እነ አቶ አንበሳው አፈወርቅ እና አቶ አበበ ተገኝ የሠ-መ-ቁጥር 185708

እነ አቶ አንበሳው አፈወርቅ እና አቶ አበበ ተገኝ የሠ-መ-ቁጥር 185708

ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በመጀመሪያ በታየበት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የቤት ቁጥሩ አዲስ የሆነውን በ360 ካሬ ሜትር የሰፈረ ቤት በብር 650,000.00 ከተጠሪ ገዝቻለሁ፡፡ በውሉ ላይ ተጠሪ ቤቱን እንዳስረከቡ የተገለጸ ቢሆንም ቤቱን በምረከብበት ወቅት እናቴ ከዚህ አለም በሞት የተለየች በመሆኑ ችግር ስለገጠመኝ ሳልረከብ የቀረሁ ስለሆነ ሀዘኔን ጨርሼ ተጠሪ ቤቱን እንዲያስረክቡኝ ብጠይቅም ቤቱን ሊያስረክቡኝ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ቤቱን እንዲያስረክቡኝ እና በዉሉ የተመለከተዉን መቀጫ ብር 100,000.00 እንዲከፍለኙ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በማስቀደም ፍሬ ነገሩን በተመለከተ በሰጡት መልስ አመልካች ከተጠሪ ጋር ፈጸምኩኝ ያሉትን ወል አልፈጸምኩም፡፡ምንም ገንዘብ አልተቀበልኩም፡፡አመልካች ፈጸምኩኝ ያሉት ዉል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 መሰረት ያልተፈጸመና ሕጋዊ መሰረት የሌለዉና በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1720/1 መሰረት ረቂቅ ነዉ፡፡ ከአመልካች ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት ስለነበረኝ ጉዳይ እንዲያስፈጽሙልኝ የዉክልና ሥልጣና በርካታ ሕጋዊ ሰነዶችን ሰጥቻቸዉ በእጃቸዉ የሚገኝ ቢሆንም አመልካች ዉል አለኝ የሚሉት ዉል ሳይኖርና የተቀበልኩት ገንዘብ ሳይኖር በሀሰት የቀረበ ስለሆነ ክሱ ዉድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡……..

በአማጋ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጮራ የጋዝና ኬሚካል ውጤቶች ፋብሪካ፣ሂክማ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ኃ/የተ/የቡድን ኢንተርፐራይዝ እና ሌሎች የሰ-መ-ቁ 175155

በአማጋ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጮራ የጋዝና ኬሚካል ውጤቶች ፋብሪካ፣ሂክማ የፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ኃ/የተ/የቡድን ኢንተርፐራይዝ እና ሌሎች የሰ-መ-ቁ 175155

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ139054 በ29/5/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ፤ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 172510 በ26/7/11ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት በ7/8/11ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረበ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/ከ/ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ ባቀረበው የተሻሻለ ክስ ለከሳሽ በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/98 መሰረት ለሁለት አይነት የበረኪና ምርቶች ማለትም ለትልቁ ባለ 800 ሚሊ ሊትር SEDEX እንዲሁም ለትንሹ ባለ 300 ሚሊ ሊትር SEDEX በምዝገባ ቁ.LTM/0189/2005 እና LTOW 0186/2005 በቅደም ተከተል የተመዘገበ እና እስከ 28/10/12ዓ.ም ድረስ ጸንቶ የሚቆይ የንግድ ምልክት ምዝገባ ሰርተፍኬት ከኢትዮጵያ አእምሮአዊ ንብረት ጽ/ቤት በ2005ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን የንግድ ምልክቶቹ የተመዘገቡት እና ፈቃድ የተሰጠው በቃል እና በስእል(በቅርጽ) (በምስል) ከመሆኑም ባሻገር የቀለም አይነቱ በአዋጁ አንቀጽ 5(2) መሰረት ጥቁር እና ነጭ ነው፡፡ የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ አላማው የተለያዩ እቃዎችን በማምረትና በማከፋፈል ወይም አገልግሎት በመስጠት የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መልካም ስም እና ዝና ለመጠበቅ እንዲሁም በተመሳሳይ ስራዎች እና አገልግለቶች መካከል ማሳከርን ለማስወገድ እና አንድን ምርት/እቃ ወይም አገልግሎት በቀላሉ ለመለየትና የንግድ ምልክቱ በአገልግሎት ተጠቃሚው (ኮንሲዩመሩ) ላይ ግርታ እንዳይፈጥር ለማድረግ ነው፡፡…………

እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807

እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807

ጉዳዩ የእግድ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሠሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የሥር ከሳሽ፣ 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ 2ኛ ተጠሪ ቤት እንዲገዛልኝ ገንዘብ ልኬለት የንብረቱን ሥመ-ሀብት በስሙ ስላደረገ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥሩ TH-14-B-4 የሆነ ቤት ያስረክበኝ ወይም ግምቱን ይክፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር እየተከራከሩ ባለበት ሁኔታ ክርክር ያስነሳው ንብረት ላይ ፍርድ ቤቱ  እግድ ሠጠ፡፡ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ በመግባት ንብረቱን ከ2ኛ ተጠሪ በውል ስለገዛሁ ሊከራከሩበት አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ በክርክሩ መካከል አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ሠኔ 29 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረጉት የእርቅ ሥምምነት የገንዘብ ዕዳውን 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች ሊከፍሉና ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ ንብረቱ ላይ የተሠጠው እግድ ሳይነሳ እንዲቆይ የተስማሙ ሲሆን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 190764 ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የእርቅ ሥምምነቱን ተቀብሎ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 277 መሠረት አጽድቋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ ቁጥር 191057 ክርክር ያስነሳውን ንብረት 1ኛ ተጠሪ ስለገዙት 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲያስረክቡ ሕዳር 20 ቀን 2011 ዓ/ም የተሠጠውን ፍርድ በማያያዝ ንብረቱን በፍርድ ስላገኘሁት በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ ክርክር ምክንያት የተሠጠው እግድ እንዲነሳ በማለት አመልክተዋል፡፡ አመልካች ለእግድ ይነሳልኝ ማመልከቻው ያቀረቡት መልስ በእርቅ ስምምነቱ የተመለከተውን ገንዘብ 2ኛ ተጠሪ እስኪከፍሉ ድረስ እግዱ ጸንቶ እንዲቆይ ተስማምተን እርቁ በፍርድ ቤት የጸደቀና ይህንንም 1ኛ ተጠሪ እያወቁ ያልተቃወሙና በይግባኝ ያላስለወጡ በመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡…………

First282930313233343537