አቶ መንገሻ መሮ እና እነ መ/ር መስፍን መንገሻ (2ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 258429 አቶ መንገሻ መሮ እና እነ መ/ር መስፍን መንገሻ (2ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር 258429 በአመልካቾች የይግባኝ አቤቱታው የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤትም ተጠሪዎች ከወላጆቻቸው ይዞታ በመውሰድ በራሳቸው ጉልበት እና ገንዘብ ያለሙ እና ለምርትም ሲደርስ ለአመልካች እና ባለቤታቸው እኩል በማካፈል በጋራ ሲጠቀሙ የነበሩ በመሆናቸው እንዲሁም የቤተሰብ አባል በመሆን በቤተሰብ በተመዘገበ ይዞታ ላይ እየተጠቀሙ የነበሩ በመሆናቸው የመጠቀም መብታቸው ቀሪ ሊሆን እና ያፈሩትንም ንብረት ሊያጡ አይገባም፣የስር ፍ/ቤቶችም ተጠሪዎች በይዞታው ላይ መብት የላቸውም በማለት የሰጡት ውሳኔ ተጠሪዎች በይዞታው ላይ ካላቸው መብት እና የቤተሰብ አባልነት አኳያ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውም ይዞታው ላይ የሚገኝ ቡና እና ኮረሪማ ባልና ሚስቱ ሊካፈሉ አይገባም፣አመልካች እና ባለቤታቸው ከተጠሪዎች ጋር በጋራ ሊጠቀሙ ይገባል በሚል ወስኗል፡፡ አመልካችም የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በሚል ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡ ሲሆን አቤቱታው የቀረበለት ችሎትም ውሳኔው የህግ ስህተት አልተፈጸመበትም በማለት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ አመልካችም ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ በአጭሩ ተጠሪዎች በውል ወይንም በውርስ ያገኙት የይዞታ ባለቤትነት መብት ሳይኖራቸው መከራከራቸው በህገ መንግስት አንቀጽ 40/7/8 የተቀመጠውን መብት ጥሰት ነው፡፡ተጠሪዎች መሬቱን ከ2000 ዓ.ም ጀምረው አልምተውታል ቢባል እንኳን አባታቸውን ስላገዙ የባለቤትነት መብት አይሰጣቸውም፡፡የክርክር መነሻ የሆነውን ይዞታ ያገኘሁት በአዋጅ ቁጥር 110/99 መሰረት አርሶአደር በመሆኔ ሲሆን ተጠሪዎች የከተማ ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞች በመሆናቸው በውርስም ከሆነ ከሞትኩ በኃላ የሚፈፀም ይሆናል እንጂ በህይወት እያለው ይዞታውንና ንብረቱን ሊካፈሉ አይችሉም በሚል የተሰጠው ውሳኔ እንዲታረም ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…
እነ ወ/ሮ ተናኜ ሞላ ብርሐኔ(3ሰዎች) እና አቶ ሳሙኤል ተገኝ ኃይሌ የሰበር መዝገብ ቁጥር - 257774 እነ ወ/ሮ ተናኜ ሞላ ብርሐኔ(3ሰዎች) እና አቶ ሳሙኤል ተገኝ ኃይሌ የሰበር መዝገብ ቁጥር - 257774 ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በስር ፍርድ ቤት አመልካቾች ተጠሪዎች ተጠሪ ደግሞ አመልካች በመሆን ተከራክረዋል፡፡በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካቾች ላይ ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ ወላጅ አባት ሟች አቶ ኃይሌ ተገኝ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ኑዛዜ የፈፀሙ መሆኑን አመልካች የሟች ብቸኛ ልጅ መሆኑን ለተጠሪዎች ኑዛዜ በመፈፀም ከሚደርሰው ድርሻ ከሩብ በላይ ጉዳት እንዲደርስበት ያደረገ በመሆኑ ከኑዛዜው እንድነቀል ተደርጊያለሁ ስለዚህ ሟች ፈፀመውታል የተባለው ኑዛዜ እንዲሻርልኝ የሚል ነው፡፡ ከአመልካቾች በኩል የተሰጠው መልስ በአጭሩ ኑዛዜው በህግ ፊት የፀና ነው ሟች ማንም ሰው ሳያስገድዳቸው በራሳቸው ፍቃድና ፍላጎት በትክክለኛ አእምሮ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ፊት ቀርበው የኑዛዜው ሰነድ ተነቦላቸው በምስክሮች ፊት የቁም ኑዛዜ ያደረጉ ስለሆነ ኑዛዜው ህጋዊ መሆኑን ሟች ጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረጉት የቁም ኑዛዜ በተራ ቁጥር 2፣ 3 እና 4 የተጠቀሱት የኑዛዜ ተቀባዮች በሟች ስም የሚጠሩ መሆናቸውን ኑዛዜ አድራጊው ልጆች ናቸው ብሎ የተቀበላቸውን ግለሰቦች 3ኛ ወገን ተወላጆች ስላልሆኑ የኑዛዜ ስጦታ ሊበረከትላቸው አይገባም ብሎ መከራከር የሟችን በንብረቱ ላይ የማዘዝ መብትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የኑዛዜ ተቀባዮች ተወላጆች አይደሉም ቢባል እንኳን የኑዛዜ ስጦታ ለተወላጅ ብቻ የሚሰጥ መብት ነው የሚል የህግ ድንጋጌ ያለመኖሩን አመልካች ሟች አባታቸው ባደረጉት ኑዛዜ የኑዛዜ ተቀባይ ነው እንጂ በኑዛዜው ከውርስ አልተነቀለም፡፡ አመልካች ከጠየቁት ዳኝነት አንፃር በኑዛዜው የሚደርሳቸውን ድርሻ በትክክል ለይተው አልጠየቁም የሟች ቁም ኑዛዜ ፈራሽ የሚሆንበት በቂ ምክንያት ስላልቀረበ የአመልካች ክስ ውድቅ እንዲደረግ የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…
ወ/ሮ ሰላማዊት ያደሳ እነ አቶ ፀሀዬ ጌታቸው(2ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 256923 ወ/ሮ ሰላማዊት ያደሳ እነ አቶ ፀሀዬ ጌታቸው(2ሰዎች) የሠ/መ/ቁጥር 256923 ጉዳዩ አመልካች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር እንደባልና ሚስት አብረዉ በኖሩበት ጊዜ ያፈራነዉ ንብረት ነዉ ያሏቸዉን ንብረቶች ለመካፈል ያቀረቡት ክስ አስቀድሞ ዉሳኔ ባገኘ ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበ ክስ ነዉ በሚል ዉድቅ በመደረገ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል በቀረበ የሰበር አቤቱታ መነሻ የተደረገዉን ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በ1ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ የአሁን 2ኛ ተጠሪ ጣልቃ በመግባት የተከራከሩ ሲሆን የክሱ ይዘት በአጭሩ - ከ1ኛ ተጠሪ ጋር ከቀን 15/04/1999 ዓ.ም ጀምሮ እንደባልና ሚስት አብረን ስንኖር ያፈራነው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ክልል ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 121 የይዞታ መለያ ቁጥር AA000070806106 የሆነና በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ስፋቱ 403 ካሬ ሜትር የሆነ 8 የሚከራዩ ሰርቪስ ቤቶች እና 4 ክፍል ያለው ዋና ቤት እና ቦታ የጋራ ሀብት ስለሆነ ተጠሪ ድርሻዬን እንዲያካፍለኝ በማለት ሌሎች ንብረቶችንም እንደዚሁ በመጥቀስ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ መልካም ንባብ…
እነ አቶ ዮሐንስ ገ/ሚካኤል(5ሰዎች) እና ወ/ሮ ሃና ደርሶልኝ(2ሰዎች) የሰበር መዝገብ ቁጥር - 256463 እነ አቶ ዮሐንስ ገ/ሚካኤል(5ሰዎች) እና ወ/ሮ ሃና ደርሶልኝ(2ሰዎች) የሰበር መዝገብ ቁጥር - 256463 አመልካቾች ሚያዚያ 2 ቀን 2015 ዓ.ም በተፃፈ የመቃወም አቤቱታ ሟች አባታቸው አቶ ገ/ሚካኤል ኃ/ማርያም በህይወት እያሉ እንዲሁም አባታቸው ከሞቱ በኃላ በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ የሆኑት፣ አመልካቾችና የ 96 አመት የሆኑት የግራ ቀኙ እናት ጋር በአልኮልና በለስላሳ ማከፋፈያ እንዲሁም በሸቀጣሸቀጦች ጅምላ ንግድ ስራ ተሰማርተው በቁጥር ስምንት የሆኑ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች፤ ደምቢዶሎ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ሆቴል፣ የቡና ማበጠሪያ፣ የመጠጥ ማከፋፈያ፣ የመኖሪያ ቤትና መጋዘን፤ በቡና ግብይት ላይ የነበረ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ብር፣ በአዋሽ ባንክ ያለ 50 የአክስዮን ድርሻ በጋራ ያፈሩ መሆኑንና ተጠሪዎች ጋብቻ ሲፈፅሙ እነዚህ ንብረቶች የአመልካቾች መሆናቸውን በጋብቻ ውላቸው ተስማምተዋል፡፡ እነዚህ ንብረቶች ከፊሎቹ ባሉበት ከፊሎቹ በሽያጭ ሆነ በሌላ መንገድ እየተለዋወጡና እየተቀላቀሉ ብዛታቸው 16 የሆኑ በተጠሪ ስም የተመዘገቡ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፤ በተጠሪ ስም የተመዘገቡ በአዋሽ ባንክ፣ በኦሮሚያ ባንክ፣ በህብረት ባንክ ያሉ አክስዮኖች፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በአዋሽ ባንክ፣ በህብረት ባንክ፣ በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፣ በኦሮሚያ ባንክ ተጠራቅሞ የሚገኝ ገንዘብ እና ተሸከርካሪዎች በቤተሰብ የተፈሩና በተጠሪዎች የጋብቻ ውል ላይም የቤተሰብ ንብረቶች መሆናቸው ተረጋግጦ እያለ ተጠሪዎች ከዚህ በተቃራኒ በሰበታ ከተማ የሚገኘውን በ 612 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ቤት፣ በቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት እንዲሁም በዚህ ከተማ በ 2,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሆቴል ን በመተው ሌሎችን ንብረቶች የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ነው በማለት ያስወሰኑ በመሆኑ ውሳኔው ቀሪ እንዲሆን በማለት የመቃወም አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ…
ቻይና ኮሙኒኬሽን ኩባንያ ግንባታ ወንጪ ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት እና ማንዴሳ ጪብሳ የሠ/መ/ቁጥር 256412 ቻይና ኮሙኒኬሽን ኩባንያ ግንባታ ወንጪ ደንዲ ኢኮቱሪዝም ፕሮጀክት እና ማንዴሳ ጪብሳ የሠ/መ/ቁጥር 256412 ጉዳዩ የጉዳት ካሳ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ በተከሳሽነት ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ፡- አመልካች ከደንዲ ሀይቅ እስከ ወንጪ ሀይቅ ያለው መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ኮንትራክተር በመሆን በሚሰራበት ወቅት በደንዲ ወረዳ ገ/ጥራንጉ ሹቤሶሌ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከሚገኘው ስፋቱ አራት ሄክታር በሆነው የእርሻ ይዞታዬ ላይ መንገድ ለመገንባት የቆፈረውን አፈር ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በተሸከርካሪዎች ጭኖ በመድፋት በመሬቱን ገደላማ በማድረግ ከጥቅም ውጪ በመሆኑ በመሬቱ ላይ ተዘርቶ የነበሩትን የሰነፍ ቆሎ፤ገብስ እና ሚስር ቡቃያዎችን፤ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ በቁጥር 5,900.00(አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ባህር ዛፍ፤10 እግር ጥድ፤እንዲሁም 900 እግር ቀርከሃ ስላወደመብኝ የእጽዋቶቹ እና የሰብል ግምቱ ለወደፊት ያገኙ የነበረውን የ15 አመት ጥቅም በድምሩ ብር 9,823,000 (ዘጠኝ ሚሊየን ስምንት መቶ ሃያ ሶስት ሺ) የጉዳት ካሳ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት ከሰዋል፡፡መልካም ንባብ…