Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

አቶ አበበ አድገህ እና እነ ወ/ሮ ዘሪቱ ደርሰህ የሰ/መ/ቁ፡- 199400

Thursday, December 30, 2021 15988

 ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ዉል መኖሩ በተካደ ጊዜ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚገባዉን ዉል አይነት የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካች በምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ ከ1ኛ ተጠሪ እና ከተራ ቁጥር 2-5 ድረስ የተጠቀሱ ተጠሪዎች አባት ከሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ ጋር በቀን 13/10/1987 ዓ/ም በተጻፈ የቤት ሽያጭ በደንበጫ ከተማ ዉስጥ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰዉን ስፋቱ 5 ሜትር በ10 ሜትር ወይም 50 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራ በሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን 32 ዚንጎ የቆርቆሮ ቤት በብር 10,000.00 ሽጠዉልኛል፡፡ገንዘቡን በእለቱ ተረክበዉ የሽያጭ ዉሉን በደንበጫ ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት አስገብተነዉ በፋይሉ ዉስጥ ይገኛል፡፡ቤቱን በግዥ ያገኘሁ ስለመሆኑ በተለያዩ ጊዜ የታመነ እና የተረጋገጠ ቢሆንም አሁን ላይ በቤቱ ለመጠቀም ስፈልግ የተለያዩ ተግባራትን እንዳላከናዉንና የቤቱ ስመ ሀብት በስሜ ዞሮ እንዳይመዘገብ ተጠሪዎች ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ስለሆነም ተጠሪዎች በሚመለከተዉ አካል ፊት ቀርበዉ የቤቱን ስመ ሀብት በስሜ እንዲያዛዉሩልኝ እንዲወሰንልኝ፡፡ዉሉ የሚፈርስበት ምክንያት አለ ከተባለም ቤቱ በአሁኑ ጊዜ የሚያወጣዉን የዕለት ዋጋ ብር 200,000.00 እንዲከፍሉኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ...........................

Read more

አቶ አክሉሉ ካሕሳይ እና አኪር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግል ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-198891

Thursday, December 30, 2021 15924

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበር፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ ከተጠሪ ጋር ጥር 25 ቀን 2005 ዓ/ም በተደረገ የመኪና ኪራይ ውል ስምምነት መሠረት የሠሌዳ ቁጥር 3-83597 አ.አ. የሆነ ተሽከርካሪ ለ10 ወራት ከ15 ቀናት ለሰራው ብር 346,500.00 ተጠሪ መክፈል ሲገባው ብር 100,000.00 ብቻ ከፍሎ ቀሪ ገንዘብ ስላልከፈለ ብር 246,500.00 ከሕጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፈላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡……………..

Read more

አቶ ወርቁ ኃይለመስቀል እና አቶ ከበደ ደስታየሰ/መ/ቁ፡-198805

Thursday, December 30, 2021 16316

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ከሟች አባታቸው አቶ ደስታ አድማሱ በውርስ የሚተላለፍ የሚንቀሳቀስ እና በዚህ ችሎት ደረጃ አከራከሪ ሆነ የቀረበውን የገጠር እርሻ መሬት አመልካች ለቀው እንዲያስረክቧቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ አመልካች ስለመሬቱ ያቀረቡት መልስ ይዞታው የሟች ደስታ አድማሱና የባለቤቱና የአመልካች አያት የሆኑት የወ/ሮ እህተጊዮርጊስ ኃይለጊዮርጊስ ሲሆን አያቴ ወራሽ ስለሆን የሟች ደስታ አድማሱን ድርሻ በኑዛዜና በሥጦታ አስተላፈውልኛል፡፡ በድጋሜ ከልጆቹ ጋር መሬቱን አውርሰውኛል፡፡ የሟች ደስታ ድርሻ ሊተላፍልህ አይችልም ቢባል እንኳን የአያቴ የቤተሰብ አባል ስለሆንኩ ግማሽ ድርሻውን ተጠሪ ሊጠይቁኝ አይገባም ብለዋል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ…………….

Read more

አቶ ወንድማገኝ ታደሰ አጋር የጥበቃ አገለግሎት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የሠ/መ/ቁጥር 198669

Thursday, December 30, 2021 15616

ጉዳዩ የስራ ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡ አመልካች በሐረር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ተጠሪ ለጥበቃ ስራ ከቀን 01/02/2010 ዓ/ም ጀምሮ በወር ብር 1,293.00 ደመወዝ እየከፈለ ሊያሰራቸዉ ቀጥሯቸዉ እስከ ቀን 13/02/2011 ዓ/ም ድረስ እየሰሩ ቆይተዉ በስራ መመዝገቢያ ላይ ፈርሜ የተረከብኩት ጥበቃ ቀጠና ውጪ ሌላ ቀጠና ላይ ሄደህ የጥበቃ ሥራ እንዲሰሩ ሲያዛቸዉ በሥራ መመዝገቢያ ላይ ፈርሜ የተረከብኩት ጥበቃ ቀጠና ላይ ችግር ቢፈጠር ተጠያቂ እሆናለሁ በማለታቸዉ ብቻ በቀን 13/02/2011 ዓ/ም ከሥራ እንዳሰናበታቸዉ ገልጸዉ ሥንብቱ ሕገ-ወጥ ነዉ ተብሎ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የተለያዩ ክፍያዎችን በድምሩ ብር 22,487.08 ተጠሪ እንዲከፍላቸዉ እንዲወሰንላቸዉ ዳኝነት ጠይቀዋል…………...        

Read more

እነ ወ/ሮ መሠለች ደስታ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ቢሮ የሰ/መ/ቁ.193168

Thursday, December 30, 2021 15969

 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች የስር ከሳሾች ሲሆኑ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ተከሳሽ እና ተጠሪ የመቃወም አመልካች ነበሩ፡፡አመልካቾች በዚህ ችሎት ደረጃ ተከራካሪ ባልሆነው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 582 በሆነ ይዞታ   ያላቸው ካርታ እንዲያስተካክልና የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ሲሉ የጠየቁት ዳኝነት በፍርድ ቤቱ ውደቅ በመደረጉ ይግባኝ አቅርበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን ተመልክቶ አመልካቾች በዕጃቸው በሚገኘው 783.82 ካሬ ሜትር ይዞታ በመሆኑ ካርታውን እንዲያስተካክልና የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ወስኗል፡፡………………..

Read more
FirstPrevious12131415161718192021NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions