እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807 እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807 ጉዳዩ የእግድ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሠሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የሥር ከሳሽ፣ 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ 2ኛ ተጠሪ ቤት እንዲገዛልኝ ገንዘብ ልኬለት የንብረቱን ሥመ-ሀብት በስሙ ስላደረገ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥሩ TH-14-B-4 የሆነ ቤት ያስረክበኝ ወይም ግምቱን ይክፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር እየተከራከሩ ባለበት ሁኔታ ክርክር ያስነሳው ንብረት ላይ ፍርድ ቤቱ እግድ ሠጠ፡፡ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ በመግባት ንብረቱን ከ2ኛ ተጠሪ በውል ስለገዛሁ ሊከራከሩበት አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ በክርክሩ መካከል አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ሠኔ 29 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረጉት የእርቅ ሥምምነት የገንዘብ ዕዳውን 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች ሊከፍሉና ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ ንብረቱ ላይ የተሠጠው እግድ ሳይነሳ እንዲቆይ የተስማሙ ሲሆን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 190764 ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የእርቅ ሥምምነቱን ተቀብሎ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 277 መሠረት አጽድቋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ ቁጥር 191057 ክርክር ያስነሳውን ንብረት 1ኛ ተጠሪ ስለገዙት 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲያስረክቡ ሕዳር 20 ቀን 2011 ዓ/ም የተሠጠውን ፍርድ በማያያዝ ንብረቱን በፍርድ ስላገኘሁት በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ ክርክር ምክንያት የተሠጠው እግድ እንዲነሳ በማለት አመልክተዋል፡፡ አመልካች ለእግድ ይነሳልኝ ማመልከቻው ያቀረቡት መልስ በእርቅ ስምምነቱ የተመለከተውን ገንዘብ 2ኛ ተጠሪ እስኪከፍሉ ድረስ እግዱ ጸንቶ እንዲቆይ ተስማምተን እርቁ በፍርድ ቤት የጸደቀና ይህንንም 1ኛ ተጠሪ እያወቁ ያልተቃወሙና በይግባኝ ያላስለወጡ በመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡…………
አቶ ጉዕሽ ሃይሉ ደሞዝ እና ወ-ሮ ፅጌ ገ-ሂወት የሰ-መ-ቁ 180326 አቶ ጉዕሽ ሃይሉ ደሞዝ እና ወ-ሮ ፅጌ ገ-ሂወት የሰ-መ-ቁ 180326 ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር የተጀመረዉ በመቐለ ከተማ በ02 ቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.115041 በ12/09/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።የአሁን ተጠሪ በቀበሌ ማህበራዊ ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከአመልካች ጋር ያለን ጋብቻ እንዲፈርስ፣ ትዳር ሲንመሰርት በባንክ ወደ አመልካች የሂሳብ ቁጥር ገቢ ያደረኩኝ ገንዘብ እንዲከፍለኝ፣ ለጥሎሽ ከሚገዛ ወርቅ ቀንሶ የወሰደዉ ብር 8190 እንዲከፍለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቃለች፣ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ዘርዝራለች። የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ላይ ባቀረበዉ መልስ ተጠሪ ይህን ገንዘብ ለመጠየቅ መብት የለትም፣ ትዳር ሲንፈጽም ባደረግነዉ ዉል እኔም ገንዘብ በመግጠም በመቐለ ከተማ 16 ቀበሌ ዉስጥ የአልኮል ማከፋፈያ ከፍተን ኪራይ ብር 6000 ስንከፍል ቆይተን ስምምነት ስናጣ አሁን ለዋርድያ ብር 500 እየከፈልን እየተጠበቀ ስለሆነ ለትዳር መግጠሚያ ያቀረበችዉን ገንዘብ መጠየቋ ተገቢ አይደለም፣ በትዳር ዉስጥ ትርፍም ኪሳራም የጋራ ነዉ፣ ይህ ንብረት ተቆጥሮ በገንዘብም ሆነ በዓይነት እንዲንካፈል በማለት ተከራክሯል፣ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ጠቅሷል።…………
አቶ ኢሳያስ አድማሱ አለማየሁ እና ወ-ሮ አልማዝ ተድላ ደስታ የ-ሰ-መ-ቁ 183547 አቶ ኢሳያስ አድማሱ አለማየሁ እና ወ-ሮ አልማዝ ተድላ ደስታ የ-ሰ-መ-ቁ 183547 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ 2ኛ ፍ/ብሄር ችሎት በኮ.መ.ቁ 62214 በ13/3/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ 230102 በ28/10/11ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ7/1/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ ሟች አባቴ አቶ አድማሱ አለማየሁ በ29/10/03ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ አመልካችን ከወራሽነት የነቀለ እና የወራሽነት ድርሻ የሌለኝ ያደረገ ስለሆነ ይህ ኑዛዜ ተሰርዞ በፍ/ብ/ህ/ቁ 842(1) መሰረት ከሌሎች ወራሾች እኩል ድርሻ ያለኝ መሆኑ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ የሟች ህጋዊ ሚስት ስሆን ወራሽ ባልሆን ከሚስት እና ከባለቤቴ ንብረት ድርሻ ግማሹ(50%) የኔ መሆኑ እስከታወቀ ከሌሎች ወራሾች ጋር መከሰስ የሌለብኝ በመሆኑ፤ አመልካችም ከ1ኛ ተጠሪ የሚፈልገው መብት እና ጥቅም ስለሌለ ክሱ በ1ኛ ተጠሪ ላይ መቅረቡ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 33 መሰረት ተቀባይነት የለውም የሚል ሲሆን፤ ተጠሪዎች በጋራ ባቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሟች አቶ አድማሱ አለማየሁ ግንቦት 29 ቀን 2003ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በአርባ ቀን መታሰቢያው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲነበብ አመልካችም በአካል ተገኝቶ የሰማ በመሆኑ ይህን ደግሞ መቃወም የሚችለው በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(2) በ15 ቀን ውስጥ ብቻ ሲሆን አመልካችም ለሽምግልና ዳኞች ይህን ያላደረገ በመሆኑ፤ በአንቀጽ 973(2)(3) መሰረትም እስከ 3 ወር ግዜ ውስጥ ያላቀረበ በመሆኑ ክሱ በፍ/ብ/ህጉ እና በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 244(2)(ለ) መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የተከራከሩ ሲሆን፤ ፍ/ቤቱም በመቃወሚያዎቹ ላይ ክሱን ከሰማ እና የግራቀኙን ምስክሮች ቃል ከሰማ በኋላ አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ ሰምተዋል ወይስ አልሰሙም? ያልሰሙ ከሆነ የአመልካች ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው ወይስ አይደለም? የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ ጉዳዩን መርምሮ የአመልካች ምስክሮች በሰጡት ቃል አመልካች ኑዛዜው ሲነበብ በቦታው እንዳልነበሩ እና በእለቱም አብረው መዋላቸውን ገልጸዋል ይሁን እንጂ የአመልካች እናት አመልካች የ40 ቀን መታሰቢያው ቦታ እንዲሄድ በምስክሮች በኩል ያደረጉ ቢሆንም አመልካች ግን ሳይሄድ እንደቀረ መስክረዋል፤ የተጠሪዎች ምስክሮች በበኩላቸው አመልካች የሟች አባቱ የ40 ቀን መታሰቢያ ቀን የካቲት 5 2009ዓ.ም እዛ እንደነበር ፤ የኑዛዜው ኮፒ ለአመልካች እንደተሰጠ እና ስሙም በሄኖክ አድማሱ በሚባል ተራ ቁጥር 13 ላይ የሰፈረ ነው፤ የአመልካች ስም በሄኖክ አድማሱ ስም እንደሚታወቅ ለዚህም ማሳያ የአመልካች እናት የአመልካች ስም ሄኖክ ነው ማለታቸውን 1ኛ ምስክር መስክረዋል፤ አመልካች ጠዋት 1 ሰአት ጀምሮ እዛ እንደነበር እና የኑዛዜው ድርሻ አንሶኛል ያለውም ከ1 ወር በኋላ ነው በማለት በመመስከራቸው ከግራቀኙ ምስክሮች ቃል አመልካች ኑዛዜው በሚነበብበት ወቅት ቦታው የነበረ መሆኑን የተጠሪዎች ምስክሮች ከአመልካች ምስክሮች በበለጠ እና በአሳማኝ መልኩ በመግለጻቸው የፍ/ብሄር ህግ አንቀጽ 973(2) (3) ከደነገገው አንጻር ኑዛዜው የተነበበው የካቲት 5 ቀን 2009ዓ.ም ሲሆን የአመልካች ክስ የቀረበው በ22/12/09ዓ.ም በመሆኑ ይህም ሲቆጠር ከ15(አስራ አምስት) ቀናት በኋላ ብሎም ከ3(ሶስት) ወር በኋላ በመሆኑ ፤ አመልካችም በኑዛዜው ላይ ስማቸው እስከሰፈረ ድረስ የፍ/ብ/ህ/ቁ 939 ከደነገገው እና የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 36604 እና 53223(ቅጽ 8 እና 12) ከሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች አንጻር ከኑዛዜው ተነቅያለሁ የሚባልበት አግባብ የለም ስለሆነም ክሱ በፍ/ብ/ህ/ቁ 973(1) እና 244(2) (ረ) መሰረት በይርጋ ይታገዳል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፌ/ከ/ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱም በሰጠው ትእዛዝ ይግባኙን ሰርዞታል፡፡……….
አቶ ወንድማገኝ መንግስቱ ማሞ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ-መ-ቁ 191629 አቶ ወንድማገኝ መንግስቱ ማሞ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ-መ-ቁ 191629 አቶ ወንድማገኝ መንግስቱ ማሞ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ-መ-ቁ 191629 ይህ የሰበር ጉዳይ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው ተጠሪ በአመልካች ላይ 3 የወንጀል ህግ ድንጋጌዎችን በመጥቀስ ተደራራቢ ወንጀል ፈፅሟል በማለት ያቀረበው ክስ በደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን መርምሮ በ 2 ድንጋጌ ጥፋተኛ በማድረግ በ 11 ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 5,000.00 እንዲቀጣ የሰጠው ውሣኔ በይግባኝ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመቅረቡ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ቅጣቱን በማሻሻል በ 7 ዓመት ከ 8 ወር ፅኑ እስራት እና በብር 2,500.00 እንዲቀጣ ሲወሰን ለክልሉ ከ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ሁለቱን ድንጋጌ በመተው በወንጀል ህግ አንቀፅ 543/3 ስር ብቻ ጥፋተኛ በማድረግ 5 ዓመት ፅኑ እስራት እና በብር 1,000.00 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የፈፀመ በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ ሲል አመልካች የሰበር አቤቱታ በማቅረቡ መነሻነት ነው፡፡የጉዳዩን አመጣጥ እንዲህ ነው፡፡…….
እነ አቶ አንበሳው አፈወርቅ እና አቶ አበበ ተገኝ የሠ-መ-ቁጥር 185708 እነ አቶ አንበሳው አፈወርቅ እና አቶ አበበ ተገኝ የሠ-መ-ቁጥር 185708 ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በመጀመሪያ በታየበት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥሩ አዲስ የሆነውን በ360 ካሬ ሜትር የሰፈረ ቤት በብር 650,000.00 ከተጠሪ ገዝቻለሁ፡፡ በውሉ ላይ ተጠሪ ቤቱን እንዳስረከቡ የተገለጸ ቢሆንም ቤቱን በምረከብበት ወቅት እናቴ ከዚህ አለም በሞት የተለየች በመሆኑ ችግር ስለገጠመኝ ሳልረከብ የቀረሁ ስለሆነ ሀዘኔን ጨርሼ ተጠሪ ቤቱን እንዲያስረክቡኝ ብጠይቅም ቤቱን ሊያስረክቡኝ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ቤቱን እንዲያስረክቡኝ እና በዉሉ የተመለከተዉን መቀጫ ብር 100,000.00 እንዲከፍለኙ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም ፍሬ ነገሩን በተመለከተ በሰጡት መልስ አመልካች ከተጠሪ ጋር ፈጸምኩኝ ያሉትን ወል አልፈጸምኩም፡፡ምንም ገንዘብ አልተቀበልኩም፡፡አመልካች ፈጸምኩኝ ያሉት ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት ያልተፈጸመና ሕጋዊ መሰረት የሌለዉና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1720/1 መሰረት ረቂቅ ነዉ፡፡ ከአመልካች ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት ስለነበረኝ ጉዳይ እንዲያስፈጽሙልኝ የዉክልና ሥልጣና በርካታ ሕጋዊ ሰነዶችን ሰጥቻቸዉ በእጃቸዉ የሚገኝ ቢሆንም አመልካች ዉል አለኝ የሚሉት ዉል ሳይኖርና የተቀበልኩት ገንዘብ ሳይኖር በሀሰት የቀረበ ስለሆነ ክሱ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡……..