ሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች በቀን 01/07/2012 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፌደራል
መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 132828 በቀን 06/10/2010 ዓ.ም እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት
በመ/ቁ 219424 በቀን 28/05/2012 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁን 1ኛ አመልካች ተከሳሽ፤ እንዲሁም 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ጣ/ገብ ነበሩ፡፡
ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው ተጠሪ በቀን 24/09/2007 ዓ.ም ባቀረቡት ክስ በጻፉት አቤቱታ በአራዳ
ክ/ከተማ የሚገኝ የቤ.ቁ 200 የሆነ መኖሪያ ቤት በወላጅ አባቴ አቶ ይመር ስም ያለኝ ሲሆን አባቴ በመሞቱ ወራሽነቴ ተረጋግጦ ማስረጃ ተሰጥቶኛል፤ ተከሳሽ የእህቴ ልጅ ሚስት በመሆኗ ቤቱን ይዛ እየተጠቀመችበት ትገኛለች፣ በአሁን ግዜ ቤቱን ስለምፈልገው እንድታስረክበኝ ብጠይቃት ፈቃደኛ ባለመሆኗ ቤቱን እንድትለቅ እና እንድታስረክበኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል………