ጉዳዩ የጉዳት ካሳን የሚመለከት ሲሆን ክሱ በጀመረበት የፌ/ከ/ፍ/ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ ነበር፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት የክስ ይዘትም፡- የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-53974 ኢ.ት እንዲሁም ኮድ 3-1775 ኢ.ት ለሆነው ተሽከርካሪያቸው ከአመልካች አጠቃላይ የንግድ ተሸከርካሪ የመድን ዋስትና የገዙ መሆኑን፤ ይህ መድን የተገባለት ተሸከርካሪያቸው በስራ ላይ እያለ በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ ህዳር 17 ቀን 2011 ዓ.ም ያልታወቁ ግለሰቦች አስገድደው እንዲቆም አድርገው ተሸከርካሪውን፤ጭኖት የነበረውን ቢራ እና የሽያጭ ደረሰኞች ይዘው መሰወራቸውን፤ ይህ ስርቆት መፈጸሙን የተጠሪ ወኪል እንዳወቁ ወዲያውኑ ለአመልካች ድርጅት አሶሳ ቅርንጫፍ ማሳወቃቸውን፤ ከበርካታ ክትትል በኋላ ነሀሴ 16 ቀን 2011 ዓ.ም ተሳቢው ምንም ጉዳት ሳይደርስበት የተገኘ መሆኑን እና ዋናው ተሸከርካሪ ግን ተቃጥሎ መገኘቱን፤ ነሀሴ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ፖሊስ ባደረገው ሪፖርት ተሽከርካሪው እና ተሳቢው 2,400 ሳጥን ቢራ ጭኖ ከአ.አ ወደ አሶሳ በመጓዝ ላይ እንዳለ ህዳር 17 ቀን 2011 በሌቦች ተሰርቆ ዋናው ተሸከርካሪ በቃጠሎ ከጥቅም ውጭ ሆነ መገኘቱን መግለጹን፤አመልካች ካሳ እንዲከፍል ሲጠየቅ ደርጊቲ የተፈጸመው በሽፍቶች ነው፤ በኋላ ላይ ደግሞ ድርጊቱ የተፈጸመው በጦርነት እንቅስቃሴ እና መሰል ሁኔታዎች ነው፤ እንዲሁም ስለድርጊቱ መከሰት አላሳወቃችሁኝም በማለት የካሳ ክፍያ ጥያቄአቸወን ውድቅ ማድረጉን ገልጸው ንብረቱ በእሳት ሙሉ በሙሉ የወደመ ስለሆነ በመድን ውሉ ለንብረቱ ከተሰጠው የዋስትና ጣሪያ ብር 2,000,000.00 ከተወሰነው የአደጋ መነሻ ውስጥ ከፍተኛውን 5 % ተቀናሽ በማድረግ 1,900,000.00 ከወጪና ኪሳራ ጋር አንዲከፍል ይወሰንልኝ ሲሉ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…