የአሁን ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በአሁን አመልካች ላይ ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 693(1)ን በመተላለፍ በቀን 20/03/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በሀዋሳ ከተማ መሃል ክፍለ ከተማ ንጋት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ልዩ ቦታው አረብ ሰፈር በሚባልበት ከግል ተበዳይ ሉቻ ተክሉ የምትነግድበት ሥራ ቦታ ድረስ በመሄድ በኦሮሚያ ክልል እና ሲዳማ ክልል የቢሮ ዕቃዎች ለማስገባት ጨረታውን ስላሸነፍኩ ብር ቸግሮኛል በጋራ እንሰራለን ብር አበድሪኝ በማለት በተለያየ ቀን ዕቃዎችን ለመግዛት ብሎ በካሽ እና በአካውንት የወሰደውን ብር በንግድ ባንክ በሁለት ግዜ እንዲከፈል ሲል ቼክ ቁጥር BC19664274 በሆነው 1,600,000 (አንድ ሚሎዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር) ቀን 30/3/2013 ዓ.ም ጽፎ የሰጠ በመሆኑ እንዲሁም በቼክ ቁጥር BC19664275 በሆነው 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) በቀን 15/4/2013 ዓ.ም ጽፎ በመስጠት በአጠቃላይ ብር 3,100000 (ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ብር) የሚሆን በአመልካች ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ ውስጥ በቂ ገንዘብ እንደሌለ አጣርቶ መረጃ የተሰጠ በመሆኑ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በማዘዙ ተከሷል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…….