ፊዳ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበርየሰበር እና አቶ ፋሲካ መርሻ መዝገብ ቁጥር 215158

ፊዳ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበርየሰበር እና አቶ ፋሲካ መርሻ መዝገብ ቁጥር 215158

ጉዳዩ ተጠሪ ከአመልካች ማኀበር ለመውጣት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ በዚሁ አግባብ ተውስኖ ከማህበሩ ሲወጡ የሚከፈላቸውን ድርሻ ለማጣራ የሂሳብ አጣሪ ተሹሞ ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ/ም የቀረበው ሪፖርት ስህተት አለበት ተብሎ እንደገና ተስተካክሎ በቀረበው ሪፖርት ላይ ግራቀኙ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን አመልካች በአስተያየታቸው ተከፈለ የተባው የማኀበሩ ዕዳ በተጠሪ የተከፈለውን እንጅ በአመልካች የተወሰደው የብድር ገንዘብ በሪፖርቱ አለመካተቱንና ብድሩን ለመውሰድ የተያዘውን ቃለ ጉባኤ ተጠሪ ወስድው ያልመለሱ ሲሆን መውሰዳቸውን ያመኑበት ቃለ ጉባኤ ቀርቦ ሳይጣራ ሂሳቡ መሰራቱ ፍትሐዊ አይደለም በማለት ተቃውሞ አቅርበዋል፡፡ የሂሳብ አጣሪው በቀረበው ቅሬታ ላይ በሰጠው ማብራሪያ በአመልካች የቀረበው ሰነድ በአመልካች ብቻ የተፈረመ ፣ ተጠሪ ያልፈረሙበት የተሟላ ሕጋዊ ሰነድ ባለመሆኑ በሂሳብ ማጣራቱ አለመካተቱን አስረድተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም በአመልካች ለሂሳብ አጣሪው የቀረበው ሰነድ በግራቀኙ ያልተረጋገጡ በመሆኑ ሂሳቡን ለመሥራት እንደህጋዊ ሰነድ ሊያቀርቡ የማይችሉ በሂሳብ አሰራር ደንብ ተቀባይነት የሌላቸው ሰነዶች በመሆናቸው በሂሳብ አጣሪው ተቀባይነት ማጣቱ አግባብ ነው በማለት የአመልካችን ቅሬታ ውድቅ በማድረግ የቀረበው የሂሳብ ማጣራት ሪፖርት በማጽደቅ ተጣርቶ በቀረበው ሪፖርት መሠረት የተጠሪ ድርሻ ብር 42,788.5(አርባ ሁለት ሺ ሰባት መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር ከ5/100) እንዲከፈላቸው የወሰነ ሲሆን ፣ አመልካች በውሳኔው ባለመስማማት ያቀረቡት ይግባኝ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረዙ በፍርዱ መግቢያ ላይ የተመለከተውን የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

አቶ ገብሬ ሽፈራው እና ወ/ሮ እሌ ገበየሁ የሰ/መ/ቁ 2215096

አቶ ገብሬ ሽፈራው እና ወ/ሮ እሌ ገበየሁ የሰ/መ/ቁ 2215096

ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ ከሳሽና ተከሳሽ በባልና ሚስትነት አብረን ስንኖር ተማሪ ጌጤ ገብሬ እድሜ 16፣ ተማሪ ጥሩ አየሁ እድሜ 14፣ ተማሪ አማረ ገብሬ እድሜ 10 የሆኑ ልጆች ወልደን ሀብት አፍርተን መግባባት ባለመቻላችን በሽማግሌ ከፊል ሀብቴን አካፍሎ ከፊሉን ከልክሎኛል፤ ስለሆነም አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰውን መሬት እንዲያካፍለኝ ፣ የፍልጥ ባህር ዛፍና ጌሾ በግምቱ መሰረት እንዲያካፍለኝ፣ 100 ዚንጎ የገጠር ቆርቆሮ ቤት ግምቱ 33,000.00 (ሰላሳ ሶስት ሺህ) ከሆነው ከግማሽ ድርሻየ ላይ ብር 13,000.00 (አስራ ሶስት ሺህ) የሰጠኝ ሲሆን ቀሪ ብር 3500.00 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ) እንዲከፍለኝ፣ እንዲሁም የልጅ ቀለብ እንዲከፍል እንዲወሰን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…..

የኢትዮጵያ ኤርፖርት ጎንደር አፄ ቴወድሮስ ኤርፖርት አስተዳደር እና አዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ የገቢዎች ጽህፈት ቤት የሰ/መ/ቁጥር 214756

የኢትዮጵያ ኤርፖርት ጎንደር አፄ ቴወድሮስ ኤርፖርት አስተዳደር እና አዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ የገቢዎች ጽህፈት ቤት የሰ/መ/ቁጥር 214756

ጉዳዩ የቦታ አገልግሎት ግብርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በጎንደር ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ መልካም ንባብ…..

አቶ ገዛሄኝ ጉታ እና አቶ ማርቆስ ባልቻ የሰ/መ/ቁጥር 214389

አቶ ገዛሄኝ ጉታ እና አቶ ማርቆስ ባልቻ የሰ/መ/ቁጥር 214389

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 376464 ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 343284 ሚያዝያ 19 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ፣ የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 34778 መጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የደንዲ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 65240 የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው፡፡ ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የውርስ ንብረት በፍ/ቤት በውርስ አጣር ሳይጣራ እና ክፍፍል ሳናደርግበት ተከፋፍላችኋል ተብሎ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ……. 

ዳቫል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ወ/ሮ ሐይማኖት መራ የሰ/መ/ቁጥር 214291

ዳቫል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ወ/ሮ ሐይማኖት መራ የሰ/መ/ቁጥር 214291

ጉዳዩ የይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩ በተጀመረበት አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ይልማና ዴንሣ ወረዳ ፍርድ ቤት አመልካች ከሣሽ ተጠሪ ደግሞ ተከሣሽ ነበሩ፡፡ አመልካች የካቲት 24ቀን 2012ዓ/ም በተፃፈ ክሱ በእጁ አድርጎ በሚጠቀምበት ስምንት ቃዳ ይዞታው ውስጥ ተጠሪዋ ከ2003ዓ/ም ጀምሮ የግንባታ ፈቃድና የይዞታ ማረጋጫ ሣይኖራት በ75 ካሬ ሜትር ላይ በ12ዚንጎ ቆርቆሮ የተሰራ ቤት ስርታ የአልኮል መጠጦችን፣ ምግቦችንና ልዩ ልዩ ሸቀጣቀጦችን እየሸጠች የመማር ማስተማሩን ስራው ላይ ችግር እየፈጠረችበት ለትምህርት ቤቱ ገቢ የሚያስኝ ይዞታውንም የያዘችበት መሆኑን በመዘርዘር ይዞታው በአንድ አመት የሚያስገኘውን የሳር ግምት በአመት መቶ ብር ሆኖ የዘጠኝ ዓመት በድምሩ 900 ብር ከፍላ ቤቱን አፍርሣ እንድትለቅ እንዲወሰንባት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ…….

First45679111213Last