ወ/ሮ ገነት ገሠሰ ቸኮል ፣ የአ/አ ከተማ የየካ ክ/ከተማ አስ/ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ሌሎች የሰ/መ/ቁ 180001 ወ/ሮ ገነት ገሠሰ ቸኮል ፣ የአ/አ ከተማ የየካ ክ/ከተማ አስ/ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ሌሎች የሰ/መ/ቁ 180001 ጉዳዩ ከሚመለከተው የመንግስት አካል የግንባታ ፈቃድ ተሰጥቶ ግንባታው ከተጀመረ በኋላ ፈቃዱ የተሰጠው በተጠቀሰው ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር በጥናት በተለዬ ይዞታ ላይ ነው በሚል የተሰጠውን የግንባታ ፈቃድ አግዶ የተጀመረው ግንባታ እንዲቆም መደረጉ የሁከት ተግባር ነው በሚል የቀረበውን ክስ የመረመረው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በአመልካች መብት ላይ የፈጠሩት ሁከት የለም ሲል በሰጠው ውሣኔና ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የአመልካችን ይግባኝ በመሰረዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈፅመዋል ተብሎ እንዲታረም የቀረበን ክርክር የሚመለከት ነው፡፡………….
ወ/ሮ ትዕግስት ዓለሙ ቢ/አ/ኤ/ካ ኃ/የተ/የግል ማሕበር የጉባ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት፣የጉባ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ፣መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ. 161449 ወ/ሮ ትዕግስት ዓለሙ ቢ/አ/ኤ/ካ ኃ/የተ/የግል ማሕበር የጉባ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት፣የጉባ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ፣መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ. 161449 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ በጉባ ወረዳ ማንኩሽ ቀበሌ 10 ሄክታር የእርሻ መሬት በ1987 ዓ/ም ተመርቼ በሕጋዊ መንገድ የያዝኩትን 1ኛ ተጠሪ ፈቃድ ሳያወጣ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ትክና ካሣ ሳይከፍሉኝ ያላግባብ የይዞታ መሬቴን ለ1ኛ ተጠሪ በ2008 ዓ/ም ስለሰጡብኝ የ2008/2009 ዓ/ም የምርት ዘመን ያጣሁት የሰሊጥ ምርት ብር 115,000.00፣ ማሳ ለማዘጋጀት ያወጣሁት ብር 40,000.00፣ የማፈናቀያ ካሣ ብር 115,000.00 እና 10 ሄክታር ትክ የእርሻ መሬት እንዲሰጡኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ ያቀረበው መልስ ካሣና ትክ አስተዳደሩ የሚሰጠው እንጂ 1ኛ ተጠሪን አይመለክትም፡፡ በኢንቨስትመንት በሕጋዊ ፈቃድ የተሰጠኝ ስለሆነ ልጠየቅ አይገባም ብሏል፡፡ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በበኩላቸው መሬቱን የሠጠው የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ እንጂ እኛ አይደለንም፡፡ ካሣው የተጋነነ ነው፡፡ ብር 40,000.00 መሬቱን ለማጽዳት ስለመውጣቱ ማስረጃ አልቀረበም፡፡ ለ21 ዓመት መሬቱ ስለታረሰ የሚጸዳ ነገር የለውም፡፡ መሬቱን የሠጠው ቢሮ በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ይታዘዝልን ብለዋል፡፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ በክርክሩ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ታዞ ባለመቅረቡ ጉዳዩ በሌለበት ታይቷል፡፡..........
በአማጋ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጮራ የጋዝና ኬሚካል ውጤቶች ፋብሪካ፣ሂክማ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ኃ/የተ/የቡድን ኢንተርፐራይዝ እና ሌሎች የሰ-መ-ቁ 175155 በአማጋ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጮራ የጋዝና ኬሚካል ውጤቶች ፋብሪካ፣ሂክማ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ኃ/የተ/የቡድን ኢንተርፐራይዝ እና ሌሎች የሰ-መ-ቁ 175155 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ139054 በ29/5/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 172510 በ26/7/11ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ7/8/11ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረበ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/ከ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረበው የተሻሻለ ክስ ለከሳሽ በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/98 መሰረት ለሁለት አይነት የበረኪና ምርቶች ማለትም ለትልቁ ባለ 800 ሚሊ ሊትር SEDEX እንዲሁም ለትንሹ ባለ 300 ሚሊ ሊትር SEDEX በምዝገባ ቁ.LTM/0189/2005 እና LTOW 0186/2005 በቅደም ተከተል የተመዘገበ እና እስከ 28/10/12ዓ.ም ድረስ ጸንቶ የሚቆይ የንግድ ምልክት ምዝገባ ሰርተፍኬት ከኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት በ2005ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን የንግድ ምልክቶቹ የተመዘገቡት እና ፈቃድ የተሰጠው በቃል እና በስእል(በቅርጽ) (በምስል) ከመሆኑም ባሻገር የቀለም አይነቱ በአዋጁ አንቀጽ 5(2) መሰረት ጥቁር እና ነጭ ነው፡፡ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ አላማው የተለያዩ እቃዎችን በማምረትና በማከፋፈል ወይም አገልግሎት በመስጠት የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መልካም ስም እና ዝና ለመጠበቅ እንዲሁም በተመሳሳይ ስራዎች እና አገልግለቶች መካከል ማሳከርን ለማስወገድ እና አንድን ምርት/እቃ ወይም አገልግሎት በቀላሉ ለመለየትና የንግድ ምልክቱ በአገልግሎት ተጠቃሚው (ኮንሲዩመሩ) ላይ ግርታ እንዳይፈጥር ለማድረግ ነው፡፡…………
አቶ አህመድ አብዱራህማን ከ ኢልይስ ዲተርጀንት ኢንዱስትሪ ኩባንያ የሰ-መ-ቁ 193292 አቶ አህመድ አብዱራህማን ከ ኢልይስ ዲተርጀንት ኢንዱስትሪ ኩባንያ የሰ-መ-ቁ 193292 በዚህ መዝገብ የተያዘው ክርክር የውጪ ሀገር ሰው (ኩባንያ) በንግድ ምልክት ምዝገባ ላይ ያቀረበውን የተቃዉሞ አቤቱታ መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩም ጆብ (Job) እና ሂላክ (Hilaac) የተባሉ የሳሙና ንግድ ምልክቶችን ይመለከታል፡፡ የሰበር አቤቱታው በአመልካች የቀረበውም በንግድ ምልክት የተቃውሞ አቤቱታው ላይ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በመ/ቁ 0036 በቀን 21/06/2011 ዓ.ም እንዲሁም ይግባኙ የቀረበለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 235010 በቀን 27/06/2012 ዓ.ም ያሳለፉት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ..................
አቶ ደምሴ ኦዳ ከ አቶ አሰፋ ወርቁ አቶ ደምሴ ኦዳ ከ አቶ አሰፋ ወርቁ ከፍርድ ቤት ውጪ በአማራጭ የሙግት መፍቻ መንገዶች እልባት የተሰጠ አንድ የፍትሐብሔት ጉዳይ በፍርድ ቤት ቀርቦ በቀጥታ ለአፈጻጸም ሊቀርብ የሚችልበትን ሁኔታ በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 196228 ግንቦት 25 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ