Login
  • Register
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • Message from the President
    • History and Traditions
    • Vision Mission and Mandate
    • President
      • Current President
      • Former Presidents
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • Judges
      • Current
      • Former Judges
    • Judicial Administration Council
    • Court Administration & Directorates
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • E-Filing
    • Quick Start Guide
      • Registration
      • E-Filing
    • User Guide
    • Rules and Guidelines
    • Forms
    • Tutorials
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
አቶ በፍቃዱ ጌታቸው እና እነ አቶ ዮናስ ጌታነህ የሰ/መ/ቁ196346

አቶ በፍቃዱ ጌታቸው እና እነ አቶ ዮናስ ጌታነህ የሰ/መ/ቁ196346

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 182644 ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው፡፡ ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ ያከራከረን ቤት በእናቴ ስም የተመዘገበ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ጣልቃ ገብዎች ቤቶቹን ሰራን የሚሉት 1ኛ ጣ/ገብ አያቴ ሞግዚቴ ሆኖ ባለበት ጊዜ መሆኑ እየታወቀ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያላደረኩትን እርቅ መሰረት አደርጎ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡……..   

አቶ ከተማ ኑኔ እና ወ/ሮ መረጠች ለማ የሰበር መ/ቁጥር 191095

አቶ ከተማ ኑኔ እና ወ/ሮ መረጠች ለማ የሰበር መ/ቁጥር 191095

 

በዚህ መዝገብ ላይ የቀረበው ጉዳይ በሊዝ ውል የተገኘ ይዞታ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እና ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ/ቁ/14021 ላይ ታህሳስ 17/2012 ዓም በዋለው ችሎት የስር ፍቤቶችን ውሳኔ የሻረበትን የመጨረሻ ውሳኔ በመቃወም ነው፡፡

የክርክሩ ስረ ነገር አመጣጥ እንዲህ ነው፡፡ አቶ ባላይ ላጲሶ የተባሉት የአሁን ተጠሪ የቀድሞ ባለቤት ከተጠሪ ጋር የነበራቸውን ጋብቻ በፍቺ መፍረሱ ተከትሎ ቦታ እና አዋሳኙ በክስ አቤቱታው ውስጥ የተዘረዘረውን እና ጋብቻቸው ፀንቶ በነበረበት ወቅት በሊዝ ውል ያገኙትን 4000 ካሬ ሜትር ይዞታ ለመካፈል በሆሳና ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ የአሁን ተጠሪም ቀርበው ንብረቱ የጋራ በመሆኑ ቢካፈሉ አልቃወምም የሚል መልስ በመስጠታቸው የተጠቀሰው ይዞታ የጋራ ንብረት መሆኑ ተጠቅሶ እንዲካፈሉ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ የአሁን አመልካች ባልና ሚስቱ እንዲካፈሉ ተብሎ ውሳኔ ያረፈበት ይዞታ ተጠሪና ባለቤታቸው በጋብቻ አብረው በነበሩበት ወቅት ተጠሪ ለባለቤታቸው በሰጡት ውክልና መሰረት መጋቢት 29/2008 ዓም በተደረገ የሽያጭ ውል ያስተላለፉላቸው መሆኑን፤ በውሉ መሰረት ጉዳዩ በሚመለከተው አስተዳደር ክፍል ቀርቦ ተገቢውን ክፍያ ፈፅመው በስም ዝውውር ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን በመግለፅ ንብረቱን ባልና ሚስቱ በሽያጭ ያስተላለፋት በመሆኑ እንዲካፈሉ የተሰጠው ውሳኔ ሊሻር ይገባል በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ ያቀርባሉ፡፡…………….

እነ አቶ ቶፊቅ መሀመድ እና የኢፌዲሪ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የሰ.መ.ቁ 190228

እነ አቶ ቶፊቅ መሀመድ እና የኢፌዲሪ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የሰ.መ.ቁ 190228

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ የቀረበው አመልካቾች የፌደራል የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ይግባኝ ሰሚ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 00027 በ26/4/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 169910 በ30/4/12ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት በ19/5/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ በስር የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የዳኝነት ችሎት በአመልካቾች ላይ ባቀረበው ክስ የግል ተበዳይ የሆነው የK.C.J ካምፓኒ ወኪል ጆሽ ወንድማማቾች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የድርጅቱን እቃዎች ከሌሎች ለመለየት የሚያስችል EVEREST (ኤቨረስት) የሚል የማይዳሰስ ንብረት ምስል ባለቤት ነው፡፡…………..

እነ ወ/ሮ አስካለ ዘለቀ እና ወ/ሮ ጽጌ ዘለቀ የሰ/መ/ቁ 188271

እነ ወ/ሮ አስካለ ዘለቀ እና ወ/ሮ ጽጌ ዘለቀ የሰ/መ/ቁ 188271

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች በቀን 24/04/2012 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 178872 በቀን 26/01/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የጀመረው በስር የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካቾችና በዚህ ፍርድ ቤት ተከራካሪ ያልሆኑት ዋና ሳጅን ደረሰ ዘለቀ ከሳሾች ነበሩ፤ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ፡፡

 ከሳሾች በቀን 07/03/2010 ዓ.ም በተፃፈ የውርስ ይጣራልን አቤቱታ የሟቾች አቶ ዘለቀ በቀለ እና ወ/ሮ ደደፌ ዱጉማ የመጀመሪያ ደረጃ እና ተተኪ ወራሾች መሆናቸውን፤ በመግለጽ ውርስ እንዲጣራላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ በማስረጃነትም ሟች አቶ ዘለቀ በቀለ በ16/01/1996 ዓ.ም እና ወ/ሮ ደደፌ ዱጉማ በ14/03/2008 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የሚገልፅ የወራሽነት ማስረጃ አቅርበዋል፡፡እንደሚከተለው ቀርቧል………                           

አቶ መለሰ ዘርጋው እና የፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ የሰ/መ/ቁጥር 185932

አቶ መለሰ ዘርጋው እና የፌዴራል ጠቅላይ ዐ/ሕግ የሰ/መ/ቁጥር 185932

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች በሂሣቡ ውስጥ የሚያዝበት በቂ ገንዘብ አለመኖሩን እያወቀ ቼክ ማውጣት ወንጀሎችን ፈፅሟል በሚል የቀረቡበትን ክሶች በመዝገብ ቁጥር 200631ና 200588 በማጣመር ከመረመረ በኋላ ጥፋተኛ ብሎ ቅጣት መወሰኑና የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም ውሣኔውን ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተበሎ እንዲታረምለት በመጠየቁ ነው፡፡…………….

Previous12345678910NextLast
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us 
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions