አቶ ሾሻይ አበበ ከ ወ/ሮ አፀደ ገተንሳይ አቶ ሾሻይ አበበ ከ ወ/ሮ አፀደ ገተንሳይ ክርክሩ የጀመረው በትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ እኔና ባለቤቴ በትዳር በጋራ ያፈራነውና በአክሱም ከተማ ንግስተ ሳባ ቀበላ የሚገኘውን 175 ካ.ሜ ቦታ ሊይ ያረፈ ባታ ስምንት ክፍል ቤት እኔ ከሌሎች አምስት ሰዎች ጋር በነበረኝ የአፈፃፀም ክርክር በሀራጅ ሊሸጥ ሲል ከነልጆቼ ጎዳና ላይ እንዳልወጣ በሚል የአፈፃፀም ካሰሾቼ ከተወሰነላቸው ገንዘብ ውስጥ ብር 100,000.00 ሊተውልኝ፣
አቶ አማኑኤል ገ/ጊዮርግስ ከ የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤ ሕግ አቶ አማኑኤል ገ/ጊዮርግስ ከ የትግራይ ክልል ፍትሕ ቢሮ ዓቃቤ ሕግ የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 07 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ምዕራባዊ ዞን የሽሬ እንዳስሴ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ 22620 መጋቢት 05 ቀን 2011 ዓ.ም አመልካች በሌለበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ሊነሳ አይገባም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው፡፡
እነ አቶ ተረፈ በቀለ ከ ወ/ሮ ውድነሽ ዳዲ እነ አቶ ተረፈ በቀለ ከ ወ/ሮ ውድነሽ ዳዲ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ 153643 ሚያዚያ 26 ቀን 2010 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ክርክሩ የጀመረው ተጠሪ በአመልካቾች ላይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ነው፡፡
ወ/ሮ ፍሬህይወት ገበየሁ ከ አቶ ዘሪሁን ተፈራ ወ/ሮ ፍሬህይወት ገበየሁ ከ አቶ ዘሪሁን ተፈራ ጉዳዩ የውጪ ሀገር የተሰጠ ፍርድ የሚፈፀምበትን አግባብ የሚመለከት ነው፡፡አመልካች ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በቀን 19/07/2009 ዓ.ም ፅፈው ባቀረቡት የአፈፃፀም አቤቱታ የአሜሪካን የዲስትሪክት ፍ/ቤት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረውን የባልና ሚስት ፍቺና ንብረት ክፍክል ክርክር መርምሮ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በቀን 1/02/2013 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ መሠረት ተጠሪ እንዲፈፅሙ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡
አግሪኮም ኢንተርናሽናል ኩባንያ ከ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን አግሪኮም ኢንተርናሽናል ኩባንያ ከ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ጉዳዩ የስንዴ ግዢ ውልን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተደረገው ግራ ቀኙ እ.ኤ.አ ኖቨንበር 25/2011 ባደረጉት ስምምነት መሰረት አለመግባባታቸውን በኢትዮጵያ መሰረታዊ ህግ (Substantive Law) እንዲሁም በ Grain and Feeds Trading association (GAFTA) የሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 125 (GAFTA Rules NO. 125) መሰረት በሚቋቋም የግልግል ዳኝነት አካል በእንግሊዝ ሃገር ለመቋጨት በተስማሙት መሰረት ነው፡፡