ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 271726

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 271726

ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁጥር 249795 ላይ “ሠራተኛዉ በተከታታይ ከ5 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ቢቀር እንኳ ከሥራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን አሠሪዉ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) ሳይሰጥ የሥራ ዉልን ለማቋረጥ እንደማይችል” ተገልጾ የተሰጠው የህግ ትርጉም ተለውጦ “የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27(1)(ለ) ድንጋጌ ሠራተኛዉ በዚሁ አዋጅ ከተመለከቱ እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ዉጭ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከሥራ ላይ ከቀረ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ (Warning in Writing) መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ዉልን ያለ ማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ይቻላል” በሚል ተተርጉሟል፡፡ 

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 244308

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔ: መዝገብ ቁጥር 244308

  1. ጉዳዩ በከተማ ክልል የሚገኝ መሬት ይዞታ መብት ለማስከበር የቀረበ ክስ የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡ ተጠሪ በ14/11/2013 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ስሙ ፊጋ በሚባል ሰፈር አዋሳኞቹ በክስ የተገለፀውን ግምቱ 2000 ካ.ሜ የሆነ የእርሻ መሬት ከደርግ መንግስት ጀምሮ ተገቢውን የመሬት ግብር በመክፈል ስጠቀምበት የቆየሁትን የእርሻ መሬት ለ11 ዓመት ውጭ ሀገር ቆይቼ ግንቦት 2012 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት ስመለስ ይዞታዬን እንዲያስተዳድሩልኝ ተወካይ አስቀምጬ እያለ አመልካች ምንም ህጋዊ መብት እና የውል ግንኙነት ሳይኖረው ግምቱ ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ) የሆነውን ያጠርኩትን አጥር ሰኔ ወር 2011 ዓ.ም በማፍረስ ተወካዬንም ከይዞታው በማባረር ግንብ አጥር በማጠር ቤት ሰርቶ በሕገወጥ መንገድ ይዞታዬን የያዘብኝ በመሆኑ ያለፈቃዴ የገነባውን ቤትና አጥር አፍርሶ በፍ/ሕ/ቁ 1206 መሰረት ይዞታዬን ለቆ ያስረክበኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡
ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠ የህግ ትርጉም

ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠ የህግ ትርጉም

በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ አስተዳደራዊ ተግባርን ለማከናወን በተሰማሩ ሰራተኞች የሚነሱ  የስራ ክርክሮችን በተመለከተ ፍርድ ቤቶች የስራ ክርክሩን ተቀብለው አከራክረው ለመወሰን ህጋዊ የዳኝነት ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ ትርጉም ተሰጠ

በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26 ስር እንደተደነገገው አምስት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት የተሰጠን ትርጉም በተለያዩ ምክንያቶች ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከሰባት ያላነሱ ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት እንዲታይ እንደሚደረግ እና በዚህ መልኩ የሚሰጠው የህግ ትርጉም ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በማናቸውም ደረጃ ለሚገኝ የፌደራል ወይም የክልል ፍርድ ቤት አስገዳጅ እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡ 

በዚህ መሰረት ከዚህ ቀደም በሰ/መ/ቁ 234706 “በሲኖዶስ ትዕዛዝ መሰረት እንደ ተጠሪዎች ያሉ አካላት ካልተፈጸሙ ባላቸዉ አሠራር መሰረት በአስተዳደር ረገድ እንዲፈጽሙ ከሚደረግ በቀር ተጠሪዎች በፍርድ ተገደዉ ውዝፍ ክፍያ እንዲፈጽሙ፣ ….. የሚወሰንበት አግባብ የለም፤ የስር ፍርድ ቤቶችም ይህንኑ መሰረት አድርገው በፍ/ብ/ስ/ስህግ ቁጥር 9(1) እና 231(1/ለ) መሰረት መዝገቡን መዝጋት አለባቸው” በማለት የተሰጠው ትርጉም በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 26 መሰረት  በሰበር መዝገብ ቁጥር 265878 ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ/ም ሰባት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ችሎት ተለውጦ ‹‹በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ አስተዳደራዊ ተግባርን ለማከናወን በተሰማሩ ሰራተኞች የሚነሱ የስራ ክርክሮችን በተመለከተ ፍርድ ቤቶች የስራ ክርክሩን ተቀብለው አከራክረው ለመወሰን ህጋዊ የዳኝነት ስልጣን አላቸው›› የሚል ትርጉም ተሰጥቷል፡፡

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎች ልዩ ዕትም ቁጥር 01

ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎች ልዩ ዕትም ቁጥር 01

ከ2002 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰባት (7) ዳኞች በተሰየሙበት ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎችን ያጠቃለለ መጽሐፍ በልዮ ዕትም ለንባብ ምቹ ሆኖ ቀርቧል።

ወ/ሮ የማርውሃ ወርቅነህ እና እነ ወ/ሮ ዓለም ወርቅነህ የሰ.መ.ቁ 242314

ወ/ሮ የማርውሃ ወርቅነህ እና እነ ወ/ሮ ዓለም ወርቅነህ የሰ.መ.ቁ 242314

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ከሳሽ አመልካች ደግሞ ጣልቃ ገብ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪዎች በቀን 11/09/2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ የእናታቸው ወ/ሮ ሸዋነሽ ስመኝ ድልነሳው የውርስሀብት ተጣርቶ እንዲቀርብ አመልክተው አመልካች ወደ ክርክሩ በውርስ ማጣራት ሂደት በጣልቃ ገብነት ገብተው የውርስ አጣሪ ሪፖርቱ ከቀረበ በኋላ ግራ ቀኙ አስተያየት እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡ 1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በሰጡት አስተያየት የሟች እናታችን ውርስ እንዲጣራ በዉርስ አጣሪ ባቀረብነው አቤቱታ ላይ ምስክሮች ቀርበው ይሰሙ በማለት አስተያየት ሰጥተዋል መልካም ንባብ…

1345678910Last