አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594 አቶ ዮሀንስ ካሳዬ እና የፍትህ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የሠ/መ/ቁጥር 273594 ጉዳዩ የዋስትና መብት አተገባበር የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረተዉ ክስ አመልካች በኢፌዲሪ ወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1/ሀ) እና 590(1/ሀ እና 2/ሐ) ስር የተደነገገዉን በመተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነት በሚፈፀም የሰው ማገት(መጥለፍ) ወንጀል በመፈጸሙ ተከሷል የሚል ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ አመልካች የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ፍርድ ቤቱም የዋስትና መብት ጥያቄውን በተመለከተ በሰጠው ትዕዛዝ አመልካች የተከሰሰበት ክስ በመርህ ደረጃ ዋስትና የማያስከለክል ቢሆንም እንጂ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን ድርጊት አፈፃፀም በተመለከተ አመልካች የመከላከያ ሰራዊት የደንብ ልብስ ለብሰው እና የጦር መሳሪያ ይዘው ፈፀመ ተብሎ በክስ ዝርዝር ላይ ባይገለፅም ድርጊቱን ፈፅሞ ከሆነ ተሳትፎዉ ወደ ፊት ማስረጃ በመስማት ጊዜ የሚታይ ሆኖ በአጠቃላይ ከክሱ ዝርዝር ፍርድ ቤቱ የወንጀሉ አፈፃፀሙ ከባድ ሆኖ ስለአገኘዉ አመልካች ምን አልባት ወደፊት የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙ ተረጋግጦ ጥፋተኛ የሚባል ከሆነ ሊጣልበት የሚችለው ቅጣት ከባድ ሊባል የሚችል በመሆኑ ይህን ፈርቶ ቀጠሮ አክብሮ ይመጣል የሚል እምነት የለንም በማለት የአመልካችን የዋስትና መብት ጥያቄ ዉድቅ አድርጓል፡፡መልካም ንባብ…..
አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592 አቶ ሰለሞን አርአያ እናእነ ህፃን ዳንኤል ቴውድሮስ ሞግዚት ወ/ሮ የሺ መንግስቱ(5ሰዎች)የሰ/መ/ቁጥር፡- 255592 ጉዳዩ የውርስ ማጣራትን የሚመለከት ሆኖ አቤቱታው በቀረበበት የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች 5ኛ ጣልቃ ገብ ፣ 2ኛ ተጠሪ የስር ተጠሪ፤1ኛ ተጠሪ የስር አመልካች፤ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያሉ ተጠሪዎች ደግሞ 3ኛ፤4ኛ እና 6ኛ ጣ/ገቦች ነበሩ፡፡ የክርክሩ አመጣጥ በአጭሩ፡- የአሁን 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ የሟች ባለቤታቸው ቴውድሮስ አርአያ ወላጆች የልጃቸው አያት የሆኑት ጀነራል አርአያ ዘርዓይ ጥር 25 ቀን 2003 ዓም እናቱ ወ/ሮ ሰነዳይ ሀይሌ ጥር 04 ቀን 2004 ዓም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ መሆኑን፤ባለቤታቸው ከወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆን በ29/08/2005 ዓም ወራሽነታቸውን ያረጋገጡ ቢሆንም ውርሱ ሳይጣራ መኖሪያ ቤቱን ሳይከፋፈሉ በጋራ ይዘው ሲጠቀሙበት ቆይተው ከ2006 ዓም ጀምሮ ቤቱን አከራይተው የኪራዩን ገንዘብ እኩል እየተካፈሉ መሆኑን ገልጠው ድርሻቸውን ለይተው ለማወቅና ለማረጋገጥ እንዲችሉ የውርስ ሀብት እንዲጣራ ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…..
ወ/ሮ በላይነሽ ጫላእና አቶ ሸዋንግዛው ሽብሩ/ቁጥር የሰ/መ/ቁ 254862 ወ/ሮ በላይነሽ ጫላእና አቶ ሸዋንግዛው ሽብሩ/ቁጥር የሰ/መ/ቁ 254862 ጉዳዩ በጋብቻ ዉስጥ ተፈርቷል የተባለ ሀብት ስለሚጣራበት አግባብ የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ - ከአመልካች ጋር በጋብቻ ዉስጥ በነበሩበት ጊዜ ያፈሩት ንብረቶች እንደሆነ እና ጋብቻቸዉ መፍረሱን በመግለጽ የተለያዩ ንብረቶችን በመዘርዝር ድርሻቸዉ ተካፍሎ እንዲሰጣቸዉ የጠየቁ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ በፊት አዲስ አበባ ከተማ ስር ኮዬ ፈጬ ሳይት የነበረ አሁን ላይ በሸገር ከተማ በገላን ክፍለ ከተማ ኮዬ ፈጬ ሳይት ፕሮጀክት 16፣ ብሎክ 34፣ 6ኛ ፎቅ የሚገኝ፣የቤት ቁጥር 56 ባለ ሶስት መኝታ በአመልካች ስም የተሰጠና ብር 1,500,000.00 የሚያወጣ ስላለን እኩል እንድታካፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…..
ወ/ሮ ሳፊያ ከድር እና እነ ሐጂ አማን ሐጂ ሁሴን (6ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 254696 ወ/ሮ ሳፊያ ከድር እና እነ ሐጂ አማን ሐጂ ሁሴን (6ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 254696 ጉዳዩ የውርስ ድርሻን የሚመለከት ሲሆን ክሱ በቀረበበት ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ባሌ ዞን በርበሬ ወረዳ ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ 1ኛ ተጠሪ ተከሳሽ፤ ከ2ኛ እስከ 6ኛ ያሉ ተጠሪዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ ተከራካሪዎች ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ ይዘት፡- የ1ኛ ተጠሪ ሚስት የነበሩት እናታቸው ወ/ሮ ነኢማ ሀሚድ በሞት ከዚህ ዓለም መለየታቸውንና የሟች ወራሾች 7(ሰባት) እንደሆኑ ፤ ሟች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር አፍርተዋል የሚሉትን መገኛቸው እና አዋሳኞቹ በክሱ ላይ ከተመለከቱት ከተራ ቁጥር 1-10 ከተዘረዘሩ ንብረቶች የሟች 50% የሚስት ድርሻ መሆኑን በመግለጽ 1ኛ ተጠሪ የውርስ ድርሻቸውን እንዲያክፈሏቸው እንዲወሰንላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…..
ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ኃይሉ እና እነ ወ/ሮ እታገኘው ኃይሉ(4ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 253718 ወ/ሮ ኢየሩሳሌም ኃይሉ እና እነ ወ/ሮ እታገኘው ኃይሉ(4ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 253718 ጉዳዩ የውርስ ማጣራትን ተከትሎ የውርስ ሀብት ስለመሆኑ በተለየ ንብረት ላይ መብት ያላቸው ወራሾች ሊያገኙ ይችሉ የነበረውን ገቢ ቤቱን ከያዘው ሰው ለመጠየቅ ያላቸውን መብት የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን 1ኛ፣2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ከሳሾች፣4ኛተጠሪ ጣልቃገብ አንደዚሁም አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡በተጠሪዎች የቀረበው ክስ በአጭሩ ሟቾች አቶ ሀይሉ ደነቀው እና ወ/ሮ ልንገርሽ ይሁኔ በ422 ካ.ሜ ላይ ያረፈና የቤት ቁጥር 191 የሆነ ዋና ቤትና ሰርቪስ ቤቶች የነበሯቸው ሲሆን በመ/ቁ 82464 በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት በነበረን የውርስ ሀብት ይጣራልን ክርክር ላይ የሟች አቶ ኃይሉ ደነቀው የውርስ ሀብት ተጣርቶ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡አመልካች በኑዛዜ የተላለፈላቸው 02 ክፍል ቤት ብቻ ሲሆን ክፍሎቹን እያከራዩ የሚጠቀሙበት ሆኖ በውርስ የሚደርሰንን ዋና ቤትና ሰርቪስ ቤቶችን ከህግ አግባብ ውጪ በመያዝ በዋናው ቤት እየኖሩበት አከራይተን እንዳንጠቀም በማድረግ ሰርቪስ ቤቶቹን ከተከራዩት ሰዎች ላይ የኪራዩን ገንዘብ በመሰብሰብ ለራሳቸው ጥቅም በማዋል ልናገኝ የሚገባውን ጥቅም አሳጥተውናል፡፡በመሆኑም በውሳኔው መሰረት የሚኖሩበትን ዋናውን ባለ ሶስት ክፍሉን ቤት እና የምያከራዩትን 03 ክፍል ሰርቪስ ቤቶች ከነቦታው ለቀው እንዲያስረክቡን በተደጋጋሚ ከመጠየቅ ባሻገር ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ደግሞ የጹሑፍ ማስጠንቀቂያ የሰጠናቸው ቢሆንም አመልካች ቤቶቹን ለማስረከብ እንደዚሁም የቤቶቹ ኪራይ ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሟች ከሞቱበት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ዋናው ቤት ቢከራይ በወር ብር 8000 (ስምንት ሺህ) ክስ እስካቀረብንበት ጊዜ ድረሰ ያለውን የ28 ወር ብር 224,000.00 (ሁለት መቶ ሀያ አራት ሺህ) እንዲከፍሉን፣የሚከራዩ 3 (ሶስት) ክፍል ሰርቪስ ቤቶች ሟች ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ ወር ብር 1500 (አንድ ሺ አምስት መቶ) ይከራይ የነበረው አመልካች ብር 300 (ሶስት መቶ) በመጨመር ብር 1800 (አንድ ሺ ስምንት መቶ)፣ ሌላው 1 (አንድ) ክፍል ቤት 500 (አምስት መቶ) ይከራይ ነበረው ብር 700 (ሰባት መቶ) እና ቀሪውን 01 ክፍል ቤት በብር 1000 (አንድ ሺህ) ልዩነቱ የ4 (አራት) ወር ብር 4000 (አራት ሺ) ሟች ከሞቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጋቢት ወር መጨረሻ ክስ እስካቀረብንበት ጊዜ ድረስ ያለው ሲሰላ ሁለት ዓመት 24 (ሀያ አራት) ወር በመሆኑ ብር 70,000.00 (ሰባ ሺህ) በድምሩ ብር 74,000 (ሰባ አራት ሺህ) ልናገኝ የሚገባውን ጥቅም ያሳጡን ስለሆነ ዋናውን ቤት እና የሰርቪስ ቤቶቹን የኪራይ ገንዘብ ተከፍሎ እስከሚጠናቀቅበት ድረስ ከነወለዱ ታስቦ እንድከፍሉን እንዲወሰንልን የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…..