Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቀበሌ 11/12/08 ሸማቾች ኃ/የተ/ሕ/ሥ/ማ እና አቶ እንኮሳ አመንቴ ሱፋ(9ሰዎች)የሰ.መ.ቁ 249104

Wednesday, June 4, 2025 2488

የክሱ ይዘት በአጭሩ፡- በየካ አውራጃ ከፍተኛ 16 ቀበሌ 08 የቀድሞው የቀበሌ አመራሮች የተጠሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በማሰብ ከህብረት ሥራ ማህበር ብር 29.000 (ሃያ ዘጠኝ ሺህ ብር) በብድር መልክ ወጪ ተደርጎ ቤት እንድንገነባ ተፈቅዶልን ቤቶቹን በመገንባት የብድር ገንዘብም  ተመልሷል፤ ተጠሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ነዋሪዎች በራሳችን ገንዘብ ቤቶቹን አፍርሰን እንደሰራን በወቅቱ የነበሩ የአመልካች አመራሮች አረጋግጠው በሰነድ ማስረጃ ሰጥተውናል፤ ተጠሪዎች ከ1982/1983 ጀምሮ በሰነድ አልባ በመኖሪያ ቤቶቹን ገንብተን እየኖርን እያለን ከ20 ዓመታት በኋላ አመልካች ለተጠሪዎች ያሰበ በማስመሰል ከፊሎቹን የተጠሪዎች ቤቶች ለልማት ሊፈርሱ ስለሚችሉ የጋራ መኖሪያ ቤት መንግስት እንዲሰጣችሁ እና ቀበሌው እንዲያውቃችሁ በማለት ከሱ ጋር የቤት ኪራይ ውል እንድንዋዋል ሲጠይቀን ተጠሪዎችም የአመልካች ህብረት ሥራ ማህበር አባላት በመሆናቸን እና መንግስታዊ ተቋም ነው ብለን በማመን ከ2ኛ ተጠሪ በስተቀር ከአመልካች ጋር የቤት ኪራይ ውል ልንፈርም ችለናል፤ተጠሪዎች የይዞታ ማረጋገጫ ለመቀበል በሂደት ላይ እያለን አመልካች ከህግም ሆነ ከውል የመነጨ መብት ሳይኖረው እንዳይፈጸም አድርጓል፤ አመልካች ተጠሪዎችን በማታለል ባስፈረመን የኪራይ ውል መነሻነት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኪራዩን ከፍለው ቤቱን ያስረክቡኝ በማለት ክስ አቅርቦ ተጠሪዎች ቤቱን እንድናስረክብ ተወስኗል፤ ሆኖም ከመነሻው ቦታው በጎርፍ ምክንያት ለህይወታችን እስጊ በመሆኑ ልዋጭ ቦታ እንዲሰጠን የሚመለከተውን አካል ጠይቀን ሲሰጠን በቦታው ላይ ቀበሌው ቤት መስራት ካልቻለ ነዋሪዎች በራሳችን ወጪ እንድንሰራ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በራሳችን ወጪ ቤት ገንብተን በስማችን ውሃ፣ መብራት እና መሰል መሰረታዊ አገልግሎቶችን አስገብተን የምንኖርበት ቤት በመሆኑ ቤቶቹ የተጠሪዎች ናቸው ተብሎ ይወሰንልን በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡መልካም ንባብ….

Read more

አቶ ታዬ ከተማ ደጋጋ እናእነ አቶ ሙሉጌታ ታደሰ (3ሰዎች) የሰ/መ/ቁጥር---244417

Wednesday, June 4, 2025 2772

ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የገጠር መሬት ይዞታ ዉርስን የተመለከተ ጉዳይ ሲሆን የተጀመረው በሲናና ወረዳ ፍ/ቤት ነው፡፡ በዚህ ፍ/ቤት 2ኛ ተጠሪ ከሳሽ፤ አመልካች ተከሳሽ ሲሆኑ 1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች እንዲሁም አቶ ጉደታ ሸለማ እና አቶ መርጋ ደበላ ጣልቃ ገቦች ነበሩ፡፡ የሰበር አቤቱታዉ የቀረበዉ የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 33516 መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም የወረዳዉን ፍ/ቤት በማሻሻል የሰጠዉና በየደረጃዉ ባሉት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ችሎቶች በተሰጡ ዉሳኔዎች የጸናዉ ዉሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በሚል ነዉ፡፡መልካም ንባብ…

Read more

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና ብርሃን ባንክ አክስዮን ማህበር ሰበር መዝገብ ቁጥር-242024

Friday, May 30, 2025 1155

ጉዳዩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በተጠሪ ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ ፍሬ ቃሉ በአጭሩ በከሳሽና በተክለ ብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ መካከል የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ውል መዋዋላቸውን ጥር 08 ቀን 2014 አ.ም ሰርቶ እንዲያጠናቅቅ መስማማታቸውን ነገር ግን ስራውን በውሉ መሰረት ባለመስራቱ ከሳሽ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ የስራ ውሉን ያቋረጠ መሆኑን ለተቋራጩ ቅድመ ክፍያ በሁለት ዙር 96,000.00 እና 43,600,173.83 የተከፈለ መሆኑን ተከሳሽ ለቅድመ ክፍያ ዋስትና ብር 89,609,174.04 ለ 2 ዓመት ከ 5 ወር የሚቆይ ዋስትና የሰጠ መሆኑን ተከሳሽ የሰጠው የዋስትና አይነት ጥያቄ እንዳቀርብ የሚከፈል በመሆኑ ተከሳሽ የቅድመ ዋስትና ገንዘብ ብር 89,609,174.02 ከመስከረም 19 ቀን 2012 አ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፍል የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…

Read more

ቢትወደድ ጂማ እና እነ አቶ ሳምሶን መለሰ (2ሰዎች)የሰበር መዝገብ ቁጥር - 245370

Friday, May 30, 2025 3046

ጉዳዩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል የሴደን ሶዶ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪዎች ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ይዘት በምስራቅ ታደሰ ዳቢ፣ በምእራብ እና ደቡብ መንገድ በሰሜን ቢትወደድ ጅማ የሚዋሰን ሁለት ቀርጥ እንዲሁም በምስራቅ አረጋሽ ግራኝ በምእራብ ለኤልጆ ባንቲ በሰሜን ታደሰ ዳቢ እና በደቡብ መዲና ሰኢድ የሚያዋስኑት ሁለት ቀርጥ በተጨማሪም በምስራቅ እና በሰሜንና በደቡብ መንገድ በምዕራብ በይራባ ወሸንቦ ቀበሌ የሚዋሰን አንድ ቀርጥ በድምሬ አምስት ቀርጥ ይዞታዮን ተከሳሾች ከ 10/10/2013 አ.ም ጀምሮ እንዳልጠቀምበት የከለከሉኝ በመሆኑ እንዲለቁልኝ እንዲወሰን የሚል ነው፡፡መልካም ንባብ…

Read more

ወ/ሮ ፋንቱ ዘነበ (2ሰዎች) እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የእንጦጦ ስብሐት ቅድስት ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን መ.ቁ 246386

Friday, May 30, 2025 2851

የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ በመሆን አመልካቾች 1ኛ እና 4ኛ ተከሳሽ በመሆን እንዲሁም በዚህ ክርክር ተካፋይ ያልሆኑት እነ ሳልሳይ ኤፍሬም ጌታቸው 4 ሰዎች በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ፣ 3ኛ፣ 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል፡፡ተጠሪ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበችው የተሻሻለ ክስ የአባ ኃይለስላሴ መገኖ ርስት እና ንብረት የሆነው አንድ ጋሻ ይዞታ ሰኔ 17 ቀን 1948 ዓ.ም በተደረገ ግልጽ ኑዛዜ የተሰጣት መሆኑን ኑዛዜው በከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 169/55 ግንቦት 13 ቀን 1955 ዓ.ም መጽደቁን እና ከሳሽ ይዞታውን ተረክባ ስታስተዳድር የቆየች መሆኑን፤ ከአንድ ጋሻ መሬት ላይ 1192 ካ.ሜ ይዞታ ቀንሳ ለአገልጋይ ካህናት ደመወዝ መክፈያ ይሆን ዘንድ የ1ኛ አመልካች ባለቤት ለነበሩት ለአቶ ኤፍሬም ጌታነህ በወር ብር 30 (ሰላሳ) ሂሳብ ለአምስት ዓመታት አከራይታ የኪራይ ውሉ እስከ 1967 ዓ.ም እየተራዘመ መቆየቱን፤ ይዞታው ያልተወረሰ እና የግል ቤቴ ነው በማለት አቶ ኤፍሬም ጌታነህ በ2004 ዓ.ም ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ እንደ ቅደም ተከተላቸው የስር 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች የነበሩት ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር እና ጉለሌ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር የቤት ቁጥር 815(ለ) በሚል በአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ስም ተመዝግቦ ስም እንዲዞር ማድረጋቸውን፤ ይህንኑ ይዞታ የአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ወኪልና የስር 4ኛ ተከሳሽ(2ኛ አመልካች) የቦርድ ሰብሳቢ በሆኑት አቶ መኮንን አያሌው እና የተጠሪ ፀሀፊ ዲያቆን ተስፋሚካኤል ታደሰ አመልካችነት ይዞታው ወደ አቶ ኤፍሬም ጌታነህ እንዲተላለፍ በመጠየቁ ህዳር 17 ቀን 2005ዓ.ም ቁጥሩ 22/69/28322/00 የሆነ ካርታ በአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ስም ተዘጋጅቶ ተሰጥቷል፡፡ ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም በተደረገ በሽያጭ ውል ለ2ኛ አመልካች(ስር 4ኛ ተከሳሽ) ተላልፏል፡፡ የተጠሪ ይዞታ ከህግ ውጪ የተላለፈ በመሆኑ የስር 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች የይዞታውን ባለቤት በአግባቡ ሳያጣሩ በአቶ ኤፍሬም ጌታነህ ስም በ17/3/2005ዓ.ም አዘጋጅተው የሰጡትን ካርታ እንዲሰርዙ፤ በሟች አቶ ኤፍሬም ጌታነህ እና በስር 4ኛ ተከሳሽ(2ኛ አመልካች) መካከል የተደረገው በ15/12/2005ዓ.ም የተደረገው ውል እንዲሰረዝ፤ የስር 5ኛ ተከሳሽ አለአግባብ በሰጠው መረጃ መሰረት ለስር 4ኛ ተከሳሽ(2ኛ አመልካች) የተሰጠው ካርታ እንዲሰረዝ፤ በምትኩ የስር 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ለይዞታው ለተጠሪ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲሰጡ፤ በይዞታው ላይ ያለን ንብረት 2ኛ አመልካች አንስቶ ይዞታውን ለተጠሪ እንዲያስረክብ እንዲወሰን በማለት ዳኝነት ጠይቃለች፡፡ ማስረጃዎችንም አያይዛለች፡፡ነው፡፡መልካም ንባብ…

Read more
FirstPrevious567891011121314NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions