አነ አቶ ጳውሎስ ኦርጂኖ እና አቶ ተስፋዬ ኤጌዶ የሰበር መ/ቁ/215762

አነ አቶ ጳውሎስ ኦርጂኖ እና አቶ ተስፋዬ ኤጌዶ የሰበር መ/ቁ/215762

ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ውል አፈጻጸም የሚመለከት ጉዳይ ነዉ፡፡የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ፡- ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን በአሁኑ አመልካቾች ላይ ባቀረበው ክስ አመልካቾች በዱራሜ ከተማ ውስጥ በ460.6 ካ.ሜ ላይ ያላቸውን መኖሪያ ቤት በብር 2,250,000.00 በቀን 24/01/2012 ዓ.ም በተደረገው ውል ሽጠውልኝ ቀብድ ብር 1,000,000 መቀበላቸዉን እንዲሁም የተጠሪ ወኪል በ1ኛ አመልካች የባንክ ሂሳብ ብር 800,000.00 ገቢ በማድረጋቸው በአጠቃላይ ብር 1,800,000.00 የተቀበሉ መሆኑን ገልጾ አመልካቾች በውሉ መሰረት ቤቱን እንዲያስረክቡ እንዲወሰን ይህ ካልሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ.1885(2) መሰረት የተቀበሉትን ቀብድ አጠፌታ እና ገንዘቡ ተከፍሎ እስከሚያልቅ ህጋዊ ወለድ ከወጪና ኪሳራ ጋርእንዲከፍሉ እንዲወሰን በማለት ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን አመልካቾች በበኩላቸዉ ባቀረቡት መልስ የቤት ሽያጭ ውል ሲደረግ ቀብድ መሆኑ በውሉ ስላልተገለጸ ቀብድ ነው በሚል አጠፌታ መጠየቅ ተገቢ ስላለመሆኑ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 26996 አስገዳጅ የህግ ትርጉም መስጠቱን፤በውልም ሆነ በወኪላቸው ገንዘብ ያልተቀበሉ ከመሆኑም በላይ የሽያጭ ውሉ በሚመለከተው አካል ፊት ያልተደረገ እና ያልተመዘገበ የማይፀና ረቂቅ ውል በመሆኑ ቤቱን የማስረከብ ግዴታ የለብንም፣የቀብድ ውል የሌለና የባንክ ሰነድ ቀብድ መሆኑን የሚገልጽ አይደለም፣ክሱ ውድቅ እንዲደረግ በማለት መከራካራቸዉን መዝገቡ ያሣያል፡፡ መልካም ንባብ…..

ዳግም አከበረኝ ከ ፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ

ዳግም አከበረኝ ከ ፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ

የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ ቻለው አመልካች ሐምሌ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ 284716 ሠኔ 19 ቀን 2012 አመልካች የተከሰሰነት የወንጀል ሕግ ከ15 ዓመት እስከ 25 ዓመት ፅኑ እሥራት የሚያስቀጣ በመሆኑ በዋስ ቢወጣ ወንጀሉ ከሚያስከትለው ቅጣት ሙሉ በሙሉ እንደማይቀርብ ፍ/ቤቱ ግምት ስለወሰደ የዋስትና መብቱ ወንጀሉ ከሚያስከትለው ቅጣት ሙሉ በሙሉ እንደማይቀርብ ፍ/ቤቱ ግምት ስለወሰደ የዋስትና መብቱ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67/ሀ መሠረት ተነፍጓል በማለት የሰጠው ትዕዛዝ፣ይህንኑ ትዕዛዝ በማፅናት የፌደራል ደፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ 255442 ሐምሌ 21 ቀን 2012 ዓ.ም ሰጠው ፍርድ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው::

እነ አቶ ወድወሰን ታደሰ ይስማ ከ የለም

እነ አቶ ወድወሰን ታደሰ ይስማ ከ የለም

ኢትዮጵያዊ እናት እና አባት የሆኑት 1ኛ እና 2ኛ አመልካቶች በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት አሜቲካዊ የሆኒት የ2ኛ አመልካች እህት 3ኛ አመልካች የ1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ልክ የሆነችውን ተማሪ ኤፍራታ ወንደሰን ቤተሰብ የሚያደርገውን ሁሉ ከልጅነቷ ጀምሮ ካለችበት ሀገር ሆና ስትንከባከባት የነበረች እና በምትኖርበት ሀገርም ልጇ መሆኗን የተለያዩ ፈርሞችን መሙላቷን አንስተው በአመልካቾች መካከል ተደረገው የተማሪ ኤፍራታ ወንደሰን የጉዲፈቻ ስምምነት እንዲፀድቅላቸው ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱ በመዝገብ ቁጥር 103957 በ2/11/2011 በዋለው ችሎት የውጭ ሀገር ጉዲፈቻ በአዋጅ ቁጥር 103957 የተከለከለ ነው በማለት አቤቱታውን ባለመቀበል ትዕዛዝ ሰጥቷል ፡፡

አቶ አወል አህመድ ከ እነ አቶ አምባቸው በለጠ

አቶ አወል አህመድ ከ እነ አቶ አምባቸው በለጠ

ጉዳዩ የጉዳት ካሳን መነሻ ያደረገ ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ እንዲሁም 2ኛ ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ከክርክሩ እንደተረዳነዉ 1ኛ ተጠሪ በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረተዉ ክስ 1ኛ ተጠሪ በቀን 24/07/2009 ዓ/ም ጠዋት 3፡00 ሰዓት በኦሮሚያ ክልል አስቦት በተባለ አካባቢ አሰሪዉ ስተን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የአሁን አመልካችን የነዳጅ ማደያ ሲሰራ የዚህ ማህበር ሰራተኛ በመሆን እየገነባ ሳለ በአሁን 2ኛ ተጠሪ የተዘረጋ ከባድ የኤሌክትሪክ ሀይል ማስተላለፊያ ገመድ
 

አቶ እዶሳ አብዲሳ ከ እነ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን

አቶ እዶሳ አብዲሳ ከ እነ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን

ይህ ወራሽ የሌለዉ የዉርስ አክስዮን ድርሻ ክርክር የተጀመረዉ በፌዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.167717 ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ  እንዲታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ።

123