240
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች በቀን 01/08/2013 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 237391 በቀን 27/11/2012 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 196246 በቀን 20/05/2013 ዓ.ም ያሳለፈው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው፡፡ መልካም ንባብ…………
2361
የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ባቀረበዉ ክስ በከሳሽ እና ተከሳሽ መካከል በ1985 ዓ.ም የተፈፀመው ጋብቻ ከየካቲት ወር 1989 ዓ.ም ጀምሮ በሁኔታ መፈረሱ ፍ/ቤት በ28/2/2007 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ እና ዉሳኔዉ በ4/5/2008 ዓ.ም በታረመበት ትዕዛዝ መሰረት የጋራ ንብረትና እዳ ክፍፍል እንዲደረግልኝ ዳኝነት ጠይቋል፡፡መልካም ንባብ………
2314
ጉዳዩ የስጦታ ዉል ማፍረሻ ምክንያት የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካቾች በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ ወላጅ አባታቸዉ አቶ ታምራት ፈለቀ በቀን 20/05/2010ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸዉ ወራሽነታቸዉን አረጋግጠዉ ዉርስ በሚጣራበት ጊዜ በሟች አባታቸዉ ስም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ዉስጥ በካርታ ቁጥር ቦሌ2/39/10/6/11970/00 የተመዘገበ ቤት ተጠሪ በቀን 15/05/2010ዓ/ም በተደረገ የስጦታ ዉል ሟች እንዳስተላለፉላቸዉ በመግለጻቸዉ የስጦታ ዉሉ መኖሩን እንዳወቁ በመግለጽ ይህ የስጦታ ዉል የኑዛዜ ፎርም ያልተከተለና ያልተነበበ በመሆኑ እና የስጦታ ዉሉ በሟቹ ነጻ አዕምሮ ሳይሆን በጫና የተደረገ በመሆኑ እንዲፈርስ ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…….
2323
የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ከሳሽ በመሆን በአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካች የመጨረሻ ልጃችን ስለሆነ የእርሻ ይዞታችን ለጋራ አራሽነት አርሰው ምርት ለመጠቀም የሰጠነውን የሐሰት የስጦታ ውል በማዘጋጀት ይዞታችን እንዳንጠቀም ከልክሎናል፣ስለዚህ የስጦታ ውሉ ተሰርዞ ይዞታችን ለቆ እንዲወጣልን የሚል ሲሆን አመልካች በበኩሉ በዚህ ጉዳይ ቀደም ሲል ተጠሪዎች በመ/ቁ.26038 ላይ ክስ መስርተው እስከ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተወስኗል፤ክሱ ድጋሚ የቀረበው ነዉ በሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበ ሲሆን የወረዳ ፍ/ቤት ቀደም ሲል በመ/ቁ.26038 ላይ የነበረው ክርክር ሁከት ይወገድልኝ የሚል መሆኑን አሁን በመ/ቁ. 26670 የቀረበው ክስ ደግሞ የስጦታ ውል ተሰርዞ ይዞታችን እንዲለቅ የሚል ስለሆነ ድጋሚ የቀረበ አይደለም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አድርጎ በፍሬ ክርክር ላይ ውሳኔ ሰጥቷልመልካም ንባብ……..
2328
ጉዳዩ የከተማ ቦታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአፍደም ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- ተጠሪ በህገወጥ መንገድ ባለቤትነቱ የአመልካች በሆነው መሬት ላይ ያላግባብ ግንባታ ሊገነባ ስለሆነ ተጠሪ እያደረገ ያለውን ህገወጥ ግንባታ እንዲያቆም ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ………