7286
የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ያለፍርድ ቤት ፈቃድ በተወዉ ጉዳይ ላይ የቀረበዉ ክስ ተቀባይነት የለዉም ተብሎ የተሰጠዉን ብይን ለማስለወጥ ነዉ፡፡የክርክሩ መነሻ የቤት ሽያጭ ውል የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ላይ የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ተጠሪ ከሟች ባለቤታቸው አቶ ተሾመ አፈወርቅ ጋር በመሆን በቀን 06/12/1996 ዓ.ም በአ/አ/ከ/ቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 047 የካርታ ቁጥር ሴ.ኬ.አሲ/02/31/1229/001040/01 የሚታወቅ መኖሪያ ቤት ለአመልካችና ለአቶ ፀጋዬ ገ/መንፈስ ሽጠዋል፣ቤቱን እንዲለቁ ሲጠየቁ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ/153563 ቤትን አንዲለቁልኝ ክስ አቅርቤ ፍ/ቤቱን አስፈቅጄ ያነሳሁት ቢሆንም ተጠሪ ቤቱን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ተጠሪ ቤቱን ለቀው እንዲወጡና እንዲያስረክቡኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋዋል፡፡……………
7671
ጉዳዩ የውርስ ሀብት ነዉ የተባለዉን የመሬት ይዞታ አስለቅቆ ለመረከብ በቀረበ ክስ መነሻ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ተብሎ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካቾች በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ሮቢት ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ ሟች አባታችን እንድሪስ አደም ከባለቤቱ ከስር 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አሊያ አህመድ ጋር በባልና ሚስት በነበሩበት ጊዜ ከ1966 ዓ/ም ጀምሮ ይዘዉ በኋላም በ1989 ዓ/ም በነበረው የመሬት ሽግሽግ በሕጋዊ መንገድ ተደልድሎ የተሰጣቸዉ እና ከ1978 ዓ/ም ጀምሮ ግብር የሚገብሩበት በሸዋ ሮቢት ከተማ 05 ቀበሌ ውስጥ አዋሳኞቻቸዉ በክሱ የተጠቀሰ ልዩ ቦታዉ እስላም ቀብር ተብሎ በሚታወቅበት አካባቢ 2 ጥማድ መሬት፣ልዩ ቦታዉ ንብ እርባታ ተብሎ በሚታወቅበት አካበቢ 1 ጥማድ መሬት እንዲሁም እንስርቱ ዉሃ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ እሩብ ጥማድ መሬት 1ኛ ተከሳሽ ለብቻቸዉ ይዘዉ እየተጠቀሙ ሊያካፍሉን ፈቃደኛ ስላልሆኑ ድርሻችንን እንዲያካፍሉን ይወሰንልን፡፡ እንዲሁም 2ኛ ተጠሪ አለአግባብ ስለያዘብኝ ለቆ እንዲያስረክበን ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡……………….
7470
አመልካች የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባቀረበው ክስ አመልካች የኮምፒዩተር እቃዎችን ለመግዛት ባወጣው ጨረታ ተጠሪ አሸንፎ እቃዎቹን አቅርቦ ክፍያ የተቀበለ ቢሆንም እቃዎቹን ከሰርቨሩ ጋር የሚያገናኙ ኬብሎችን ባለማቅረቡ ምክንያት እቃዎቹ የተፈለገውን አገልግሎት መስጠት አልቻሉም፡፡ በመሆኑም ኬብሎቹን እንዲያቀርብ ወይም በወቅቱ የገበያ ዋጋ የእቃዎቹን ግምት ብር 182,900 ወጪና ኪሳራን ጨምሮ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ተጠሪ የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች እቃዎቹ ጉድለት ያለባቸው መሆኑን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በ1 አመት ውስጥ ክስ ስላላቀረበ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል፡፡…………
6988
መዝገቡ ከቀነ ቀጠሮ በፊት ሊቀርብ የቻለው አመልካች 15/4/ቀን 2014 ዓ.ም በተፃፈ ቃለ መሃላ ስላቀረቡ ነው፡፡ ለዚህ ችሎት 7/4/2014 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ችሎት በመ/ቁ 279892 በ 27/3 /2014 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፆ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ባቀረበው ማመልከቻ መነሻነት ነው፡፡ በዚህ መሰረት መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩን ትአዛዝ ሰጥተናል፡፡……………
6956
መዝገቡ ከቀነ ቀጠሮ በፊት ሊቀርብ የቻለው አመለካች 01/04/2014 ዓ.ም በተፃፈ ቃለ መሃላ አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡ ለዚህ ችሎት 28/03/ቀን 2014 ዓ/ም በተፃፈ አቤቱታ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 193860 በ 23/02 ቀን 2014 የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት መሆኑን ገልፆ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ/ን/ በማለት ባቀረቡት ማመልከቻ መነሻነት ነው፡፡ በዚህ መሰረት መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ትእዛዝ ተሰጥቷል፡፡…………….