እነ አቶ በሀይሉ ንጉሴ እና እነ ወ/ሮ ሞሲት መኮንን የሰ/መ/ቁ 217975 እነ አቶ በሀይሉ ንጉሴ እና እነ ወ/ሮ ሞሲት መኮንን የሰ/መ/ቁ 217975 አመልካቾች ባቀረቡት ክስ በሟች አባታችን አቶ ንጉስ መኮንን ተተክተን ከሟች አያታችን እማሆይ ፈንቴ ሃይሉ በውርስ የሚተላለፍ በተለያየ ቦታ የሚገኝ በጠቅላላው 7.5 ጥማድ መሬት ውስጥ ተጠሪዎች የሟች አባታችንን ድርሻ 2.5 ጥማድ መሬት ጭምር በራሳቸው ስም አዙረው በመያዝ የከለከሉንና ሊያካፍሉን ፈቃደኛ ያልሆኑ በመሆናቸው ድርሻችንን እንዲያካፍሉን ይወሰንልን በማለት የመሬቱን አዋሳኝ ጠቅሰው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ……..
ፀሀይ ደረጃ 1 ሀ ድንበር ተሻጋሪ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች መህበር እና ኪንግ ሳምተስ ንግድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሰ/መ/ቁጥር 215000 ፀሀይ ደረጃ 1 ሀ ድንበር ተሻጋሪ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች መህበር እና ኪንግ ሳምተስ ንግድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሰ/መ/ቁጥር 215000 የአመልካች መኪኖች ጭነቱን ጭነው በአዳማ ጉምሩክ ከ6 እስከ 12 ቀናት በመቆማቸው ጉዳት/ዲመሬጅ ደርሷል፡፡ ይህ ጉዳት የሚሰላው በአዋጅ ቁጥር 811/2006 አንቀፅ 4(1) መሰረት ተሽከርካሪው ደርሶ ለማራገፍ ከተመደበው 8 ሰዓት ውጪ በቀጣይ ያሉት ቀናት ሙሉ በሙሉ ኪሳራ የሚታሰብባቸው ናቸው፡፡ በመሆኑም በአዋጁ አንቀፅ 7(1)(ሀ)(3)(5) መሰረት ከሳሽ ባሰማራቸው ተሽከርካሪዎች ብዛት በድምሩ ብር 300,000 ገንዘቡ መከፈል ከነበረበት ህዳር 20 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ወጪ እና ኪሳራ ጭምር እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ ……..
እነ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ማስረሻ እና አቶ ኃ/ማርያም ወዳጆ የመ.ቁ.220108 እነ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ማስረሻ እና አቶ ኃ/ማርያም ወዳጆ የመ.ቁ.220108 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ሰበር ችሎት ሐሰተኛ ቃለ-መሐላ አቤቱታ ያቀረቡ ባለጉዳይን በችሎት መድፈር ጥፋተኛ ናቸው በማለት ሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ቀላል እስራት እንዲቀጡ ወሰነ፡፡ ፍርድ ቤቱ በእስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው አቶ ኃይለማርያም ወዳጆ በደሀ ደንብ መስቀልኛ የሰበር አቤቱታ ለማቅረብ የዳኝነት ለመክፈል ምንም ሀብት እና ንብረት የሌላቸውና በቀበሌ ቤት የሚኖሩ መሆኑን በቃለ-መሐላ በማረጋገጥ አቤቱታቸውን በሀሰተኛ መንገድ በማቅረባቸው ነው፡፡ መልካም ንባብ ………
ግሩም ሆስፒታል ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ዶ/ር ተስፋዬ አልማው የሰ/መ/ቁ. 219386 ግሩም ሆስፒታል ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ዶ/ር ተስፋዬ አልማው የሰ/መ/ቁ. 219386 ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአመልካች ሆስፒታል ውስጥ በኤክስፐርት ሜዲካል ስፔሻሊስት (ሰርጀሪ) የስራ መደብ ላይ በወር ብር 49,000.00፣ ሃርድሺፕ አሎዋንስ 19,124.00፣ እንዲሁም ለእያንዳንዱ የቀዶ ጥገና ህክምና ብር 1,000.00 እየተከፈላቸዉ ከቀን ግንቦት 07 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ አመልካች የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ የሁለት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት ከስራ ከህግ ውጪ ከስራ ያሰናበታቸዉ መሆኑን ጠቅሰዉ የተለያዩ ክፍያዎች እንዲከፈላቸዉ ይወሰንላቸዉ ዘንድ የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡መልካም ንባብ……
እነ አቶ ኃብተወልድ ተከተለው እና ህዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የሰበር መ/ቁ/ 218918 እነ አቶ ኃብተወልድ ተከተለው እና ህዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የሰበር መ/ቁ/ 218918 ጉዳዩ የደረጃ እድገት የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደ/ብርሃን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካቾች ከሳሽ በመሆን በአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረበቡት ክስ ተጠሪ ሚያዝያ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ባወጣው የደረጃ እድገት እና የዝውውር ማስታወቂያ ለመወዳደር በተለያየ ስራ መደብ ላይ ተመዝግበን የነበርን ቢሆንም ተጠሪ ግን የአከባቢ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ የስራ መደብ ላይ ብቻ የደረጃ እድገት አወዳድሮ ተፈፃሚ ያደረገ ሲሆን አመልካቾች ለመወዳደር ከተመዘገብንበት መደብ ላይ ያለ አግባብ ከደረጃ እድገት እና ዝውውር መታገዳችን ህገወጥ በመሆኑ በደረጃ እድገቱና ዝውውሩ ላይ ተሳታፊ እንዲንሆን ውሳኔ ይሰጥልን በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ……..