እነ ወ-ሮ ባህጃ ሳላህ፣ወ-ሮ ፎዚያ መሀመድ እና ወ-ሪት ምስራ አግዛ የሰ-መ-ቁጥር 184798 እነ ወ-ሮ ባህጃ ሳላህ፣ወ-ሮ ፎዚያ መሀመድ እና ወ-ሪት ምስራ አግዛ የሰ-መ-ቁጥር 184798 ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካቾች ጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 84261 ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ እና የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 239167 ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታቸውን በማቅረባቸው ነው፡፡ ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ በስር ፍ/ቤት ያቀረብነው ክስ ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ የእናቷን ውክልና መሰረት በማድረግ ውርስ እንዲጣራ አድርጋ ያከራከረንን ቤት ወደ እናቷ ስም ያዛወረች በመሆኑ ይሰረዝልን የሚል ሆኖ እያለ በውርስ ህግ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1000(1) መሰረት ክሳችንን በይርጋ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን የሚል ነው፡፡………..
አቶ አሰፋ በላይ፣ የጅማ ከተማ ወረዳ 1 ፖሊስ ጽ/ቤት ዋና ሳጅን ወጋየሁ አሊ እና የጅማ ከተማ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሰ-መ-ቁ 183680 አቶ አሰፋ በላይ፣ የጅማ ከተማ ወረዳ 1 ፖሊስ ጽ/ቤት ዋና ሳጅን ወጋየሁ አሊ እና የጅማ ከተማ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሰ-መ-ቁ 183680 ይህ የጉዳት ካሳ ክርክር የተጀመረዉ በጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር 1ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች፣ እንዲሁም በዚህ ክርክር ተካፋይ ያልሆኑትን ሌሎች ሶስት የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.300905 በ11/10/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች ባቀረቡት ክስ አመልካች የቡና አምራችና ነጋዴ በመሆናቸዉ ቡና ከየቡ ከተማ ካለኝ መጋዘን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ስላነሰኝ የወረዳዉን ቡናና ሻይ ባለስልጣን በአፍ በማስፈቀድ 54 ኬሻ ቡና ከጅማ ከተማ 17 ኪ.ሜ ርቅት ላይ ወደ ምትገኘዉ የቡ ከተማ በመጓጓዝ ላይ ሳለሁ የይለፍ ፍቃድና ቡናዉ ቡናዉ በፕሎምፕ መታሸግ በማያስፈልግበት ሁኔታ ያስፈልጋል በማለት የአሁን 1ኛ ተጠሪ አባላት ሲይዙኝ የአሁን 2ኛ ተጠሪ በኮሚቴ ለጉዳዩ በፍጥነት መወሰን ሲገባዉ ባለማድረጉ የያዙትን ቡና ዋጋና በገንዘቡ እስከ አሁን ብሰራበት ኖሮ ትርፉን፣ መኪናዉ ቆሞ ላጣሁት የቀን ገቢና የጠበቃ አበል እንዲከፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል። የአሁን ተጠሪዎች በዚህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ በኦሮሚያ ቡና ጥራት ቁጥጥርና ንግድ አዋጅ ቁ.160/2006 አንቀጽ 23 ቡናን ለማጓጓዝ የይለፍ ወረቀት እንደሚያስፈልግ፤ በቡና አዋጅ ቁጥር 602/2000 ህገ ወጥ የሆነን ቡና በመያዝ ለሚመለከተው አካል የቀረበ በመሆኑ፤ በፌደራል ደንብ ቁ.159/2001 አንቀጽ 22 (2) (ለ) ህገ ወጥ ተብሎ ለተያዘ ቡና ቅሬታ ማቅረብ የሚገባው ለሚመለከተው አካል እንጂ ለፍ/ቤት አይደለም፤ በአዋጅ ቁጥር 1051/2009 አንቀጽ 19 (7) ከአቅጣጫ ውጪ እያጓገዘ በመሆኑና በፕሎምፕም ያልታሸገ በመሆኑ በህገ ወጥ የሚጓጓዝን ቡና በህጋዊ መንገድ የያዙ በመሆኑ ልንከሰስ አይገባም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና በአማራጭ ክርክር አቅርበዋል።………….
እነ አቶ መርጋ ከበደ፣ አቶ አበራ ከበደ እና ጠ/ዮሴፍ አመንቴ የሰ-መ-ቁ-189155 እነ አቶ መርጋ ከበደ፣ አቶ አበራ ከበደ እና ጠ/ዮሴፍ አመንቴ የሰ-መ-ቁ-189155 የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 48351 በቀን 01/09/2011 ዓ.ም የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 30573 በቀን 06/07/2011 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የሰጠውን ውሳኔ፤ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 313390 በቀን 29/01/2012 ዓ.ም እንዲሁም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 319820 በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በመሻራቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የተጀመረው በስር የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት ክስ ሲሆን ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡……..
እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807 እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807 ጉዳዩ የእግድ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሠሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የሥር ከሳሽ፣ 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ 2ኛ ተጠሪ ቤት እንዲገዛልኝ ገንዘብ ልኬለት የንብረቱን ሥመ-ሀብት በስሙ ስላደረገ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥሩ TH-14-B-4 የሆነ ቤት ያስረክበኝ ወይም ግምቱን ይክፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር እየተከራከሩ ባለበት ሁኔታ ክርክር ያስነሳው ንብረት ላይ ፍርድ ቤቱ እግድ ሠጠ፡፡ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ በመግባት ንብረቱን ከ2ኛ ተጠሪ በውል ስለገዛሁ ሊከራከሩበት አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ በክርክሩ መካከል አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ሠኔ 29 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረጉት የእርቅ ሥምምነት የገንዘብ ዕዳውን 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች ሊከፍሉና ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ ንብረቱ ላይ የተሠጠው እግድ ሳይነሳ እንዲቆይ የተስማሙ ሲሆን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 190764 ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የእርቅ ሥምምነቱን ተቀብሎ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 277 መሠረት አጽድቋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ ቁጥር 191057 ክርክር ያስነሳውን ንብረት 1ኛ ተጠሪ ስለገዙት 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲያስረክቡ ሕዳር 20 ቀን 2011 ዓ/ም የተሠጠውን ፍርድ በማያያዝ ንብረቱን በፍርድ ስላገኘሁት በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ ክርክር ምክንያት የተሠጠው እግድ እንዲነሳ በማለት አመልክተዋል፡፡ አመልካች ለእግድ ይነሳልኝ ማመልከቻው ያቀረቡት መልስ በእርቅ ስምምነቱ የተመለከተውን ገንዘብ 2ኛ ተጠሪ እስኪከፍሉ ድረስ እግዱ ጸንቶ እንዲቆይ ተስማምተን እርቁ በፍርድ ቤት የጸደቀና ይህንንም 1ኛ ተጠሪ እያወቁ ያልተቃወሙና በይግባኝ ያላስለወጡ በመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡…………
ህፃን ሒዳያ አማን መሀመድ እና አመተበል መሃመድ የሰ-መ-ቁ 185175 ህፃን ሒዳያ አማን መሀመድ እና አመተበል መሃመድ የሰ-መ-ቁ 185175 የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 86183 በቀን 17/05/2011 ዓ/ም እንዲሁም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 2301172 በቀን 19/02/2012 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው፡፡ ክርክሩ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረው የአሁን አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ ሲሆን የአሁን ተጠሪ 1ኛ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡የአመልካች ሞግዚት በቀን 14/06/2010 ዓ/ም ባቀረቡት ማመልከቻ የህፃን ሒዳያ አማን ወላጅ አባት በቀን 21/05/2010 ዓ/ም በሞት የተለዩ ሲሆን የወራሽነት ውሳኔ በማቅረብ የሟች የውርስ ሀብት እንዲጣራ የውርስ አጣሪ እንዲሾም ጠይቀዋል፡፡ፍ/ቤቱም የሟች ውርስ እንዲጣራ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ የአሁን ተጠሪ እና ሰነያ መሀመድ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ የውርስ አጣሪ ውርሱን አጣርቶ ሪፖርት እንዲያቀርብ ባዘዘው መሰረት በቀን 26/02/2011 ዓ/ም ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ግራቀኙም አስተያየታቸውን አቅርበዋል፡፡በተለይም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-34360 ኦ.ሮ የሆነውን ተሽከርካሪ በተመለከተ የውርስ አጣሪ ባጣራው መሰረት የቀረበው ማስረጃ ተሽከርካሪው በሟች ስም የሚገኝ ቢሆንም ለ1ኛ ጣልቃገብ /የአሁን ተጠሪ/ተሽከርካው ሟችን ጨምሮ ቤተሰባቸውን እንዲረዳ እንዲሁም ለ1ኛ ጣልቃገብም ሀብት እንዲሆን የተገዛ ተሽከርካሪ እንደሆነና ገንዘቡንም ከአረብ ሀገራት በመሰራት ካገኘሁት ገቢ የተገዛ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በበኩላቸው ይህን ክደው ተከራክረዋል፡፡..............