እነ ወ/ሮ አያልነሽ ፈንቴ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ተካ የሰ-መ-ቁ182110 እነ ወ/ሮ አያልነሽ ፈንቴ እና ወ/ሮ ብርሃኔ ተካ የሰ-መ-ቁ182110 አመልካች ለዚህ ችሎት ሐምሌ 19 ቀን 2011 ዓ/ም ባቀረቡት አቤቱታ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 62378 መጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት ማስረጃ ሳይሰማ አመልካች የሟች ሚስት አይደሉም በማለት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍርድ ቤቱም በመዝገብ ቁጥር 194677 መጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ/ም በዋለው ችሎት ያቀረቡትን አቤቱታ በመሰረዙ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅሬታ አቅርበው ችሎቱም በመዝገብ ቁጥር 148513 የሰበር አቤቱታቸውን የሰረዘው ሆኖ እያለ እና የአሁን ተጠሪ በሰበር መዝገብ ቁጥር 152523 ባቀረቡት ቅሬታ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፊት የተሰጠን ውሳኔን ጠቅሶ ግራ ቀኙ የሟች ሚስቶች አይደሉም በማለት የሰጠውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ በመሻር በማስረጃ ተጣሪቶ እንዲወሰን ወደ ሥር ፍርድ ቤት መልሶት እያለ ፤ ይህ ውሳኔ ለአመልካችም ተፈፃሚነት ሊኖረው ሲገባ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ስላላቀረብሽ ውሳኔውን እንደተቀበልሽ ይቆጠራል በማለት ከክርክሩ እንዲወጡ በማድረግ ተጠሪ ብቻ ሚስትነታቸውን እንዲያረጋግጡ መደረጉ የእኩልነት መርህን የሚጥስ ነው በማለት ብይኑ ተሽሮ ሚስት መሆናቸውን በማስረጃ ማረጋገጥ እንዲችሉ እንዲወሰንላቸው ጠይቋል።………….
አቶ ደጋረገ ሙሉ እና ወ-ሮ ውብናት ላቀ የሰ-መ-ቁ 181649 አቶ ደጋረገ ሙሉ እና ወ-ሮ ውብናት ላቀ የሰ-መ-ቁ 181649 ይህ የባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር የተጀመረዉ በአማራ ክልል በሜጫ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተጠሪ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር አመልካች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.74190 ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የአሁን ተጠሪ በሥር በወረዳዉ ፍ/ቤት ባቀረበችዉ ክስ ከአሁን አመልካች ጋር ያለን ጋብቻ እንዲፈርስ፣ በጋራ የፈረናቸዉ ንብረቶች እንዲንካፈል በማለት ዘርዝራ በማቅረብ እንዲወሰንላት ዳኝነት ጠይቃለች።የአሁን አመልካች በዚህ ክስ ባቀረቡት መልስ ተጠሪዋ ባቀረበችዉ የንብረት ጥያቄ ላይ ተገቢ ነዉ ያለዉን ክርክር ያቀረበ ሲሆን፤ በራሱ በኩል ባቀረበዉ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ከተጠሪ ጋር ሊንካፈል ይገባል የሚላቸዉን ንብረቶች በመዘርዘር በመጠየቅ፤ የሰራተኛ እዳ አራት ኩንታል በቆሎ አንድ ኩንታል ዳጉሳ፣ አንድ ኩንታል ጓያ አለብን ልንከፍል ይገባል በማለት ጠይቋል። የአሁን ተጠሪ በዚህ በተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ላይ መልስ ያቀረበች ሲሆን፣ የሰራተኛ የጋራ እዳ አለብን በማለት የቀረበዉም ሐሰት ነዉ፣ ይህ ተቀጠረ የተባለዉ ልጅ የአሁን አመልካች የግል ልጅ ነዉ የእኔም ሶስት ልጆች የግል ነበረኝ የግል ከብቶች ነበራቸዉ እነዚህ ልጆች አብራዉ ከእኛ ጋር ያደጉ ሲሆን ለሰሩበት ልንከፍላቸዉ አልተስማማንም አልቀጠርናቸዉም፣የአሁን አመልካች ልጅ እንደልጅ ከቤት ነበረ እንጂ የተቀጠረ አይደለም።ከዚህ በኋላ የወረዳዉ ፍ/ቤት የሰዉ ምስክሮች በመስማት በሰጠዉ ዉሳኔ የአሁን አመልካች በተከሳሽ ከሳሽነት የጋራ ዕዳ በማለት ያቀረበዉ የሰራተኛ እዳ 6 [ስድስት] ማዳበሪያ እህል በጋራ ሊከፍሉ ይገባል፤ የባልና ሚስት ንብረቶች ላይ ተገቢ ነዉ ያለዉን ዉሳኔ ሰጥቷል። የአሁን ተጠሪ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበችዉ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የባልና ሚሰት ንብረት በተመለከተ በተወሰኑ ንብረቶች ላይ የሥር ፍ/ቤት ጉዳዩን ድጋሚ አጣርቶ እንዲወስን የመለሰ ሲሆን፣ የሰራተኛ ዕዳ የተባለዉን የሥር ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል።............
እነ አቶ ጁሀር ያህያ እና ወ/ሮ መሬም አህመድ የሰ.መ.ቁ 179607 እነ አቶ ጁሀር ያህያ እና ወ/ሮ መሬም አህመድ የሰ.መ.ቁ 179607 ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ.መ.ቁ 03-76478 በ15/8/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በ16/12/11ዓ.ም በተጻፈ የተሻሻለ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ የአሁን 1ኛ ተጠሪ በስር የአብክመ ጎንደር ዞን አስተዳደር የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በአሁን 2ኛ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በ1960ዓ.ም ተጋብተን 4 ልጆች ወልደን ንብረት አፍርተን ስንኖር ባለመግባባታችን ጋብቻው ሳይፈርስ ተለያይተን ኖረናል፡፡ ስለሆነም አሁን ጋብቻው ፈርሶ 2ኛ ተጠሪ ሌላም ሚስት ስላለው የዘረዘርኩትን ንብረት ለሶስት እንድንካፈል በማለት ዳኝነት ጠይቀው 2ኛ ተጠሪም ባቀረቡት መልስ 1ኛ ተጠሪ ልጅ ወልዳልኛለች እንጂ ጋብቻ የለንም በማለት ተከራክረው ፍ/ቤቱም ጋብቻ አለ የለም? የሚለውን በምስክር እና በሰነድ በማረጋገጥ ጋብቻ እንዳለ በማረጋገጥ ብይን ሰጥቶ 1ኛ ተጠሪ የዘረዘሩትን ንብረቶች ባልና ሚስት የሆኑት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪዎች እንዲሁም በስር 1ኛ ጣልቃገቦች የነበሩት የአሁን አመልካቾች እንዲካፈሉ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ጉዳዩ በይግባኝ ወደ ክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሄዶ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ በ1ኛ እና 2ኛ ተጠሪ መካከል ጋብቻ ያለ መሆኑን አረጋግጦ የአሁን 3ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብተው ባለመከራከራቸው የተነሳ የስር የወረዳ ፍ/ቤቱን ውሳኔ በመሻር የአሁን 3ኛ ተጠሪ ጣልቃገብተው እንዲከራከሩ ውሳኔ በመስጠት ጉዳዩን ለስር የወረዳው ፍ/ቤት በመለሰው መሰረት 3ኛ ተጠሪ በስር የወረዳው ፍ/ቤት 2ኛ ጣልቃገብ ሆነው ባቀረቡት የጽሁፍ ክርክር የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው በፍሬጉዳዩ ላይ ባቀረቡት መልስ 1ኛ ተጠሪ ዘርዝራ ያቀረበችው ንብረት እንዲፈራ ያደረገችው አስተዋጽኦ የለም፤ በ2ኛ ተጠሪ እና በ3ኛ ተጠሪ ጥረት የተፈሩ ንብረቶች ናቸው፤ በ1ኛ ተጠሪ ክስ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው እና አሁን አመልካቾች በዚህ ፍ/ቤት ላቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው አከራካሪው በመሀል አራዳ የሚገኘው ባለሁለት ፎቅ ቤት ከአሁን አመልካቾች ልጆቻችን(በስር ከ1ኛ ጣልቃገቦች) ጋር በሽርክና ስራ ከመጀመራችን በፊት በንጉሱ ዘመን ከቀበሌ የተቀበልነው እኔ እና 2ኛ ተጠሪ ስንሆን እስከ 1983ዓ.ም በመኖሪያ ቤት የምንጠቀምበት 2ኛ ተጠሪ እና እኔ ባለቤቱ 3ኛ ተጠሪ ስንሆን 2ኛ ተጠሪ በእርጅና ምክንያት ስራ ሲያቆም ለገቢ ምንጭ እንዲሆነን ከጋራ ልጆቻችን ጋር የሽርክና ውል ወስደንበታል፡፡ ፎቁም የተሰራው በልጆቻችን ጥረት በመሆኑ የልጆቻችን የ60% ድርሻ መኖሩን ስለማውቅ በነሱ በኩል የቀረበውን የጣልቃገብነት አቤቱታ አልቃወምም፤ ነገር ግን ፍ/ቤቱ በ2ኛ ተጠሪ እና በአሁን አመልካቾች(በስር 1ኛ ጣልቃገቦች) መካከል የተደረገው የሽርክና ውል ፈራሽ ነው የሚልበት ምክንያት ካለው ክፍፍልን በተመለከተ የቤቱ እና ቦታው ግማሽ ሀብት የ3ኛ ተጠሪ በመሆኑ ግማሽ ባለሀብት ናት ይባልልኝ በማለት ጠይቀዋል፡፡.........
እነ ወ-ሮ ሰሚራ ጀማል እና አቶ ናስር ሐጎስ የሠ-መ-ቁጥር 188406 እነ ወ-ሮ ሰሚራ ጀማል እና አቶ ናስር ሐጎስ የሠ-መ-ቁጥር 188406 ጉዳዩ ዳኝነት ሳይከፈል መዝገብ በነጻ ስለማስከፈት የሚመለከት ሆኖ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች አቤቱታዉን በማቅረብ የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡አመልካች በተጠሪ ላይ ባቀረቡት አቤቱታ እየተከራከሩበት ካለው ንብረት ውጭ ሌላ እንደሌላቸውና በጋብቻ ወቅት የተፈራው ንብረትም በፍርድ ስለታገደ መጠቀም እንደማይችሉ በመግለፅ በተጠሪ ላይ ለሚመሰርቱት የ32‚750‚000.00 ብር ክስ ለዳኝኘት የሚከፍሉት ገንዘብ እንደሌላቸዉ በመግለጽ መዝገቡ በነጻ እንዲከፈትላቸው የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ በሰጡት መልስ አመልካች በጋብቻ ላይ እያሉ የሰሩት በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቤት ቁጥር 297 የሆነ መኖሪያ ቤት ፣ በመቐለ ከተማ መኖሪያ ቤት እንዲሁም በፒስ ደልውን ቴክኖሎጂ ሲስተም ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ውስጥ አክሲዮን ያላቸው ስለሆነ ድሃ ስላልሆኑ የዳኝነት ገንዘብ ሳይከፍሉ መዝገብ ሊከፈትላቸዉ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡…….
እነ ወ-ሮ የሺወርቅ ፈንታዉ እና ወ-ሮ ፀሀይነሽ ፈንታዉ የሠ-መ-ቁጥር 190450 እነ ወ-ሮ የሺወርቅ ፈንታዉ እና ወ-ሮ ፀሀይነሽ ፈንታዉ የሠ-መ-ቁጥር 190450 ጉዳዩ የፍርድ አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን ከክርክሩ እንደተረዳነዉ ጉዳዩ የተጀመረዉ በአማራ ክልል ሀብሩ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ፍርድ ቤቱ በመ/ቁጥር 0101191 ላይ በቀን 13/07/2011ዓ/ም በተሰጠ ዉሳኔ ላይ ክስ የቀረበበትን ቤትና ቦታ በአይነት እንዲካፈሉ ያልተጨረሰ ግንባታ ካለ ከተካፈሉ በኋላ የየድርሻቸዉን ግንባታ እንዲጨርሱና ቤት ያልተሰራበትን ትርፍ ቦታ ግራ ቀኝ እኩል እንዲካፈሉ በሰጠዉ ዉሳኔ መሰረት እንዲፈጸምላቸዉ የአሁን ተጠሪ የፍርድ አፈጻጸም መዝገብ አስከፍተዉ ፍርድ ቤቱም በመ/ቁጥር 0101101 ላይ ግራ ቀኝ እኩል እንዲካፈሉ ዉሳኔ የተሰጠበት ቤትና ቦታ ለሁለት ተካፍሎ በየግላቸዉ ካርታና ፕላን ለማሰራት የሚቻል ከሆነ በየግላቸዉ ካርታና ፕላን እንዲሰራላቸዉ ይህ የማይቻል ከሆነም እነ በሚል ካርታና ፕላን ሰርቶላቸዉ ዉጤቱን እንዲያሳዉቅ በሚል በቀን 03/10/2011 ዓ/ም ቤቱ ለሚገኝበት ለዉርጌሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ትእዛዝ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡……..