ጉዳዩ የሽያጭ ውል የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ከሳሽ በመሆን በአመልካቾች ላይ በሁለት የተለያዩ መዝገቦች ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካቾች በደራጀማ ሆቴል ኃ/የተ/የግ/ማህበር ውስጥ ስድስት አክሲዮኖችን ከአንድ ሱቅ ጋር እንሸጥላችኋለን በማለት በ2004 ዓ.ም በተደረገው ውል ለ1ኛ ተጠሪ በብር 450,000.00 እንዲሁም ለ2ኛ ተጠሪ በብር 480,000.00 የሸጡልን ቢሆንም ውሉ ከህግ ውጪ የተደረገ በመሆኑ አመልካቾች በሽያጭ ውሉ መሰረት የወሰዱት ገንዘብ እንዲመልሱልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡አመልካቾች በበኩላቸዉ ውሉ የተደረገው በቃል መሆኑንና አንደኛው ተዋዋይ በውሉ ጥቅም አለማግኘቱ የውል ማፍረሻ ምክንያት አይሆንም፣የተሸጠው በሱቅ የመጠቀም መብት እንጂ የሱቅ ባለሀብት እንዲሁም የአክሲዮን ድርሻ ላይ አይደለም፣ተጠሪዎች ሱቁን በመረከብ ሲጠቀሙበት ቆይቷል፤ይህም በሱቁ ላይ ጥቅም ሲያገኙ እንደነበር የሚያሳይ ነው፣ተጠሪዎች የከፈሉት ገንዘብ የሚመለስበት የህግ አግባብ የለም፣ማህበሩ የሚሰራበት ቤት ከቤቶች ኮርፖሬሽን በመከራየት ነዉ፤በመሆኑም ተጠሪዎች ያቀረቡት ክስ ውድቅ እንዲደረግ በማለት ተከራክረዋል፡፡………………..