አቶ ሸምሱ አሊ እና ወ/ሮ ላይላ ኢታጎ የሰበር መዝገብ ቁጥር 216211

አቶ ሸምሱ አሊ እና ወ/ሮ ላይላ ኢታጎ የሰበር መዝገብ ቁጥር 216211

ጉዳዩ በግራቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ በፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ከፈረሰ በኋላ በአመልካች እና ተጠሪ መካከል የተነሳውን የንብረት ክርክር በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም የቀረበውን ይግባኝ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አይቶ በሥር ፍርድ ቤት ተጣሪቶ ውሳኔ ሊያገኝ ይገባዋል ያለው ጭብጥ በመያዝ ወደ ሥር ፍርድ ቤት ከመለሰ በኋላ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት በጉዳዩ ላይ በሰጠው ውሳኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የይግባኝ ቅሬታው የተዘጋጀ ቢሆንም ሲታመሙ የቆዩት  የአመልካች ጠበቃ ወላጅ እናት ሚያዝያ 20 ቀን 2013 ዓ/ም ሞተው ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ/ም የቀብር ሥርዓታቸው በመፈፀሙ ምክንያት በወቅቱ ይግባኝ ማቅረብ ስላልቻሉ ጊዜ ያለፈበትን ይግባኝ ማቅረብ እንዲችሉ እንድፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ……

ወ/ሮ ፍሬሕይወት ይልማ እና ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃ/የተ/የሕብረት ሥራ ማሕበር የሰ/መ/ቁ. 216200

ወ/ሮ ፍሬሕይወት ይልማ እና ፋና ቦሌ ሸማቾች ኃ/የተ/የሕብረት ሥራ ማሕበር የሰ/መ/ቁ. 216200

የክርክሩን አመጣጥ ከሥር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ከሳሽ፤ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካች ሕዳር 30 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ ክስ በተጠሪ ማሕበር በምግብና መጠጥ ቁጥጥር ዋና ክፍል ኃላፊነት የሥራ መደብ ተቀጥሬ ስሰራ ከሕግ ውጭ የሥራ ውሌን በማቋረጡ በሕብረት ሥራ ማሕበራት ሕግና በተጠሪ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በሽምግልና ዳኞች እንዲታይ ዳኛ ለማስመረጥና ለማስመደብ ክስ አቅርቤ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 94768 ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት ጉዳዩ በሽምግልና ዳኞች ሳይሆን በሥራ ክርክር ችሎት ነው የሚታይ በማለት ክሱን ውድቅ አድርጓል፡፡ ጉዳዩ በይግባኝ ሆነ በሰበር ችሎት ተቀባይነት ያላገኘ በመሆኑ የሥራ ክርክር ችሎት ክሴን ተቀብሎ ወደሥራ እንድመለስ እንዲወሰንልኝ፣ ተጠሪ ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆነ ካሣ፣ የሥራ ስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ክፍያ ለዘገየበት ቅጣት፣ የዓመት ዕረፍት ክፍያ፣ በ2006 ዓ/ም የሐምሌ ወር ደመወዝ፣ በ2006 ዓ/ም የቡና ገለባ ሽያጭ በሕብረት ሥምምነቱ መሠረት ሊከፈለኝ የሚገባ ብር 1,900.00 እንዲከፈለኝ፣ የሥራ ምስክር ወረቀት እንዲሰጠኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ አመልካች ባቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አመልካች የሥራ መሪ በመሆናቸው ክሱ በሥራ ክርክር ችሎት ሊታይ አይገባም፣ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ…..

ወ/ሮ ጽጌ ጅማ እና እነ አቶ ፀጋዬ ፈሲሳ የሰ.መ.ቁ.215435

ወ/ሮ ጽጌ ጅማ እና እነ አቶ ፀጋዬ ፈሲሳ የሰ.መ.ቁ.215435

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን ተጠሪዎች (የሥር አመልካቾች) በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ሟች አባታችን አቶ ፈሲሳ ሉቤ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 1 የቤት ቁ.161 ውስጥ እየኖሩ ባደረባቸዉ ሕመም ምክንያት በ13/10/1959 ዓ.ም ከዚህ ዓላም በሞት የተለዩ በመሆኑ፣ የሟች የውርስ ሀብት እንዲጣራልን በማለት ዳኝነት የጠየቁ ሲሆን፤ በፍ/ቤት የውርስ አጣሪዉ ተሹሞ የዉርስ ሀብቱ ተጣርቶ ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ የአሁን አመልካች (የሥር ጣልቃ ገብ) ለይግባኝ ሰሚዉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርባ ፍ/ቤቱም ባሳለፈዉ ዉሳኔ ጣልቃ ገብ ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በቅድሚያ በማከራከርና ወደ ፍሬ ነገር የሚያስገባም ከሆነ አከራካሪዉ ቤትና ይዞታ ሟችና ጣልቃ ገብ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ የጋራ ሀብት መሆን አለመሆኑ ግራ ቀኙን እንደገና እንዲያከራክርና የመሰለዉን ዉሳኔ እንዲሰጥበት ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መልሶለታል፡፡መልካም ንባብ…..

እነ ወ/ሮ አርሴማ ኤልያ እና …….የሰ.መ.ቁ.215383

እነ ወ/ሮ አርሴማ ኤልያ እና …….የሰ.መ.ቁ.215383

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ አመልካቾች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ 1ኛ አመልካች እና 2ኛ አመልካች ባልና ሚስት ሲሆኑ፣ 1ኛ አመልካች ከ2ኛ አመልካች የማትወለደውን ህጻን ልጃቸውን ህጋዊ ባለቤታቸው ለሆነው ለ2ኛ አመልካች በጉዲፈቻ ለመስጠት ያደረጉትን ስምምነት እንዲጸድቅላቸዉ ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…….

አቶ ኤልያስ ግደይ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰ/መ/ቁጥር 215268

አቶ ኤልያስ ግደይ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰ/መ/ቁጥር 215268

ጉዳዩ በአስተዳደር አካል የወጣ መመሪያ አግባብነት በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2013 መሠረት እንዲከለስ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡

ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበዉ አቤቱታ ተጠሪ ነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም ያወጣው የትምህርት አመራሮች ድልድል መመሪያ ህግን ባልተከተለ መልኩ ስለወጣ መመሪያው ተፈፃሚ እንዳይሆን እና እንዲከለስ የሚል ነዉ፡፡መልካም ንባብ………

135678910Last