እነ አቶ ሁሴን አሊ እንድሪስ እና ወ/ሮ ዘሀራ ዱሌቦ የሰበር መዝገብ ቁጥር 214803 እነ አቶ ሁሴን አሊ እንድሪስ እና ወ/ሮ ዘሀራ ዱሌቦ የሰበር መዝገብ ቁጥር 214803 ጉዳዩ ተጠሪ የሟቹ ሚስት መሆናቸውን እንዲሁም በሰበር ክርክሩ የሌሉት ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ የሟቹ ልጆች ስለሆኑ የሟች ሐጂ አሊ እንድሪስ ሙሳ ውርስ እንዲጣራ ውርስ አጣሪ እንዲሾምላቸው 1ኛ አመልካችን ተጠሪ በማድረግ አቤቱታ አቅርበው 1ኛ አመልካችም ውርሱ ቢጣራ እንዳማይቃወሙ መልስ የሰጡ ሲሆን ፤ ቀሪዎቹ አመልካቾችም የሟቹ ልጆች መሆናቸውን በመግለጽ ጣልቃ ገብተው የውርስ ማጣራት ክርክሩ ተካፋይ ለመሆን ጠይቀው ፍርድ ቤቱም ውርሱ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ ውርሱ ተጣርቶ ሪፖርቱ ቀርቧል፡፡ አመልካቾች በሟቹ ስም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ቁጥሩ 1588 የሆነው ቤት እና በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ቁጥሩ 1577 የሆነው ጋራዥ ቤት ተሸጦ የተገኘው ገንዘብ ሟች አባታቸው ሐጂ አሊ እንድሪስ ከሟቿ እናታቸው ወ/ሮ ዘውድነሽ ጋር በጋራ ያፈሩት ነው በማለት አስተያየታቸውን ስያቀርቡ ተጠሪ ሟች ንብረቱን ያፈሩት ከእሳቸው ጋር መሆኑንና ከሟቹ ጋር በጋብቻ ውስጥ እያሉ በቤት ቁጥር 1588 ላይ ከሁለት ሚልዮን ብር በላይ በማውጣታቸውንና ጋራዥ ቤት ተሸጦ በ1ኛ አመልካች እጅ የሚገኘው የሽያጭ ገንዘብ ግማሹ እንዲሰጣቸው ተከራክረዋል፡፡መልካም ንባብ……..
ወ/ሮ ለምለም ቅጣው እና ወ/ሮ ዘቢባ የሱፍ የሰ/መ/ቁ 214325 ወ/ሮ ለምለም ቅጣው እና ወ/ሮ ዘቢባ የሱፍ የሰ/መ/ቁ 214325 ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው የአሁን ተጠሪ በቀን 09/06/2012 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ ሟች አባቴ የሱፍ ኢብራሂም በቀን 05/05/1987 ዓ.ም በሞት ተለይቷል፡፡ የአባቴን ወራሽነት በደዋ ጨፋ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 0302372 አረጋግጫለሁ፡፡ አባቴ በህይወት ሲኖር ተከሳሽን አግብቶ 6 ልጅ ያላቸው ሲሆን እኔ ደግሞ ከበፊት ሚስቱ ወ/ሮ ሀሊማ ኡስማን የወለደኝ ስሆን አባቴ በህይወት እያለ በከሚሴ ከተማ ውስጥ 528 ካ.ሜ በሆነ ቦታ ላይ የሚገኝ 1 ትልቅ ቆርቆሮ ቤት በውስጡ 2 ክፍል ያለው፣1 ትልቅ ቆርቆሮ ቤት 6 ክፍል ያለው እንዲሁም 6 ክፍል ሰርቪስ ቤት ያለው ሁሉንም በጋራ አፍርተዋል፡፡ አባቴ ሲሞት ህጻን ስለነበርኩ ካደኩኝ በኋላ በተከሳሽ ስር እንደ ወላጅ እናት በማየት በፍርሀትና በማክበር ክስ ሳላቀርብ ቆይቼ ንብረት እንድታካፍለኝ በሽማግሌ ብጠይቅም ለማካፈል እንቢ ስላለች የውርስ ንብረት ድርሻዬን እንድታካፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ………
እነ መ/ር ገመቹ ቹዋታ እና የየጋምቤላ ብ/ክ/መ/ ጠ/ዓ/ህግ ሰ/መ/ቁጥር 214184 እነ መ/ር ገመቹ ቹዋታ እና የየጋምቤላ ብ/ክ/መ/ ጠ/ዓ/ህግ ሰ/መ/ቁጥር 214184 ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በቀን ታህሳስ 15/2013 ዓ.ም በጻፈው የወንጀል ክስ በአሁን አመልካቾች እና በሌሎች 6ኛ፤7ኛ እና 8ኛ የስር ተከሳሽች ላይ በጋምቤላ ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ የመጀመሪያ ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ድ.ሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/፣37/1/ሀ እና 539/1/ን በመተላለፍ አመልካቾች በክሱ በተገለፀው ልዩ ቦታ፣ቀንና ሰዓት 1ኛና 2ኛ አመልካቾች ከስር ተከሳሾችና ከሌሎች አመልካቾች ጋር በመገናኘት 2ኛ አመልካች ለግል ተበዳይ ተማሪ ቤር አጆክ ስልክ በመደወል ቴድባሌ ወደሚባል ሰፈር በመውሰድ አንገቷን ቆርጠው ህይወቷ ካለፈ በኋላ ሞተር ሳይክል እንዲመጣ ለ3ኛ አመልካች ደውለው ሬሳውን በሞተር ሳይክል ጫካ ውስጥ የጣሉ መሆኑንና አባሪ ተባባሪ በመሆን የግድያ ወንጀል የፈጸሙ መሆኑን በመጥቀስ የከሰሰ ሲሆን፣ ሁለተኛው ክስ በ2ኛ፣ 3ኛ 4ኛና 5ኛ አመልካቾች ላይ የቀረበ ሲሆን በ1996 ዓ.ም በወጣውን የኢፌድሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ እና አንቀጽ 841/1//1 ን በመተላለፍ ከላይ በተገለፀው ልዩ ቦታ፣ቀንና ሰዓት በፈጸሙት ሬሳ የማንገላታት ወንጀል ክስ ተከሰዋል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ………
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አቶ ተከስተ ካሴ የሰ/መ/ቁ. 212603 የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አቶ ተከስተ ካሴ የሰ/መ/ቁ. 212603 ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተጠሪ ባቀረቡት ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ እ.አ.አ. ከቀን 22/04/2020 ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር 42,863.37 እየተከፈለኝ በአውሮፕላን ጥገና አሰልጣኝነት ሳገለግል ቆይቻለሁ፡፡ ከመስከረም 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በድርጅቱ ውስጥ በተቋቋመው የሰራተኛ ማህበር ውስጥ ምክትል ፀኃፊ በመሆን እያለገልኩ ቆይቻለሁ፡፡ ይሁን እንጂ አመልካች ስለእኔ እውነት ያልሆነ መረጃ በማስተላለፍ ስም እና ዝናዬን አጥፍተሃል፣ ከሌሎች ሰራተኞች ጋር በስራ ቦታ መተባበር እና ሰላማዊ የስራ ግንኙነት እንዳይኖር አድርገሃል በማለት የስራ ውሌን አቋርጦታል፡፡ ከስራ ስሰናበት በህብረት ስምምነቱ መሠረት በተቋቋመው ኮሚቴው ውስጥ የሰራተኛ ማህበር ተወካይ አልነበረም፡፡ ስለሆነም ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ ያልተከፈለኝ ደሞዝ ተከፍሎኝ ወደ ስራዬ እንድመለስ ይወሰንልኝ፤ ወደ ስራ ልመለስ የማልችልበት አግባብ ካለ ደግሞ የስራ ስንብት ክፍያ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የሚያዝያ ወር ሙሉ ደሞዝ፣ እ.አ.አ. የ2020 ዓ.ም የዓመት እረፍት ክፍያ እንዲከፍለኝ እና የስራ ልምድ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡መልካም ንባብ……..
የደቡብ ክልል ዐ/ሕግ እና እነ በረከት በየነ የሰ/መ/ቁጥር 211689 የደቡብ ክልል ዐ/ሕግ እና እነ በረከት በየነ የሰ/መ/ቁጥር 211689 ጉዳዩ የሰው መግደል ወንጀል የሚመለከት ክስን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነበር፡፡ የአሁን አመልካች ጳጉሜ 4ቀን 2011ዓ/ም በተፃፈ ክሱ 1ኛ ተጠሪን 3ኛ ተከሣሽ 2ኛ ተጠሪን ደግሞ 5ኛ ተከሣሽ በማድረግ ተጠሪዎች ከሌሎች ተከሣሾች ጋር ሆነው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ) እና 540 የሚደነግገውን ተላልፈው የካቲት 24ቀን 2011ዓ/ም ከምሽቱ በ2ሰዓት አረካ ከተማ ቀበሌ 04 ትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሟች አዲሱ በለጠን 4ኛ ተከሣሽ ስሙን ጠርቶ እንዲቆም አድርጎ ለስላምታ የሟችን እጅ ጨብጦ እንደያዘው፤ 1ኛ ከሣሽ ከኋላ በኩል በፌሮ ብረት የኋላ ጭንቅላቱን 2 ጊዜ ሲመታው፤ 2ኛ ተከሣሽ በጌጠኛ ድንጋይ (ኮብል ስቶን) የግራ ጭንቅላቱን 3ኛ ተከሣሽ(1ኛ ተጠሪ ) የሟችን ጀርባ በክራንች ሁለት ጊዜ፤ 5ኛ ተከሣሽ(ሁለተኛ ተጠሪ) ሟቹ እንደወደቀ ጉረሮውን እና ሆዱን ከረገጠው በኋላ ሮጠው ማምለጣቸውን ሟች በድብደባው ስለደከመ በዱቦ ሆስፒታል ሲታከም ቆይቶ መጋቢት 5ቀን 2011ዓ/ም መሞቱን በመዘርዘር የሰው መግደል ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል፡፡መልካም ንባብ………….