 የስራ መደብ መጠሪያ የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው መመደባቸውን በመግለጽ ሆኖም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሰራተኞች ምደባ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ከአመልካች ጋር የተወዳደሩት ተወዳዳሪው የትምህርት ደረጃ በዲፕሎማ የእንስሳት እርባታ (Animal Production and Rangeland management) ይዘው የልማት ጣቢያ ሰራተኛ ሆነው የሰሩት የስራ ልምድ አያያዝ ትክክል አይደለም በማለት ባቀረቡት ቅሬታ ላይ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው ቅሬታው ተገቢ መሆኑን ተገንዝቦ ምደባው እንዲስተካከል በወሰኑት ውሳኔ መሰረት አመልካች የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተመደቡበት የስራ ምደባ ከሀምሌ 1 ቀን 2015ዓ.ም ጀምሮ ተነስቷል በማለት በጻፈው ደብዳቤ ያሳለፈውን ውሳኔ አመልካች በመቃወም ለየኢፌዲሪ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳደር ፍርድቤት ባቀረቡት ይግባኝ ያለኝ ዲፕሎማ እንስሳት እርባታ (Animal Production and RangeLand Management) ቢሆንም የተቀጠርኩት እና ለ6 አመት ያገለገልኩት ግን ሁሉንም የግብርና ሙያ ድጋፍ ማድረግ የሚችል አጠቃላይ እርሻ ዲፕሎማ ሙያ በሚጠይቀው ማለትም 2ኛ እና 1ኛ ደረጃ ሁለገብ ልማት ጣቢያ ሰራተኛ እንደቅደም ተከተሉ ነው፡፡መልካም ንባብ….
አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947 አቶ ተስፋዬ ደገፋ እና ዶ/ር ትዕዛዙ ተፈራ ፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት፤የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 259947 ለዚህ የሰበር ክርክር ምክንያት የሆነዉ ክርክር የተጀመረዉ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በከፍተኛዉ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሾች በመሆን መከራከራቸዉን የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ያመለክታል፡፡ ክርክሩ በማህበር በመደራጀት ከተገኘዉ ይዞታ ጋር የተያያዘ ሲሆን አመልካች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ በ03/08/1990 ዓ/ም ተመዝግቦ በፀደቀዉ የመተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተደራጀ ታቦር የመኖሪያ ቤቶች ኅብረት ሥራ ማኅበር አባል በመሆን ተደራጅተዉ ማኅበሩ በሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ካገኘዉ ጠቅላላ ይዞታ ላይ መጠኑ 203.67 ካሬ ሜትር የሆነዉን የክርክሩን ይዞታ በድርሻ እንደሰጣቸዉና የዚሁ ይዞታ ሕጋዊ ባለመብት ስለመሆናቸዉም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 281839 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ጽ/ቤትና በኮልፌ ቀራኒዮ ክለ ከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት ላይ ክስ አቅርበዉ መብታቸዉ ተረጋግጦ ዉሳኔ እንዲያገኝ የሚል ነው፡መልካም ንባብ…
ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243 ወ/ሮ ሙርሽዳ ሁሴን እና ወ/ሮ አልፊያ ሁሴን (13) ሰዎች የሰ/መ/ቁ 257243 ጉዳዩ የውርስ ንብረት እና የሚስትነት ድርሻ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በጀመረበት በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች 1ኛ ጣ/ገብ ፤ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተጠሪዎች ከሳሽ፤ከ6ኛ እስከ 13ኛ ያሉ ተጠሪዎች እንዲሁ ጣ/ገብ አመልካች ነበሩ፡፡ አሁን ከ1ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተጠሪዎች አሁን በክርክሩ በሌሉ ሁለት ተከሳሾች ላይ ባቀረቡት ክስ የሟች አባታቸው አቶ ሁሴን አህመድ ንብረት የሆኑና በሟች ስም የሚገኙ 1ኛ/ በስር 1ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ በአሊቾ ውሪሮ ወረዳ ቀረሶ ቀበሌ ገሸዴ ተብሎ በሚጠራ መንደር የሚገኝ 3 ጥማድ የእርሻ መሬት፤2ኛ/ በስር 2ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ በወልቂጤ ከተማ 01 ቀበሌ የሚገኝ በ1050 ካ.ሜ ላይ ያለ የንግድ ቤት እና ከቤቱ የሚገኝ የኪራይ ገቢ፤3ኛ/ በስር 1ኛ ተከሳሽ እጅ የሚገኝ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 03-21138 የሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ፤ 4ኛ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በደቡብ ግሎባል ባንክ በሟች ስም በተከፈቱ ሂሳቦች የተቀመጠ ገንዘብ የሟች የውርስ ሀብት ስለሆነ በድርሻችን ተከሳሾች ያካፍሉን ሲሉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…
ሆሆተ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እናወ/ሮ ዘውዲቱ በዳሶ የሰ/መ/ቁ 256580 ሆሆተ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እናወ/ሮ ዘውዲቱ በዳሶ የሰ/መ/ቁ 256580 በከሳሽ የቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ ከአመልካች ፋብሪካ በሚወጣው መርዛማ ጭስ ምክንያት የግል ንብረቴ የሆነውን የሆላንድ ጥጃ ግምቱ ብር 10,000.00 (አስር ሺ) እና የሆላንድ የወተት ላም ብር 170,000.00 (አንድ መቶ ሰባ ሺህ) መስከረም 06 ቀን 2014 ዓ.ም ጥጃዋ ወዲያውኑ ስትሞት ላሚቷ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ሞታለች፡፡ስለሆነም የሆላንድ ላሟ ከነጥጃዋ የዋጋ ግምት በድምሩ ብር 180,000.00 (አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ) የሚያወጡ ሲሆን ላሟ ከመታመሟ በፊት በቀን 27 ሊትር ወተት የምትሰጥ ሲሆን የአንድ ሊትር ወተት ዋጋ ብር 40 የሚሸጥ በመሆኑ በቀን ብር 1080 (አንድ ሺህ ሰማኒያ) ሲሆን በወር ብር 32‚400 (ሰላሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ብር) ገቢ ሳገኝ የነበረ ሲሆን ላሟ ለሶስት ወር ከ 9 ቀናት ታማ ምርት በማቆም ስትታከም በነበረበት ያጣሁት ገቢ ብር 106,920.00 (አንድ መቶ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ) ጨምሮ በአጠቃላይ ብር 286 920.00 (ሁለት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሃያ እንዲወሰንልኝ የሚል ነው፡፡ተጠሪም በሰጡት መልስ ፋብሪካው ሲቋቋም በአካባቢው ላይ ተጽዕኖ የማያደርስ ስለመሆኑ ተረጋግጦ ነው፣ የክርክር መነሻ የሆኑት ጥጃ የሞተችበት እና ላሚቷ የታመመችበት ጊዜ የአመልካች ፋብሪካ ስራ ያልጀመረ በመሆኑ ለላሞቹ ሞት ምክንያት የደረሰው ጉዳት ከፋብሪካው የወጣ ጭስ ሊሆን የማይችል በመሆኑ አመልካች ለተጠሪ ጥጃ እና ላም መሞት ኃላፊነት የለበትም፤ካሳ ለመክፈልም ሊገደድ አይችልም በሚል የቀረበው ክስ ውድቅ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እና አቶ አበራ ተፈሪ የሰ/መ/ቁጥር 254101 የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እና አቶ አበራ ተፈሪ የሰ/መ/ቁጥር 254101 ጉዳዩ የጉዳት ካሳን የሚመለከት ሲሆን ክሱ በጀመረበት የፌ/ከ/ፍ/ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት የክስ ይዘትም፡- የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-53974 ኢ.ት እንዲሁም ኮድ 3-1775 ኢ.ት ለሆነው ተሽከርካሪያቸው ከአመልካች አጠቃላይ የንግድ ተሸከርካሪ የመድን ዋስትና የገዙ መሆኑን፤ ይህ መድን የተገባለት ተሸከርካሪያቸው በስራ ላይ እያለ በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ ህዳር 17 ቀን 2011 ዓ.ም ያልታወቁ ግለሰቦች አስገድደው እንዲቆም አድርገው ተሸከርካሪውን፤ጭኖት የነበረውን ቢራ እና የሽያጭ ደረሰኞች ይዘው መሰወራቸውን፤ ይህ ስርቆት መፈጸሙን የተጠሪ ወኪል እንዳወቁ ወዲያውኑ ለአመልካች ድርጅት አሶሳ ቅርንጫፍ ማሳወቃቸውን፤ ከበርካታ ክትትል በኋላ ነሀሴ 16 ቀን 2011 ዓ.ም ተሳቢው ምንም ጉዳት ሳይደርስበት የተገኘ መሆኑን እና ዋናው ተሸከርካሪ ግን ተቃጥሎ መገኘቱን፤ ነሀሴ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ፖሊስ ባደረገው ሪፖርት ተሽከርካሪው እና ተሳቢው 2,400 ሳጥን ቢራ ጭኖ ከአ.አ ወደ አሶሳ በመጓዝ ላይ እንዳለ ህዳር 17 ቀን 2011 በሌቦች ተሰርቆ ዋናው ተሸከርካሪ በቃጠሎ ከጥቅም ውጭ ሆነ መገኘቱን መግለጹን፤አመልካች ካሳ እንዲከፍል ሲጠየቅ ደርጊቲ የተፈጸመው በሽፍቶች ነው፤ በኋላ ላይ ደግሞ ድርጊቱ የተፈጸመው በጦርነት እንቅስቃሴ እና መሰል ሁኔታዎች ነው፤ እንዲሁም ስለድርጊቱ መከሰት አላሳወቃችሁኝም በማለት የካሳ ክፍያ ጥያቄአቸወን ውድቅ ማድረጉን ገልጸው ንብረቱ በእሳት ሙሉ በሙሉ የወደመ ስለሆነ በመድን ውሉ ለንብረቱ ከተሰጠው የዋስትና ጣሪያ ብር 2,000,000.00 ከተወሰነው የአደጋ መነሻ ውስጥ ከፍተኛውን 5 % ተቀናሽ በማድረግ 1,900,000.00 ከወጪና ኪሳራ ጋር አንዲከፍል ይወሰንልኝ ሲሉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…