Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

አቶ በድሩ አባገላን እና የሟች አቶ አባድጋ አባጎጃም ወራሾች የሰ.መ.ቁ.200480

Thursday, December 30, 2021 12460

ይህ የእርሻ መሬት ክርክር የተጀመረዉ በየም ልዩ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.14976 በ1/9/2012 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ በሟች አባቴ አቶ አባገላን አባጊቤ እጅ ለ56 ዓመታት የቆየን ባህር ዛፍ ይዞታ ከዚህ ቀደም በመ.ቁ.09921 ላይ ባህር ዛፍ የሟች አባቴ ነዉ ተብሎ የተወሰነዉ የዉርስ ይዞታዬን በጉልበት ስለያዘብኝ የአሁን ተጠሪ ይዞታዉን እንዲለቅልኝ፣ የወደመዉን ንብረት ግምትና በክሱ ምክንያት የወጠዉን ወጪና ኪሳራ የመጠየቅ መብት እንዲጠበቅልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡……………..

Read more

አቶ ታሪኩ ዮናስ እና ዳንጎቴ ኢትዮጵያ ሲምንቶ ፋብሪካ የሰበር መ/ቁ/200247

Thursday, December 30, 2021 13126

ጉዳዩ የአሰሪና ሠራተኛ የስራ ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩበት ነዉ፡፡አመልካች 02/06/2012 ዓ.ም ባቀረበው ክስ ተጠሪ በሰው ኃይል አስተዳደር የሥራ ዘርፍ በደብዳቤ ቁጥር DI-HR-009-14 ሕዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም በወር ደመወዝ ብር 7,100 የቀጠረኝ ሲሆን የሥራ ብቃት ምዘናዬ ከፍተኛ ስለሆነ በተለያየ ጊዜ እድገት ሰጥቶኝ በመጨረሻ በወር ደመወዝ ብር 29,980.14 እየሰራዉ እያለ ታህሳስ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ያለአንዳች ጥፋት ከስራዬ ስላሰናበተኝ በአዋጅ ቁ/1156/2011 መሰረት ወደ ስራዬ እንዲመልሰኝ ወይም ካልመለሰኝ የተለያዩ ክፍያዎች በድምሩ ብር 435,711.34 እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ በቀን 12/06/2012 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ አመልካች ከፍተኛ የኦፊሰር ስራ ዘርፍ እና የድርጅታችን የሰው ኃይል መመሪያ ኃላፊ በመሆን ሲሰራ ቆይቷል፣ሃላፊነቱ ሥራ አስኪያጅ የሆነ ሰው ደግሞ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 3(2ሐ) መሰረት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መክሰስ ስለማይችል ክሱ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ እንዲሆን ጠይቋል፡፡……………..

 

Read more

ወ/ሮ ህብስት ምሕረቴ እና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ የሰ/መ/ቁ. 200178

Thursday, December 30, 2021 13050

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኛ የነበሩ ሲሆን በወንጀል ተጠርጥረውና ተከሰው የነበረ ሲሆን በኋላም ከወንጀል ክሱ በፍርድ ቤት በነጻ በመሰናበታቸው ወደሥራ ለመመለስ አመልክተዋል፡፡ መሥሪያ ቤቱ በሰው ኃይል አስተዳደር ደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 41 መሠረት በወንጀል ተጠርጥሮ ሥልጣን ባለው አካል በእስር ላይ የነበረና እስከ ሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ከወንጀል ነጻ መሆኑ ተረጋግጦ ወደሥራ ካልተመለሰ አገልግሎቱ ይቋረጣል በሚል በግልጽ የተቀመጠ በመሆኑና አመልካች በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ጥያቄውን ያላቀረቡ በመሆኑ ተቀብለን መድበን ለማሰራት አንችልም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል፡፡………….

Read more

እማሆይ አዛል አይናለም እና አቶ ምህረት በላይ የሰ/መ/ቁ.200144

Thursday, December 30, 2021 12921

ጉዳዩ የስጦታ ውል እንዲፈርስ የቀረበ ክስ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ እንዲሁም የቡሬ ወረዳ መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ጽ/ቤት 2ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡የአመልካች ክስ ይዘት ባጭሩ ለተጠሪ ያደረግሁለት የሥጦታ ውል በመንፈስ ልልነት እና በዕድሜ የገፋሁ አቅመ ደካማ በመሆኔ ምክንያት ከፈቃዴ ውጭ ህጉን ሳይከተል ያደረግሁት በመሆኑ እና በስር 2ኛ ተከሳሽ ከአሁኑ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር የስጦታ ውሉን ያፀደቀ በመሆኑ የስጦታ ውሉ ይፍረስልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ ባቀረበዉ መልስ አመልካች በፈቃዷ ስጦታውን ያደረገችለት መሆኑን እና ክሱ የቀረበው የአመልካች ልጆች ከቅን ልቦና ውጭ በሆነ ሁኔታ መሬቱን ለመውሰድ በማሰብ ነዉ፤የስጦታ ውሉ የሚፈርስበት የህግ ምክንያት የለም በማለት ተከራክረዋል፡፡……………….

Read more

እነ ወ/ሮ ከጆ ሆዕለሞ እና አቶ ብርሃኑ ሸንቆ የሰ/መ/ቁ. 199518

Thursday, December 30, 2021 12627

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት የሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት የአፈጻጸም ተከሳሾች ሲሆኑ ተጠሪ ደግሞ የአፈጻጸም ከሳሽ ነበሩ፡፡ ለአፈጻጸም መነሻ የሆነው አመልካቾች ሁለት ጥማድ የይዞታ መሬት ለቀው ለተጠሪ እንዲያስረክቡ ተብሎ የተሠጠው ውሳኔ ነው፡፡…………

Read more
FirstPrevious11121314151617181920NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions