አቶ ደረጀ ቢያዝን እና ፋል ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የሰ/መ/ቁ. 216938

አቶ ደረጀ ቢያዝን እና ፋል ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የሰ/መ/ቁ. 216938

ጉዳዩ በመጀመሪያ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ተጠሪ ያቀረበውን መቃወሚያ በብይን ውድቅ ካደረገ በኋላ በፍሬ ነገሩ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶ አመልካች ከስራ የተሰናበቱት በህገ ወጥ መንገድ ስለሆነ የስድስት ወር ደሞዝ ተከፍሏቸው ወደ ስራቸው ይመለሱ በማለት ወስኗል፡፡ ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ያስቀርባል ካለ በኋላ ግራ ቀኙን አከራክሮ በስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ብይን እና ውሳኔ አፅንቶታል፡፡ ለዚህ ፍርድ መነሻ የሆነው የሰበር አቤቱታ በአመልካች የቀረበውም የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሲያፀና አመልካች እስከ አንድ ዓመት የሚደርስ ውዝፍ ደሞዝ እንዲከፈላቸው አለመወሰኑን በመቃወም ለማስለወጥ ነው፡፡ መልካም ንባብ……..

እነ አቶ አበበ እንሰተነ እና አቶ ኃይሉ ቦሬሳ የሰ.መ.ቁ 216299

እነ አቶ አበበ እንሰተነ እና አቶ ኃይሉ ቦሬሳ የሰ.መ.ቁ 216299

የጉዳዩ አመጣጥ አመልካቾች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረቡት የክስ አቤቱታ በፍ/ቤቱ በመ.ቁ 105883 በ29/6/08ዓ.ም በዋለው ችሎት በፍርድ ቤቱ ጸድቆ የነበረ የውርስ አጣሪ ሪፖርት በፍ/ብ/ህ/ቁ 998 መሰረት እንዲሰረዝላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…….

እነ አቶ ጳውሎስ ኦርጂኖ እና አቶ ተስፋዬ ኤጌዶ የሰበር መ/ቁ/215762

እነ አቶ ጳውሎስ ኦርጂኖ እና አቶ ተስፋዬ ኤጌዶ የሰበር መ/ቁ/215762

ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸም የሚመለከት ጉዳይ ነዉ፡፡የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ፡- ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን በአሁኑ አመልካቾች ላይ ባቀረበው ክስ አመልካቾች በዱራሜ ከተማ ውስጥ በ460.6 ካ.ሜ ላይ ያላቸውን መኖሪያ ቤት በብር 2,250,000.00 በቀን 24/01/2012 ዓ.ም በተደረገው ውል ሽጠውልኝ ቀብድ ብር 1,000,000 መቀበላቸዉን እንዲሁም የተጠሪ ወኪል በ1ኛ አመልካች የባንክ ሂሳብ ብር 800,000.00 ገቢ በማድረጋቸው በአጠቃላይ ብር 1,800,000.00 የተቀበሉ መሆኑን ገልጾ አመልካቾች በውሉ መሰረት ቤቱን እንዲያስረክቡ እንዲወሰን ይህ ካልሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1885(2) መሰረት የተቀበሉትን ቀብድ አጠፌታ እና ገንዘቡ ተከፍሎ እስከሚያልቅ ህጋዊ ወለድ ከወጪና ኪሳራ ጋር  እንዲከፍሉ እንዲወሰን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል መልካም ንባብ……..

ወ/ሮ ፋኖስ ባይልኝ እና እነ ወ/ሮ ፋኖስ ባይልኝ የሰ/መ/ቁ 215524

ወ/ሮ ፋኖስ ባይልኝ እና እነ ወ/ሮ ፋኖስ ባይልኝ የሰ/መ/ቁ 215524

ከሳሾች ባቀረቡት አቤቱታ ወላጅ አባታችን አስር አለቃ ሞገስ ጋሻው ከዚህ አለም በሞት ስለተለዩ የውርስ ሀብት እንዲጣራ ውርስ አጣሪ እንዲሾምልን በማለት ጠይቀው ተከሳሾችም ክርክራቸውን አቅርበው ውርሱ ተጣርቶ ሪፖርቱ ጥቅምት 24/2009 ዓ.ም ተዘጋጅቶ ቀርቦ ፍ/ቤቱ የውርስ አጣሪ ሪፖርቱን በማረም አጽድቆታል፡፡ በዚህ ውሳኔ ላይ በይግባኝ እስከ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ደርሶ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በመ/ቁ 177586 ግንቦት 26 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለ ችሎት የስር ፍርድ ቤቶች አከራካሪውን  የቤት ቁጥር 1285 የሆነ መኖሪያ ቤት በተመለከተ የሰጡትን ውሳኔ በመሻር ጉዳዩ ተጣርቶ እንዲወሰን ጭብጥ ለይቶ በመመሪያ ወደ ስር ፍርድ ቤት መልሷል፡፡ መመሪያ የተሰጠውም የአሁን አመልካች ከሟች ባለቤታቸው ፲ አለቃ ሞገስ ጋሻው በትዳር ሲኖሩ ለክርክር መነሻ የሆነውን የቤት ቁጥር 1285 የሆነ መኖሪያ ቤት በጋራ ያፈሩት ንብረት መሆን አለመሆኑን የግራቀኙን ማስረጃ እራሱ ፍርድ ቤቱ ሰምቶና ተገቢውን ማጣራት አድርጎ ውሳኔ እንዲሰጥበት በሚል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 343(1) ነው፡፡ መልካም ንባብ……..

መ/ር ሙሴ አሳየኸኝ የሰበር እና የአ/አ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ መ/ቁ/215321

መ/ር ሙሴ አሳየኸኝ የሰበር እና የአ/አ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ መ/ቁ/215321

ጉዳዩ በአስተዳደር አካል የወጣ መመሪያ አግባብነት በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2013 መሠረት እንዲከለስ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡

ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበዉ አቤቱታ ተጠሪ ነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም ያወጣው የትምህርት አመራሮች ድልድል መመሪያ ህግን ባልተከተለ መልኩ ስለወጣ መመሪያው ተፈፃሚ እንዳይሆን እና እንዲከለስ የሚል ነዉ፡፡የአቤቱታ ይዘትም አመልካች የአለም ብርሃን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ-መምህር በመሆን ታህሳስ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በፌደራል ደረጃ በወጣው የመምህራን እና ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘር የስራ መደብ የድልድል አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 2/2012 መሰረት አድርጎ ጄ.ጂ.ኤ ጥናት አንቀጽ 9 መሰረት ያለውድድር ከነበረበት ርዕሰ መምህር ኬሪየር በደረጃ 18 ተመድቦ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡መልካም ንባብ…..

First34568101112Last