እነ አቶ ፈልመታ አምቦ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ደምሴ የሰ-መ-ቁ 189090

እነ አቶ ፈልመታ አምቦ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ደምሴ የሰ-መ-ቁ 189090

ጉዳዩ በቤት ሽያጭ ውል መሰረት ቤቱን አስለቅቆ ለመረከበ ዳኝነት ተጠይቆ በቀረበ ክስ መነሻ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ተብሎ የቀረበ የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች 2ኛ ተከሳሽ በመሆን የአሁን ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ በአመልካች እና በስር 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ዛይድ መኮንን ላይ በመሰረቱት ክስ የስር 1ኛ ተከሳሽ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በቀድሞ አጠራር ቀበሌ 02 ክልል ውስጥ በምስባክ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማኅበር ስም በካርታ ቁጥር 62/96/1119/90 ተመዝግቦ በተሰጠው ቦታ በማኅበር ተደራጅተው ተሸንሽኖ  በተሰጣቸዉ የቦታ ቁጥር 99 በሆነ 175 ካ/ሜ ቦታ ላይ የሰሩትን ጅምር ቤት በብር 145‚000.00 በቀን 29/12/1999 ዓ/ም በተደረገ ውል ሽጠውልኝ ቤቱን አስረክበውኛል፡፡ ተጠሪ በስር በ1ኛ ተከሳሽ እግር ተተክቼ ከቀን 03/13/1999 ዓ/ም ጀምሮ በአባልነት ለማህበሩ የሚከፈሉ መዋጮዎችን እየከፈልኩ ቆይቻለው፡፡የግንባታ እቃዎችን በማቅረብ የጅምር ቤቱን ግንባታ በማጠናቀቅ ላይ እያለሁ የአሁን አመልካች ቤቱን ከስር 1ኛ ተከሳሽ ገዝቻለው በማለታቸው በፍ/ቤት ክርክር ተደርጎ በመ/ቁ 291299 ላይ በቀን 29/09/1999 ዓ/ም በተሰጠ ውሳኔ አመልካች ቤቱን በሕገ-ወጥ መንገድ ይዘዋል ተብሎ ቢወሰንም አመልካች እስካሁን ድረስ ቤቱን በህገ-ወጥ መንገድ ይዘውብኝ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም አመልካች ያስከተሉብኝን የንብረት ባለቤትነት ክርክር የስር 1ኛ ተከሳሽ ተከራክረው በማስመለስ የውል ግዴታቸውን እንዲወጡ እንዲወሰንልኝ ፡፡ የአሁን አመልካች በሕገ-ወጥ መንገድ የያዙትን ቤት ለቀው እንዲያስረክቡኝ እንዲወሰንልኝ፡፡እንዲሁም አመልካች ቤቱን በሕገ-ወጥ መንገድ በመያዛቸው ያጣሁትን ገቢ አሰልቼ መጠየቅ እንድችል መብት ተጠብቆ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡……….

እነ አቶ አድማስ አደመ ከ የባህደር ዙሪያ ወረዳ የገጠር መሬት አስተዳደር ፅ/ቤት የሰ/መ/ቁጥር 189495

እነ አቶ አድማስ አደመ ከ የባህደር ዙሪያ ወረዳ የገጠር መሬት አስተዳደር ፅ/ቤት የሰ/መ/ቁጥር 189495

ክርክሩ የገጠር መሬት ይዞታን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የባህዳር ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካቾች እንደየቅደም ተከተላቸው ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ ሐምሌ 25 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ ክስ በልጆሚ ቀበሌ አምላክ ጎጥ በምስራቅ መንገድ፣ በምእራብ የግጦሽ መሬት፣ በሰሜን የግጦሽ መሬት፣ በደቡብ ፍቅሬ ባየሕ የሚያዋስኑት ስፋቱ 2 ቃዳ መሬት የቀበሌው አስተዳዳሪ እየተቃወማቸው አመልካቾች በ2011 ዓ.ም ለ2012 ዓ.ም በማረስ ሩዝ የዘሩበት ስለሆነ መሬቱ እንደለበሰ ለቀው እንዲያስረክቡ ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ …..

ወ-ሮ በድሪያ ዳውድ እና አቶ በርገና መሃመድ የሰ-መ-ቁ 184428

ወ-ሮ በድሪያ ዳውድ እና አቶ በርገና መሃመድ የሰ-መ-ቁ 184428

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች በቀን 03/02/2012 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 13570 በቀን 28/12/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው፡፡ ክርክሩ የጀመረው በስር የስልጤ ዞን በሳንኩራ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሰሽ ነበሩ፡፡ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው በወረዳ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች በቀን 22/04/2011 ዓ.ም ባቀረቡት  አቤቱታ ተከሳሽ በወረዳው ልዩ ስሙ ሀያት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኝ ዘጠኝ ጥማድ መሬት ባለቤቴ ከሀይለ ስላሴ ግዜ ጀምሮ የያዘውና በደርግ ዘመን መሬት ለአራሽ ከተባለ በኋላም 1978 ዓ.ም አካባቢ ከእኔ ጋር ትዳር መስርተን በመሬቱ አብረን እየተጠቀምንበት ቤት ሰርተን ልጅ ወልደን በ1990 ዓ.ም ባለቤቴ ዘመድ ጥየቃ ብሎ ወደ ሀድያ ዞን ሲሄድ የተጠቀሰውን መሬት፣ አንድ በሬና እኔን ከነልጄ አደራ ብሎ ሔዶ ሊመለስ አልቻለም፤ ተከሳሽም በተጣለበት አደራ መሰረት መሬቱን ለግማሽ እያረሰ እየበላን ቆይቶ መጀመሪያ መሬቱ ላይ የነበረው ቤት የፈረሰ በመሆኑ መኪዬ ሰይድ የተባለ ግለሰብ ሌላ ቤት ሰርቶልኝ እየኖርኩ 2002 ዓ.ም አካባቢ በንፋስ በመውደቁ ድጋሚ ሊሰራልን ሲል ተከሳሽ በመከልከል ከራሱ ጋር እንድቀመጥ አድርጎ እስከ 2005 ዓ.ም ድረስ መሬቱን እያረሰ ቀለቤን እየሰጠኝ ከቆየ በኋላ በሬዬንም ሽጦ ለግልጥቅሙ በማዋልና የእኔን አቅመ ደካማነት መስማትና መናገር የማልችል ረዳት የሌለኝ መሆኔን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም መሬቱን በራሱ ስር በማድረግ ከኖርኩበት ቤት ከእነልጄ አፈናቅሎኝ በሽማግሌ ሲጠየቅ ከሳሽ ያላት ሁለት ጥማድ መሬት ብቻ ነው በማለት እሱንም ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ስለሆነም አላግባብ የያዘውን መሬት እንዲለቅ፤ መሬቱ በስድስት አመት ውስጥ ቢከራይ ሊያወጣ የሚችለውን ዋጋ ብር 43,000.00 (አርባ ሶስት ሺህ)፣ ሽጦ ለግል ጥቅሙ ያዋለው የበሬ ዋጋ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ)፣ ከቤት ንብረቴ አፈናቅሎኝ ለተለያየ እንግልት ለዳረገበት ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) የሞራል ካሳ እና ለክስ ያወጣሁት ብር 5000.00 (አምስት ሺህ) በአጠቃላይ ድምር ብር 63,000.00 (ስልሳ ሶስት ሺህ) እንዲከፍለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡……….

እነ አቶ ብርቄ ደስታ፣ወ-ሮ ላቀች ገብረወልድ እና ወ-ሮ ፈለቀች በልሄ የሰ-መ-ቁ 189274

እነ አቶ ብርቄ ደስታ፣ወ-ሮ ላቀች ገብረወልድ እና ወ-ሮ ፈለቀች በልሄ የሰ-መ-ቁ 189274

ይህ ጉዳይ የተጀመረዉ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ማማ ምድር ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በ 012 ቀበሌ ልዩ ስሙ አመጃ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ የሚገኘውንና መጠኑ አራት ጥማድ የሆነውን መሬታችንን አመልካች መብት ሳይኖራቸዉ በህገ-ወጥ መንገድ የይዞታ ማረጋገጫ አውጥተዉበት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ይዘዉ እየተጠቀሙበት ስለሆነ ለቀዉ እንዲያስረክቡን ይወሰንልን በማለት የጠየቀዉን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡ አመልካች በበኩላቸዉ ክሱ በይርጋ ይታገዳል የሚለዉን የመጀመሪያ መቃወሚያ በማስቀደም ሌሎች የፍሬ ነገር ክርክሮችንም በማቅረብ ተከራክረዋል፡፡……….

ዘሀራ ሰዒድ እና የደቡብ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ መዝገቡ ሰ-መ-ቁ 193294

ዘሀራ ሰዒድ እና የደቡብ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ መዝገቡ ሰ-መ-ቁ 193294

ዘሀራ ሰዒድ እና የደቡብ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ መዝገቡ ሰ-መ-ቁ 193294

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፋ ባቀረበችው የሰበር አቤቱታ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 31781 የካቲት 09 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በስሩ ያሉት ፍርድ ቤቶች የሰጡትን የጥፋተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ በማጽናት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቧ ነው፡፡

ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጂንካ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች እና በስር 2ኛ ተከሳሸ ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ……..

First2021222325272829Last