ወ/ሮ ላምሮት ዘለቀ እና እነ ወ/ሮ መንበረ ወንድምኩን የሰበር መዝገብ ቁጥር 211647

ወ/ሮ ላምሮት ዘለቀ እና እነ ወ/ሮ መንበረ ወንድምኩን የሰበር መዝገብ ቁጥር 211647

ጉዳዩ በተጠሪዎች መካከል የነበረው እንደባልና ሚስት ግንኙነት በመቋረጡ የግንኙነቱ ውጤት የሆነው የንብረት ክርክር ተደርጎ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ አመልካች ፍርዱን በመቃወም ባቀረቡት አቤቱታ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጀመረ ክርክር ሲሆን ፤ የአመልካች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ ይዘት በአጭሩ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ጥር 12 ቀን 2002 ዓ/ም በሀገር ባህል ጋብቻ ሲፈፅሙ በዚሁ ዕለት በተደረገ የጋብቻ ውል 2ኛ ተጠሪ ከጋብቻው በፊት በስጦታ ያገኙትን በአዲስ አበባ ከተማ የካ ከፍለ ከተማ ወረዳ 12 በ226 ካ.ሜ ይዞታ ላይ ያረፈ 20 ቆርቆሮ ቤት እና ከጋብቻ በኋላ የሚያፈሩትን ንብረት የጋራ ለማድረግ ስምምነት ማድረጋቸውንና በጋብቻ ውስጥ እያሉ ብድር ወስደው ተጨማሪ 9 ከፍሎች እና የውጭ በር ማስራታቸውን በመግለፅ የተጠሪዎች የጋራ ሀብት ነው በማለት ፍርድ ያረፈበት ቤትና የቤት ቁሳቀስ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያፈሩት ንብረት በመሆኑ እነዚህን ንብረቶች አስመልክቶ ፍትሐዊ ውሳኔ ይሰጠኝ የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ………..

. አቶ ሲሳይ ለገሰ ቡሩሳ እና ወ/ሮ እቴነሽ ተስፋዬ የሠ/መ/ቁጥር 211615

. አቶ ሲሳይ ለገሰ ቡሩሳ እና ወ/ሮ እቴነሽ ተስፋዬ የሠ/መ/ቁጥር 211615

ጉዳዩ ዉል ለማስፈረስ የተጠየቀ ዳኝነት ተከትሎ የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበ የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ተጠሪ  በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ቤት በአሁን አመልካችና በስር 1ኛ ተከሳሽ ተሾመ ተስፋዬ ላይ በመሰረቱት ክስ አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰዉን በመከጡሪ ከተማ ዉስጥ ያላቸዉን ወላጅ አባታቸዉ አቶ ተስፋዬ ጨቡዴ እና እናታቸዉ ወ/ሮ አበራሽ ወርቁ በቀን 30/01/1992 ዓ/ም በተጻፈ ዉል አዋሳኙ በክሱ ላይ በተጠቀሰዉ ይዞታ ላይ የተሰራዉን መኖሪያ ቤት ለወንድማቸዉ ለስር 1ኛ ተከሳሽ ሲሰጡ 150 ካሬ ሜትር ቦታ ደግሞ ለእሳቸዉ ሰጥተዋቸዉ በቦታዉ ላይ 5 ክፍል ሰርቪስ ቤት መስራታቸዉን፤ ከዚህ በኋላ በ1998ዓ/ም ዉስጥ በግድያ ወንጀል ተከሰዉ ተፈርዶባቸዉ 9ዓመት ከ1 ወር ከታሰሩ በኋላ በዚሁ በሰሩት ክፍል ቤቶች ዉስጥ እየኖሩ እያሉ የስር 1ኛ ተከሳሽ የራሳቸዉን መኖሪያ ቤት ለአመልካች ሲሸጡ የተጠሪንም ሰርቪስ ቤቶች ቀላቅለዉ ሽጠዋል፡፡ስለሆነም በአመልካችና በስር 1ኛ ተከሳሽ መካከል በቀን 06/07/2008ዓ/ም የተጠሪን ሰርቪስ ቤቶች ተጨምሮ የተደረገዉ የሽያጭ ዉል እንዲፈርስ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ……..

አቶ አማረ አምባዬ እና እነ ወ/ሮ ነጃት ሰይድ የሰ/መ/ቁ. 211408

አቶ አማረ አምባዬ እና እነ ወ/ሮ ነጃት ሰይድ የሰ/መ/ቁ. 211408

የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 438 የሆነ ቤትና ቦታ ያለኝ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ አጎራባች ይዞታ ያላቸው በመሆኑ ተገቢውን ርቅት ጠብቀው ሕንጻቸውን መገንባት ሲገባቸው ከግድግዳዬ ጋር አጣብቀው የሠሩ በመሆኑ ቤቱ በመፍረሱ ግንቦት 13 ቀን 2011 ዓ/ም በተደረገ ውል የደረሰውን ጉዳት ሙሉ በሙሉ እተካለሁ በማለት ሥምምነት ያደረጉ ቢሆንም የበለጠ ጉዳት አድርሰው ውሉ ከሚሸፍነው በላይ ተጨማሪ ጉዳት ደርሷል የሚል ነው መልከም ንባብ……..፡፡

አቶ ፀጋነው መንበሩ እና አራዳ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዬች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 208632

አቶ ፀጋነው መንበሩ እና አራዳ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዬች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሰ/መ/ቁ 208632

ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው አመልካች ባቀረቡት ክስ ላይ ተጠሪ የመጀመሪያ መቃወሚያዎችን አቅርቦ ተከራክሯል፡፡ የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ከሳሽ ያቀረቡትን የዳኝነት ጥያቄ ለማየት ፍርድ ቤቱ ስልጣን አለው? ወይስ የለውም? ከሳሽ ያቀረቡት ክስ በድጋሚ የቀረበ ነው? ወይስ አይደለም? የሚሉ ጭብጦችን ይዞ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በሰጠው ውሳኔ በዚህ መዝገብ የተጠየቀው የዳኝነት ጥያቄ አላግባብ የተወሰነ ግብርን ተንተርሶ የደረሰ ኪሳራ በሚል ኪሳራውን ለማስከፈል የቀረበ ሲሆን ግብሩ አላግባብ ተወስኗል ወይስ አልተወሰነም የሚለውን ለማየት ፍ/ቤቱ ስልጣን የሌለው በመሆኑ ይህን ተከትሎ የደረሰ ኪሳራ ለመወሰን ቀድሞ ጥፋት ባልተረጋገጠበት ሊወሰን ስለማይችል ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለውም፡፡ በሌላም በኩል ከሳሽ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 165438 ተከሳሽ አላግባብ ግብር የወሰነብኝ  በመሆኑ ኪሳራ ይከፈለኝ በሚል ክስ አቅርበው ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን የለኝም ብሎ መዝገቡን የዘጋው በመሆኑና ውሳኔውን በይግባኝ ሳያሽሩ የገንዘብ መጠን ከፍ በማድረግ ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይዘው መቅረባቸው አግባብ አይደለም፡፡ የተጠየቀው ዳኝነት አንድ አይነት ሲሆን ፍ/ቤቱ ወደ ፍሬ ነገር ገብቶ ያላከራከረ ቢሆንም በተሰጠው ብይን ይግባኝ ከማለት በቀር የገንዘብ መጠን ጨምሮ ክስ ማቅረብ አግባብ ባለመሆኑ የከሳሽ ክስ በድጋሚ የቀረበ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡መልካም ንባብ…..

ኦርጋኒክ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር ሰ/መ/ቁጥር 217051.

ኦርጋኒክ ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር ሰ/መ/ቁጥር 217051.

ክርክሩ በብድር የተሰጠ ገንዘብ አመላለስን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ.ም በአጭር ስነ ስርዓት ባቀረበው ክስ በግራ ቀኙ መካከል መስከረም 9 ቀን 2011 ዓ.ም በተደረገ የብድር ውል አመልካች ከ13% ወለድ ጋር ለመክፈል ተስማምቶ ብር 500,000 የተበደረ ቢሆንም ብድሩን ሳይከፍል 32 ወራት ስለቆየ ዋናውን ገንዘብ ብር 500,000፣ ወለድ ብር 188,980.36፣ በውሉ መሰረት ብድሩን ባለመክፈሉ በየቀኑ የሚታሰብ 0.25% መቀጮ ብር 450,000 በድምሩ ብር 1,138,890.36 እንዲከፍል ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ……….

123578910Last