ሐረማያ ዩንቨርስቲ እና መላ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግል ማሕበር የሰ/መ/ቁ. 253530

ሐረማያ ዩንቨርስቲ እና መላ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግል ማሕበር የሰ/መ/ቁ. 253530

ጉዳዩ ከግንባታ ውል ጋር በተያያዘ በስር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ በቀረበው የዳኝነት ጥያቄ መሰረት መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበርአቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ተከሳሽ ነበር፡፡አመልካች በ20/01/2013 ዓ/ም ጽፎ ባቀረበው ክስ አመልካች እና ተጠሪ በነሀሴ 2009ዓ/ም እ.ኤ.አ የማስፋፊያ ግንባታ ለማከናወን ተስማምተው ተጠሪ ሳይቱን በመረከብ የግንባታ ማስፋፊያ ስራውን ጀምሮ የነበረ ቢሆንም በውሉ በተቀመጠው ጊዜ እና ጥራት የግንባታ ስራውን ማከናወን ባለመቻሉ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቅያ ሰጥቶ ስራው 93% ላይ እያለ አመልካች ውሉን አቋርጧል፡፡ በመሆኑም ለአምስት ሕንፃዎች/ብሎኮች የስራ ግድፈት ማስተካከያ ብር 2,031,357.91፣ ለኩሽና፣ መጽሀፍት ቤትና ምግብ ቤት ማስተካከያ ሥራ ብር 350,759.30፣ የውሉ አፈጻጸም በመዝግየቱ በውሉ አንቀጽ 49.1 መሰረት የጠቅላላ ውሉን ዋጋ 10% የደረሰ ኪሣራ ብር 5,219,807.91እና የቀሪ ሥራ ማጠናቀቂያ ብር 492,255.18በድምሩ ብር 10,107,964.5 ተጠሪ እንዲከፍል እንዲወሰንለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…..

አቶ ቴዎድሮስ መስፋን ህንፃ ሥራ ተቋራጭእና አዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (በአሁኑ - የአ/አ ቤ/ልማት ኮርፖሬሽን) የሰበር መ/ቁ 253303

አቶ ቴዎድሮስ መስፋን ህንፃ ሥራ ተቋራጭእና አዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (በአሁኑ - የአ/አ ቤ/ልማት ኮርፖሬሽን) የሰበር መ/ቁ 253303

በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዳይ የግንባታ ዉልን የሚመለከት ነዉ፡፡ ጉዳዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ አመልካች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 04664 እና መ/ቁ 06910 አጣምሮ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ/ም የሰጠዉን ዉሳኔ ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 37544 ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ/ም የሰጠዉን ዉሳኔ ፤ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 40218 ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ/ም የሰጠዉን ዉሳኔ በመቃወም ነው፡፡

ተጠሪ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ  ከአመልካች ጋር መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ/ም ጠቅላላ ዋጋዉ የብር 19,044,907.52 (አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን አርባ አራት ሺ ዘጠኝ መቶ ስባት ከ52/100) የህንፃ ግንባታ ዉል የፈፀምን ሲሆን መንግስት ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ በዘርፉ የሚገኙ ተቋራጮች በአንድ ዘርፍ ብቻ እንዲሳተፉ ስለተደረገ አመልካች በአዲስ አበባ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ሥር በግንባታ ስራ ያለመሳተፍ ማስረጃ አንዲያቀርብ ተጠይቆ ተጠሪ መስከረም 12 ቀን 2008 ዓ/ም የተፃፈ ሀሰተኛ ማስረጃ በማቅረቡ በዉሉ አንቀፅ 2 መሰረት የማጭበርበር ስራ የፈፀመ በመሆኑ ዉሉ የተቋረጠ ሲሆን አመልካች አለአግባብ የወሰደውን ብር 3,264,297.15 (ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ አራት ሺ ሁለት መቶ ዘጠና ስባት ከ15/100) ቅድመ ክፍያ ለመመለስ ፍቃደኛ ስላልሆነ ይህን ገንዘብ ከወለድ ጋር እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል፡፡መልካም ንባብ…..

ደጀኔ ደበላ አልቀረበም እና ኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 251700

ደጀኔ ደበላ አልቀረበም እና ኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የሰ/መ/ቁጥር 251700

ጉዳዩ ይለፍ ወረቀት ሳይይዙ የግብርና ምርቶችን ማጓጓዝ ወንጀል የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በሰሜን ሸዋ ዞን ወራ ጃርሶ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡በተጠሪ የቀረበውም ክስ አመልካች የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያወጣውን የገበያ ቁጥጥርና የምርት ጥራት አዋጅ ቁጥር 234/2013 አንቀፅ 26(3) እና 5 በመተላለፍ ታህሳስ 03 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 4፡00 ሰአት በወራ ጃርሶ ወረዳ ቀሬ ጎሃ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ኬላ ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ የሰሌዳ ቁጥር 3-16932 ኢት በሆነ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ላይ 220(ሁለት መቶ ሃያ) ኩንታል ባቄላ ግምቱ 836,000 (ስምንት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ) የሆነውን ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያለ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ሲደርስ በኬላ ተቆጣጣሪዎች ሲፈተሽ የንግድ ፍቃዱና የመነሻ እና መድረሻ የይለፍ ወረቀት ሳይይዝ በመጓዙ ያለ ፍቃድ የግብር ምርቶችን በማጓጓዝ ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…..

እነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ድንቁ(2ሰዎች)የቀድሞ አርጋፋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት (በአሁን አርጋፋ ማዘጋጃ ቤት)የሰ/መ/ቁ፡- 250597

እነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ድንቁ(2ሰዎች)የቀድሞ አርጋፋ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት (በአሁን አርጋፋ ማዘጋጃ ቤት)የሰ/መ/ቁ፡- 250597

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ሐምሌ 03 ቀን 2015ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 26960፤ ጥቅምት 28 ቀን 2015 የሰጠው ውሳኔ እና ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 42102፤ ሚያዝያ 03 ቀን 2015ዓ.ም መወሰኑ የመሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው፡፡

ጉዳዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 6 መሠረት የቀረበን የዳግም ዳኝነት ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ከመነሻው በዋናው ጉዳይ ክርክር የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል አጋርፋ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡መልካም ንባብ…..

አቶ ኩማ መልኩ እና አቶ ሰለሞን ዘለቀ የሰበር መ/ቁ/250546

አቶ ኩማ መልኩ እና አቶ ሰለሞን ዘለቀ የሰበር መ/ቁ/250546

መዝገቡ ለሰበር ችሎት የቀረበዉ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የስር ፍርድ ቤት ዉሳኔ የህግ ስህተት የለዉም በማለት በመ/ቁ/ 423754 ላይ በቀን 11/09/2015ዓ.ም የሰጠዉ ትእዛዝ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል በዚህ ሰበር ችሎት እንዲታረም በማለት አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነዉ፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በስር ፍርድ ቤት አመልካቹ ከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩ ሲሆን ጉዳዩ እርሻ መሬት ይዞታ የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካች ሃምሌ 12 ቀን 2014ዓ.ም በዲጋሉና ጢጆ ወረዳ ፍርድ ቤት ባቀረበው አቤቱታ በዲጋሉ አራቢ ቀበሌ ውስጥ የሚገኘውን አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰ መሬት ከአያቴ ከበደ ዋቅጅራ እና ሴት አያቴ ወ/ሮ የሺ ተ/ማሪያም በመ/ቁ/43575 በሆነው በዉርስ ተወስኖልኝ በመ/ቁ 43575 ተፈጽሞልኝ እያለ ተጠሪ ምንም መብት ሳይኖረዉ ስለያዘብኝ እንዲለቅልኝ ሲል የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባቀረበው መልስ ይዞታው የአመልካች አያቶች ሳይሆን በቅይይር ከአቶ ታደሰ ከበደ ያገኘሁት የግል ይዞታዬ ነው፤የተቀያየርነውን ይዞታ ሰዎች ተቀብለው የመኖሪያ ቤት የሰሩበት ሲሆን እኔም ይዞታውን እየተጠቀምኩበት ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለዉም በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ…..

First2345791011Last