እነ አቶ ግርማ አዳነ እና ላልይበላ ንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁጥር 247702

እነ አቶ ግርማ አዳነ እና ላልይበላ ንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁጥር 247702

የክሱ ይዘት በአጭሩ በላልይበላ ከተማ በንግድ ማህበር ተደራጅተን እየሰራን በሂደት 19 ክፍል የያዘ ሆቴል ገንብተን በለልይበላ ነጋዴዎች ማህበር ስም እየሰራን እያለ በአክሲዮን ሽያጭ ጠቅላላ ካፒታላችን ብር 2‚295‚500(ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና አምስት ሺ አምስት መቶ ብር) ስለደረሰ በ2002 ዓ.ም የማህበሩ ገንዘብ ያዥ የነበሩ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ የሆነው ሁለተኛ ተከሳሽ  የ10 ሰዎችን አክሲዮን ገዝቻለው በሚል ከ10 ሰዎች ውጪ ባለነው በ21 አባላት ስም እንደ አዲስ ማህበር መመስረት አለብን በማለት ለማህበሩ ሀሳብ አቅርቦ ከሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ የማህበሩ ስም ወደ ጌታቸው ግርማ እና ጓደኞቹ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሚል ቀይሮ እየሰራ እያለ በማህበሩ አካላት መካከል አለመግባባት ተፈጥሮአል፡፡አመልካቾች እንደ ቁጥጥር ኮሚቴ አባልነታችን በመመስረቻ ፅሁፍ አንቀፅ 8 በተሰጠን ስልጣን መሰረት የአመራር ግድፈቶች እንዲስተካከሉ የምናደርገውን ቁጥጥር በመቃወም የመተዳደሪያ ደንቡ አንቀፅ 4(2) ባላገናዘበ መልኩ አለአግባብ ከማህበሩ ስላሰናበተን ወደ ማህበራችን እንድንመለስ፣ወደ ማህበሩ የማንመለስ ከሆነም ንብረቱ ተጣርቶ በአዲስ መልክ ከተመሰረተበት ከ1997 ጀምሮ ማህበሩ ኦዲት ተደርጎ ጉዳዩ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥበት የሚገኘው ድርሻችን እና ትርፋችን ታስቦ እንዲከፈለን የሚል ነው፡፡ተጠሪም በሰጡት መልስ በአመልካቾች የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ፍ/ቤቱም ይርጋን በተመለከተ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ በፍ/ህ/ቁጥር 448(2) መሰረት በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ላይ የሚቀርብ እንጂ ለማህበር ይፍረስልን እና ድርሻችን ይሰጠን ጥያቄ ላይ የሚቀርብ ስላልሆነ እንዲሁም ግንኙነታቸው በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ የይርጋውን መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ በፍሬ ነገሩ ላይ የግራ ቀኙን ማስረጃ መዝኖ የአመልካቾች ስንብት ህገ-ወጥ ስለሆነ ወደ ማህበሩ እንዲመለሱ እና ድርሻቸው ተካቶ የተሰራው የአክሲዮን ድልድል ታርሞ ክፍፍሉ ይፈፀም ሲል ወስኗል፡፡መልካም ንባብ….

እነ አቶ አበራ ነጋሽ ደምሴ(6) ሰዎች እና ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኔዓለም ቤ/ክርስቲያን፤ የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት የሰበር መ/ቁ/245981

እነ አቶ አበራ ነጋሽ ደምሴ(6) ሰዎች እና ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኔዓለም ቤ/ክርስቲያን፤ የቦሌ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት የሰበር መ/ቁ/245981

ጉዳዩ የመሬት ባለይዞታነት መብት የሚመለከት ሲሆን በስር ፍርድ ቤት የአሁን አመልካቾች ከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡አመልካቾች በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ131415 ባቀረቡት ክስ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል ውስጥ የሚገኝ ከ1-5 የተዘረዘሩት አመልካቾች ወላጅ አባት እና የ6ኛ አመልካች ወንድም የሆኑት በጋራ ይዘው ይጠቀሙበት የነበረ በግምት ከ60‚000 ካ.ሜ ያላነሰ ስፋት ያለው አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰ ይዞታ ለረጅም ጊዜ ግብር እየገበሩበት ሲጠቀሙ የቆዩ ቢሆንም ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በ1ኛ ተጠሪ ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ኮሚቴ አባላት አማካኝነት የሀይማኖት ተቋሙ በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን መፈራት እና መከበር በመጠቀም የአመልካቾችን ይዞታ ለመቃብር ቦታ በሚል ምክንያት በመውሰድ ከፋፍሎ እና ሼዶችን ገንብቶ ለጋራዥ እና ሌሎች የንግድ አገልግሎቶች ኪራይ ገቢ እየሰበሰበ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰራ በማድረግ በህገወጥ መንገድ ይዞት ይገኛል፡፡ስለሆነም ለ1ኛተጠሪ የተሰጠው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰርዞ ለአመልካቾች እንዲመለስ ሲሉ ዳኝነት መጠየቃቸዉን መዝገቡ ያሣያል፡፡መልካም ንባብ….

አቶ ጉዕሽ ካሳ ደሞዝ እና እነ አቶ አማኑኤል ወልደሊባኖስ ተስፋዬ የሠ/መ/ቁጥር 243564

አቶ ጉዕሽ ካሳ ደሞዝ እና እነ አቶ አማኑኤል ወልደሊባኖስ ተስፋዬ የሠ/መ/ቁጥር 243564

ጉዳዩ ዳግም ዳኝነት የሚታይበትን አግባብ የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው አመልካች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የዳግም ዳኝነት አቤቱታ በማቅረባቸው ሲሆን ችሎቱ ክርክሩን መርምሮ ለሰጠዉ ዉሳኔ መነሻ ያደረገዉ ተጠሪዎች ለስር ፍርድ ቤት ያቀረቡትን የሰነድ ማስረጃዎች መሆኑን፤ነገር ግን የኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን ለአመልካች ድርጅት ብር 17,500,000.00 መክፈሉን ለማረጋገጥ በይግባኝ ሰሚዉ ችሎት በመ/ቁጥር 211132 እና በመ/ቁጥር 211227 ላይ ይግባኝ ያቀረቡት የአሁን ተጠሪዎች ለስ ፍርድ ቤት በማስረጃነት ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ ሐሰተኛ ስለመሆኑ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 249579 ላይ በቀን 16/10/2014 ዓ/ም በሰጠዉ ዉሳኔ ማረጋገጡን በመዘርዝር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥርር 6 መሠረት ዳግም ዳኝነት እንዲታይላቸዉ ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ….

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ እና የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የሰ.መ.ቁ 246233

የጉዳዩ አመጣጥ ተጠሪ ለግልግል ዳኝነት ጉባኤ በ1ኛ አመልካች ላይ ባቀረበው ክስ በተጠሪ እና በ2ኛ አመልካች(ስር ጣልቃገብ ) መካከል ከወራቤ እስከ በጆበር ያለውን 38.5ኪ.ሜ የመንገድ ስራ ፐሮጀክት ለማከናወን እ.ኤ.አ ሜይ 20 2016 ውል የተፈረመ ሲሆን የውሉም አይነት ስራ ተቋራጩ(2ኛ አመልካች) የዲዛይንና የግንባታ ስራውን በሙሉ በኃላፊነት የሚያከናውንበት ነው፡፡ በውሉ መሰረት ስራ ተቋራጩ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና የማቅረብ ግዴታ ስላለበት ይህን ተከትሎ ተቋራጩ የውሉን 10% ይኅውም ለብር 45‚844‚565 እ.ኤ.አ ከሜይ 13 2016 ጀምሮ ለአራት አመት ጸንቶ የሚቆይ የቦንድ ፖሊሲ ቁጥሩ በተገለጸ 1ኛ አመልካች የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ሰጥቷል፡፡ በውሉ መሰረት እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 26 2017 የተጀመረው የግንባታ ስራ በ1095 ቀናት ተጠናቆ ለግዜያዊ ርክክብ ብቁ መደረግ ሲገባው እና ከአመት በኋላ ጃንዋሪ 2018 አፈጻጸሙ 30.38% መሆን ሲገባው የስራ ተቋራጩ አፈጻጸም የውሉ 8% ላይ ነበር፡፡ በዛን ግዜም ከውሉ መፈጸሚያ ግዜ 33.8% ባክኖ ነበር፡፡ ተጠሪ ለስራ ተቋራጩ በቂ የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ቢሰጠውም፤ ሶስት የክፍያ ሰርተፍኬቶችም ጸድቀው ገንዘብ ቢከፈለውም፤ የውል ግዴታውን እንዲወጣ ተጠሪና የፕሮጀክቱ አማካሪ ድርጅት ተደጋጋሚ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ ቢሰጡትም ይህን ባለመቀበል የግንባታ ቦታውን ጥሎ በመሄድ አይነተኛና መሰረታዊ የውል ጥሰት በመፈጸሙ ተጠሪ በውሉ መሰረት እ.ኤ.አ በ1/3/18 በተጻፈ ደብዳቤ የ2ኛ አመልካችን(ስራ ተቋራጭ) የስራ ውል አቋርጧል፡፡

የስራ ውል መቋረጡን ተከትሎ 1ኛ አመልካች የዋስትናውን ገንዘብ ገቢ እንዲያደርግ ተጠሪ ቢጠይቀውም የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ የዋስትና ግዴታውን ለመወጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ 1ኛ አመልካች በመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና መሰረት ብር 45‚844‚565 ክፍያ እንዲፈጽም ከተጠየቀበት ግዜ ከ27/6/2010ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፍል እንዲወሰንበት በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…

አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594

አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594

ጉዳዩ የዋስትና መብት አተገባበር የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረተዉ ክስ አመልካች በኢፌዲሪ ወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1/ሀ) እና 590(1/ሀ እና 2/ሐ) ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነት በሚፈፀም የሰው ማገት(መጥለፍ) ወንጀል በመፈጸሙ ተከሷል የሚል ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ አመልካች የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ፍርድ ቤቱም የዋስትና መብት ጥያቄውን በተመለከተ በሰጠው ትዕዛዝ አመልካች የተከሰሰበት ክስ በመርህ ደረጃ ዋስትና የማያስከለክል ቢሆንም እንጂ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን ድርጊት አፈፃፀም በተመለከተ አመልካች የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ ለብሰው እና የጦር መሳሪያ ይዘው ፈፀመ ተብሎ በክስ ዝርዝር ላይ ባይገለፅም ድርጊቱን ፈፅሞ ከሆነ ተሳትፎዉ ወደ ፊት ማስረጃ በመስማት ጊዜ የሚታይ ሆኖ በአጠቃላይ ከክሱ ዝርዝር ፍርድ ቤቱ የወንጀሉ አፈፃፀሙ ከባድ ሆኖ ስለአገኘዉ አመልካች ምን አልባት ወደፊት የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙ ተረጋግጦ ጥፋተኛ የሚባል ከሆነ ሊጣልበት የሚችለው ቅጣት ከባድ ሊባል የሚችል በመሆኑ ይህን ፈርቶ ቀጠሮ አክብሮ ይመጣል የሚል እምነት የለንም በማለት የአመልካችን የዋስትና መብት ጥያቄ ዉድቅ አድርጓል፡፡መልካም ንባብ…..

123578910Last