አቶ ተስፋዬ ኪዳኔ እና አቶ ወርቁ ዋበሎ የሰ/መ/ቁጥር 198071

አቶ ተስፋዬ ኪዳኔ እና አቶ ወርቁ ዋበሎ የሰ/መ/ቁጥር 198071

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከተማ ቦታን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች አከራካሪውን ይዞታ በመልቀቅ ለተጠሪ ሊያስረክብ ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አመልካች ስላመለከቱ ነው፡፡አመልካች በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡

ተጠሪ የካቲት 19 ቀን 2011 ዓ.ም ጽፈው በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስም አዋሳኙ በክሱ ውስጥ የተጠቀሰውን በቢቾ ቀበሌ የሚገኘውን ይዞታ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በስጦታ አግኝቼ ቆርቆሮ ቤት ሰርቼ የምጠቀምበትን በ2008 ዓም በተደረገው ህገ ወጥ ይዞታን ስርአት የማስያዝ አሰራር ይዤ ካለሁበት 6 ሜትር መንገድ በመውሰዱ ወደ አመልካች ይዞታ ውስጥ ሲያስገባኝ አመልካችም ከኋላ ለኔ ለቅቆ ወደፊት እንዲሸጋሸግ ሲደረግ ለኔ በተሰጠኝ ይዞታ ላይ ቤት ገንብቶ ለመልቀቅ ፈቃደኛ ስላልሆነ በራሱ ወጪ አፍርሶ እንዲለቅልኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡………….

አቶ ዮሀንስ ክፍሉ እና አቶ ሀሰን መሀመድ የሰ/መ/ቁጥር 197942

አቶ ዮሀንስ ክፍሉ እና አቶ ሀሰን መሀመድ የሰ/መ/ቁጥር 197942

ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ ተጠሪ ለአመልካች ለቅቆ ሊያስረክብ የሚገባው በተጠየቀው ዳኝነት አግባብ በምስራቅ አቅጣጫ 1 ሜትር × 14 ሜትር ሊሆን ይገባል በማለት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ መነሻ ያደረገ ሲሆን ተጠሪ በጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩ ሲሆን አመልካች ተከሳሽ ነበሩ፡፡ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስም አዋሳኙ በክሱ ላይ የተመለከተውን በጅማ ከተማ ቦሳ ኪቶ ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ 140 ካሜ መንግስት በሰጠኝ ቦታ ሰርቪስ ቤት ሰርቼበትና የይዞታ ማረጋገጫ አውጥቼበት የምጠቀምበትን በምስራቅ አቅጣጫ በኩል ወደ ይዞታዬ ርዝመቱ 1 ሜትር ቁመቱ 14 ሜትር በመግባት ግንባታ አከናውኖበት የያዘ ስለሆነ ግንባታውን አንስቶ ይዞታዬን እንዲለቅልኝ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡………….

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ እና መልካሙ ዳታ ደሴ የሰ.መ.ቁ 197432

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ እና መልካሙ ዳታ ደሴ የሰ.መ.ቁ 197432

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 192545 ሐምሌ 27 በቀን 2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው……………..

አቶ ኃይለጊዮርጊስ ይልማ እና አቶ አዲስ እሸቱ የሰ/መ/ቁጥር 197009

አቶ ኃይለጊዮርጊስ ይልማ እና አቶ አዲስ እሸቱ የሰ/መ/ቁጥር 197009

ይህ የሰበር አቤቱታ ሊቀርብ የቻለው አመልካች እና በስር ፍርድ ቤት ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተመለከቱት ተከሳሾች አከራካሪውን ቤት ለተጠሪ ሊያስረክቡ ይገባል በማለት የስር የጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አመልካች ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ መነሻ በማድረግ ሲሆን ተጠሪ በጣርማ በር ወረዳ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩ ሲሆን አመልካች 1ኛተከሳሽ ነበሩ፡፡

ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአመልካች እና በስር ፍርድ ቤት ከ1ኛ እስከ 3ኛ በተመለከቱት ተከሳሾች ላይ ባቀረቡት ክስም አዋሳኙ በክሱ ላይ የተመለከተውን 400 ካሜ ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤት ከነሰርቪሱ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓም በተደረገ የሽያጭ ውል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ከተመለከቱት ተከሳሾች በብር 200,000.00 ገዝቼ ካርታ በስሜ የተሰጠኝ ቢሆንም ቤቱን ከአመልካች ነፃ በማድረግ ያላስረከቡኝ በመሆኑ ፤አመልካችም በአደራ ይዤ የምጠቀመው ነው በማለት ምንም መብት ሳይኖረው ለማስረከብ ፍቃደኛ ስላልሆነ ከ1ኛ እስከ 3ኛ የተመለከቱት ተከሳሾች ቤትና ይዞታውን ከ3ኛ ወገን ነፃ አድርገው እንዲያስረክቡኝ አመልካችም የፈጠረውን ሁከት አቁሞ ቤትና ቦታውን እንዲያስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት አመልክተዋል፡፡……..

አቶ ሀብታሙ ዝናቡ እና አቶ ታሪኩ አየለ የሰ/መ/ቁ 196871

አቶ ሀብታሙ ዝናቡ እና አቶ ታሪኩ አየለ የሰ/መ/ቁ 196871

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ የከተማ ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/333779 ላይ ጥቅምት 03/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔን በማፅናት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው በማለት ለማስለወጥ ነው፡፡

ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ ሐምሌ 05/2011 ዓ.ም ፅፈው በአሁን አመልካች ላይ በጅማ ወረዳ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ነው፡፡ ፍሬ ቃሉም ቦታ እና አዋሳኙ በክሱ ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሰውን 200 ካሬ ሜትር የከተማ ይዞታ ነሐሴ 06/2011 ዓ.ም ተሰጥቷቸው አስፈላጊውን ክፍያ ፈፅመው እና የግንባታ ፈቃድ አውጥተው በቦታው ላይ ግንባታ ለማከናወን ሲሄዱ ባላወቁት መንገድ የአሁን አመልካች ትንሽ ሰርቪስ ቤት ሰርተዉበት የያዙባቸው መሆኑን በመግለፅ በፍርድ ኃይል ተገደው በቦታው ላይ የሰሩትን ቤት አፍርሰው እንዲለቁላቸው ዳኝነት የሚጠይቅ ነው፡፡……………

124678910Last