ኢንፎኔት ኮሌጅ ለ የአቶ መንገሻ ታደሰ ወራሽ ወ/ሪት ፍቅርተ መንገሻ የሠ/መ/ቁጥር 198152

ኢንፎኔት ኮሌጅ ለ የአቶ መንገሻ ታደሰ ወራሽ ወ/ሪት ፍቅርተ መንገሻ የሠ/መ/ቁጥር 198152

ጉዳዩ ለተጠሪ ይመለስ በተባለ ቤት ላይ አመልካች ከወረዳ ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ጽ/ቤት ጋር ያደረገዉ የቤት ኪራይ ዉል እንዲፈርስ በመወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ተብሎ በቀረበ አቤቱታ መነሻ የተደረገ ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡

ተጠሪ በአሁን አመልካች እና በስር 1ኛ ተከሳሽ የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ጽ/ቤት ላይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ በአዉራሻቸዉ ስም ተመዝግቦ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ክልል ዉስጥ የቤት ቁጥር 1487 የሆነ ይዞታ ላይ የሚገኘዉን ቤት በቀን 26/04/1999ዓ/ም በተደረገ ዉል ለአሁን አመልካች ለ10 ዓመት አከራይተዉ የነበረዉን ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/1967 ያልተወረሰ ሆኖ እያለ የሥር 1ኛ ተከሳሽ ቤቱን በመንግስት እንደተወረሰ ቤት በማስመሰል የኪራይ ዉሉን በማቋረጥ በቀጥታ ራሱ ከአሁን አመልካች ጋር ከጥር 2009ዓ/ም ጀምሮ የኪራይ ዉል በመዋዋል አከራይቶታል፡፡

ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ እና አቶ ዓሊ መሃመድ ፣ወ-ሮ ዘምዘም፣ ወ-ሮ ፎዚያ መሃመድ የሰ-መ-ቁ. 187065

ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ እና አቶ ዓሊ መሃመድ ፣ወ-ሮ ዘምዘም፣ ወ-ሮ ፎዚያ መሃመድ የሰ-መ-ቁ. 187065

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆን ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረበው ክስ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 07 ቀበሌ 34 የቤት ቁጥር 787 ተመዝግቦ የሚገኘው ኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ጣቢያ ያረፈበትን ስፋቱ 1100 ካሬ ሜትር ቦታ ከአመልካች ጋር የተቀላቀለው የቀድሞው አጂፕ ኢትዮጵያ አክሲዮን ማሕበር በወቅቱ የመሬቱ ባለርስት ከነበሩት ከአቶ መሃመድ ሁሴን ጋር ባደረገው የመሬት ኪራይ ውል ከሚያዚያ 07 ቀን 1960 ዓ/ም ጀምሮ ለ30 ዓመታ በመከራየትና በቦታው ላይ በራሱ ወጪ የነዳጅ ማደያ ጣቢያ በመገንባት አገልግሎት ሲሰጥበት ቆይቶ በአዋጅ ቁጥር 47/1967 የመሬት ባለቤትነት ወደ መንግሥት ሲዛወር የኪራይ ውሉ ተቋርጦ ተከራዩ ለመንግሥት የቦታ ኪራይ እየከፈለ የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ ሆኖ እንዲጠቀም በሕግ የተረጋገጠ መብት አግኝቷል፡፡ አዋጁን ተከትሎ በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ መሠረትም የነዳጅ አከፋፋይ ድርጅቶች ይሰሩባቸው የነበሩ ይዞታዎች፣ ዲፖዎች፣ ጽ/ቤቶችና ጣቢያዎች የኩባንያዎቹ ድርጅታዊ አቋም እንደሆኑና ከመንግሥት ጋር ግንኙነታቸው እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡……….

አቶ ደጉ ናኔቻ እና የጉምሩክ ኮሚሽን የሰ-መ-ቁ 187878

አቶ ደጉ ናኔቻ እና የጉምሩክ ኮሚሽን የሰ-መ-ቁ 187878

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በመ.ቁ ከደ-2056 በ11/10/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ 239677 በ18/3/12ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ20/4/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ንብረትነቱ የአመልካች የሆነውን የሰሌዳ ቁጥር 3-A37350አ.አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ የጉምሩክ ስነስርአት ያልተፈጸመባቸው ህገወጥ የኮንትሮባንድ እቃዎች ጭኖ ሲንቀሳቀስ በ28/7/10ዓ.ም በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት አመልካች ተሸከርካሪውን እያሽከረከሩ የነበረ መሆኑ ስለተረጋገጠ በማለት በመመሪያ ቁጥር 112/08 አንቀጽ 19/20 መሰረት ተሸከርካሪው የተወረሰ ስለመሆኑ ከተጠሪ የደረሳቸውን የውርስ ውሳኔ በመቃወም ለተጠሪ አቤቱታ አጣሪ ጽ/ቤት አቤቱታ አቅርበው ጽ/ቤቱም አቤቱታውን መርምሮ የውርስ ውሳኔውን በማጽናቱ አመልካች ለኢፌዲሪ ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ባቀረቡት ይግባኝ አመልካች በወቅቱ አሽከርካሪው በህጋዊ መንገድ የቀጠርኩት አቶ ደምረው የሚባል ሰው መሆኑ፤ አመልካች የማሽከርከር ብቃት የሌለኝ እና የመኖሪያ አድራሻዬ መኪናው ከተያዘበት አካባቢ ስለሆነ መያዙ ተነግሮኝ ለማጣራት በቦታው እንደተገኘሁ እንዲሁም ፖሊስ ይዞኝ ቃሌን እንድሰጥ ያደረጉኝ ተደብድቤ ሲሆን በወቅቱ ቃላቸውን ሰጥተዋል የተባሉት የፌደራል ፖሊስ አባላት በወንጀል ክስ የአቃቤ ህግ ምስክር ሆነው በፍርድ ቤት ቀርበው በወቅቱ አመልካች አሽከርካሪ እንዳልነበር የመሰከሩ በመሆኑ አመልካችም መንዳት የማልችል በመሆኑ በተሽከርካሪው ላይ የተላለፈው የውርስ ውሳኔ አላግባብ ነው በማለት የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ ባቀረበው መልስ አመልካች በምርመራ ወቅት 4ኛ መንጃ ፈቃድ ያለው መሆኑ እና ምስክር የነበሩት የፌደራል ፖሊሶች ሲያሽከረክር የነበረው አመልካች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የፌደራል ፖሊሶች በፍርድ ቤት ቀርበው አመልካች ሳይሆን ሌላ ሰው ነው የሚል የምስክርነት ቃል ያልሰጡ ከመሆኑም በላይ ቃል የሰጠሁት ተገድጄ ነው ቢልም በምርመራ ወቅት መብቱ እና ግዴታው ተነግሮት ቃሉን በገዛ ፈቃዱ የሰጠ በመሆኑ በተሽከርካሪው ላይ የተላለፈው የውርስ ውሳኔ በጉምሩክ አዋጅ እና መመሪያ መሰረት ነው በማለት ተከራክሯል፡፡.............

 

እነ ወ-ሮ ብርሃን ገ/መድህን እና የሐውዜን ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሰ-መ-ቁ 182677

እነ ወ-ሮ ብርሃን ገ/መድህን እና የሐውዜን ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሰ-መ-ቁ 182677

ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የይዞታ ክርክርን የተመለከተ ሲሆን አመልካቾች የሟች ቄስ ገ/መድህን ገብሩ ልጆች የአባታችን ስፋቱ 500 ካ.ሜ የሆነ የከተማ ነባር ይዞታ ቤትና ቦታ በስማችን ተመዝግቦ ማስረጃ እንዲሰጠን ይወሰንልን በማለት ያቀረቡትን ክስ መነሻ ያደረገ ሲሆን አመልካቾች በስር በሓውዜን ወረደ ፍርድ ቤት ከሳሾች የነበሩ ሲሆን ተጠሪ  ተከሳሽ ነበር፡፡አመልካቾች በስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስም በሓውዜን ከተማ 03 ቀበሌ የሚገኝ አዋሰኙ በክሱ የተጠቀሰውን የሟች አባታችን ቄስ ገ/መድህን ገብሩ ነባር ይዞታና ቤት፣ አትክልትና ቦታ በአጣሪ ኮሚቴ የተጣራልን የሓውዜን ከተማ አስተዳደር ወደ ሓውዜን ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሊያስተላልፉልን ስላልቻሉ ክስ መስርተን የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ወደ ሓውዜን ከተማ ልማት /ማዘጋጃ ቤት/ ወስኖ በአፈፃፀም ከተላለፈልን በኋላ የሓውዜን ከተማ ማዘጋጃ ቤትን በመመሪያ መሰረት 500 ካ.ሜ ቦታ ይተላለፍልን ብለን ስንጠይቀው የሚሰጣችሁ 140 ካ.ሜ ቦታ ነው ስላለን ወደ አቤቱታ ሰሚ አካል ሄደንም ጉዳዪን ማየት የሚችለው ፍ/ቤት ነው የሚል መልስ ስለተሰጠን ሟች አባታችን ነባር ይዞታ የነበረው መሆኑ የተረጋገጠ ስለሆነ በደንብ ቁጥር 12/102/84 ክፍል 1-2 ለ-7 መሰረት 500 ካ.ሜ እንዲሰጠን ይወሰንልን በማለት አመልክተዋል፡፡ ተጠሪ በሰጠው መልስም የአሁን አመልካቾች 1ኛ አመልካች በተወሰነላቸው መሰረት እናስተላልፍላችሁ ብንላቸውም ፍቃደኛ አይደሉም፤ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች የሚመለከተቸው ከሆነ መጠያቅ የሚገባቸው 1ኛ አመልካችን እንጂ እኛን አይደለም፤ አመልካቾች የክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰጠው ፍርድ መሰረት 140 ካ.ሜ እናስተላልፍላችሁ ብንልም 500 ካ.ሜ ካልሆነ አንቀበልም ብለዋል ስለሆነም የአመልካቾች ክስ አግባብነት ስለሌለው ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል፡፡………….

አቶ ሀበን ግዑሽ እና ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ የሰ-መ-ቁ. 188331

አቶ ሀበን ግዑሽ እና ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ የሰ-መ-ቁ. 188331

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡ ተጠሪ ያቀረበው ክስ ከአመልካች ጋር ጥቅምት 25 ቀን 2002 ዓ/ም፣ መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ/ም፣ ሕዳር 12 ቀን 2004 ዓ/ም፣ ሀምሌ 30 ቀን 2004 ዓ/ም፣ ሕዳር 21 ቀን 2005 ዓ/ም እና ሕዳር 21 ቀን 2005 ዓ/ም የነዳጅ ማደያ ጣቢያ ኦፕሬተር/ዲለር ሥምምነቶች ተደርጓል፡፡ አመልካች የነዳጅ ውጤቶችን በጅምላ እየገዙ በሽሬ ከተማ፣ ሞጆ ከተማ፣ ዳንሻ ከተማ፣ ሁመራ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ሁለት ቦታ ላይ ባሉ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ለመቸርቸርና የማደያ ጣቢያ አገልግሎት ለመስጠት ግዴታ ገብተዋል፡፡ አመልካች የተረከቧቸውን የነዳጅ ውጤት ምርቶችን ባለመክፈላቸው በተለያዩ ጊዜያት ዕዳ ተሳስበን የሚከፍሉበት ጊዜ ተወስኗል፡፡ ክፍያ በማቋረጣቸውም ጥር 23 ቀን 2008 ዓ/ም በተደረገ 3ኛ የውል ማሻሻያ ሥምምነት በ2ኛው የውል ማሻሻያ ከተመለከተው ያልተከፈለው ብር 24,275,805.86 በየወሩ ብር 1,391,255.80 ሊከፍሉና ተጨማሪ አመልካች በዱቤ ሽያጭ የተረከቧቸውን ምርቶች ዋጋ ብር 8,816,151.10 በየወሩ ብር 367,339.63 ከፍለው ሊያጠናቅቁ የተስማማን ሲሆን ጎን ለጎን ሥራውን እንዲሰሩ፣ ወርሃዊ ዕዳ አከፋፈል የጊዜ ሠሌዳ ባያከብሩ በ3ኛው የውል ማሻሻያ ሥምምነት አንቀጽ 6 እና 2.13 እንዲሁም በስድስቱ የኦፕሬተር/ዲለር ውሎች አንቀጽ 5.3፣ 12፣ 13 እና 14 መሠረት ውሎችን የማቋረጥና ዕዳውን አጠቃሎ የማስመለስ መብት እንዳለን ተመልክቷል፡፡ አመልካች ለሠባት ተከታታይ ወራት ምንም ክፍያ አልከፈሉም፡፡ አራት ቼኮች ዋጋቸው ብር 27,902,795.60 የሆኑ የሠጡ ቢሆንም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቂ ስንቅ ስለሌላቸው ክፍያ ሊፈጸም አለመቻሉን ገልጾ ቼኮቹን መልሷል፡፡ ለአመልካች ክፍያውን እንዲፈጽሙ ግንቦት 01 ቀን 2008 ዓ/ም ማስጠንቀቂያ የተሠጣቸው ቢሆንም አልከፈሉም፤ የውል ግዴታቸው ጥሰው ከስድስት ወራት በላይ ማደያዎች አገልግሎት ሳይሰጡ ያለስራ እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡ ስለዚህ በ3ኛው የውል ማሻሻያ ሥምምነት መሠረት ብር 33,091,956.96 ከሕጋዊ ወለድ ጋር አመልካች ለተጠሪ እንዲከፍሉ እንዲወሰን ዳኝነት ጠይቋል፡፡………..

First2122232426282930Last