Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

አቶ ፍቃዱ አዱኛ እና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ የሰ-መ-ቁ-195138

Monday, March 8, 2021 17889

አቶ ፍቃዱ አዱኛ እና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ የሰ-መ-ቁ-195138 ጉዳዩ የጠበቃ ዲስፕሊን ክስ ጋር በተያያዘ የተሰጠ የጥፋተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ በመጀመሪያ በታየበት በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የጠበቆች የዲስፕሊን ጉባኤ በአመልካች ላይ በቀረበዉ የዲስፕሊን ክስ አቶ እሸቱ ገበየሁ እና በባለቤታቸዉ ወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር መካከል የነበረዉ ጋብቻ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በመ/ቁጥር 70064 ላይ ያደረጉትን ክርክር በፍቺ ፈርሶ የንብረት ክፍፍል ዉሳኔ በቀን 19/02/2008ዓ/ም ከተወሰነ በኋላ አመልካች የአቶ እሸቱ ገበየሁ ባለቤት ከነበሩት ወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር ጋር በመመሳጠር የአመልካች ባለቤት ወ/ሮ አዲስአለም ደሳለኝ በእላዩ ላይ ቀን 11/06/2001 ዓ/ም ተብሎ ተጽፎበት በተፈረመ ዉል ለወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር ብር 600,000.00 እንዳበደሩ በማስመሰል የሐሰት የብድር ዉል በመፈራረም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 177766 ላይ ባለቤታቸዉን ወ/ሮ አዲስአለም ደሳለኝን ወክለዉ በአቶ እሸቱ ገበየሁ ባለቤት በወ/ሮ አዲስአለም ገብረእግዚአብሔር ላይ ሀሰተኛ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ክስ በመመስርት አስወስነዋል፤በይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበዉ ተከራክረዋል በሚል በአቶ እሸቱ ገበየሁ የዲስፕሊን ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡…..   

Read more

እነ ማስተዋል ታዘበው እና ወ-ሮ አቻም ሙጬ የሰ-መ-ቁ 180761

Saturday, March 6, 2021 19003

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የአማራ ብ/ክ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 86614 ግንቦት 21 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ፣ የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 0318665 የካቲት 20 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ እና የባህርዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 54250 ጥር 17 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታቸውን በማቅረበቀቸው ነው፡፡ ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልን ይገባል የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤት አባታችን በህይወት እያለ በ300 ብር ቦታ ገዝቶ ቤት ሰርቶበት እየኖረበት የሞተ መሆኑ ምስክሮቻችን መስክረውልን እያለ የ2ኛ ተጠሪ ምስክሮች ከኛ ምስክሮች ባልተሻለ ሁኔታ የሰጡትን ምስክርነት ወስዶ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን የሚል ነው፡፡……..         

Read more

እነ መቶ አለቃ ኩምሳ ጨመዳ፣ወ-ሮ ኡርጌ መርጋ እና አቶ ካሳሁን አድነው የሰ-መ-ቁ 188071

Friday, March 5, 2021 18004

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር የሽያጭ ውል ያላቸው መሆኑና ውሉም የተፈፀመው ከጋብቻ በፊት መሆኑ በ2ኛ ተጠሪ ታምኖ እያለ ፤ 250 ካ.ሜ በሆነ ይዞታ ላይ ስድስት ክፍል ቤት ሰርቶ ከፊሉን መኖሪያቸው ቀሪውን የሚያከራዩት በአጥር ተከልሎ ለብቻው ያለ ቤት መሆኑ በምስክሮችም ሆነ በክፍለ ከተማ ተረጋግጦ እያለ ፤ እንዲሁም የአመልካች ይዞታ ከተጠሪ የተለየ መሆኑ እየታወቀ ተጠሪዎች የስድስት ክፍል ቤት ባለመብት አድርጎ እኩል እንዲካፈሉ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መወሰኑ እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህን ውሳኔ ማጽናቱ መሰረታዊ  የህግ ስህተት ነው በማለት በሰበር ለማሳረም ነው።...........

Read more

እነ ወ-ሮ መሰረት ገብሬ እና ወ-ሮ ወርቋሃ ገብሬ የሰ-መ-ቁ 182459

Monday, February 8, 2021 18315

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 123889 በቀን 15/12/2011 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 222328 በቀን 15/09/2011 ዓ.ም ያሳለፈው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው። ለውሳኔው ምክንያት የሆነው ክርክር በስር የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረው የአሁን ተጠሪዎች ባቀረቡት የመቃወሚያ አቤቱታ ሲሆን የአሁን አመልካች የመቃወም ተጠሪ ነበሩ፡፡ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው ተጠሪዎች በቀን 08/12/2009 ዓ.ም ባቀረቡት የመቃወም አቤቱታ የአሁን አመልካች የአቶ ገብሬ ደስታ ልጅ ሳትሆን ልጅ ነኝ በማለት አመልክታ ፍ/ቤቱ ልጅ ነሽ በማለት የሰጠው ውሳኔ እንዲሰረዝልን በማለት ጠይቀዋል፡፡አመልካች በሰጡት መልስ በጋብቻ ውስጥ ስለተወለድኩ እና በህጉ ላይ የተመለከተውን የህግ ግምት ስላላስተባበሉ፤ ሟች እናትና አባቴ በ1965 ተጋብተው በ1969 ዓ.ም የተወለድኩ በመሆኑ፤ እንዲሁም ሟች አባቴ ልጅ መሆኔን አምኖ እንደ ልጅ ሲያስተምረኝ እና ሲንከባከበኝ ስለነበር አቤቱታቸው ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡                                            ፍርድ ቤቱም የመቃወም ተከሳሽ የሟች አቶ ገብሬ ደስታ ልጅ ናቸው በማለት የተሰጠው ውሳኔ ሊሰረዝ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ክርክርና ማስረጃውን መርምሮ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በሰጠው ውሳኔ አቶ ገብሬ ደስታ እና ወ/ሮ ዳዊ ገመቹ ጋብቻ መስርተው የነበረ መሆኑና የመቃወም ተከሳሽን ያሳደጓቸው መሆኑ በግራ ቀኙ የታመኑ ፍሬ ነገሮች ናቸው፡፡  የመቃወም ተከሳሽ አቶ ገብሬ ደስታ እና ወ/ሮ ዳዊ ገመቹ በ1965 ዓ.ም ተጋብተው በ1969 ዓ.ም ተወለድኩ በማለት ቢከራከሩም ምስክሮቻቸው ግን አቶ ገብሬ ደስታ እና ወ/ሮ ዳዊ ገመቹ መቼ እንደተጋቡ አላስረዱም፡፡  በተጨማሪም የመቃወም ተከሳሽ የልደት ምስክር ወረቀት ቢያወጡም የመቃወም ከሳሾች ምስክሮች በተመሳሳይ ቃል የመቃወም ተከሳሽ እናትና አቶ ገብሬ ደስታ ከመጋባታቸው በፊት የመቃወም ተከሳሽ ተወልደው የመጡ መሆኑን መስክረዋል፡፡ ሟች የመቃወም ተከሳሽን ያሳደጓቸው፣ ያስተማሯቸው እና በስማቸው የሚጠሩ መሆኑ በመቃወም ተከሳሽ ማስረጃዎች ቢረጋገጥም ይህን ያደረጉት ግን የሚስታቸው ልጅ በመሆናቸው ምክንያት እንጂ ልጃቸው በመሆናቸው አይደለም፡፡ በመቃወም ከሳሾች እና ተከሳሽ መካከል ዝምድና እንደሌለም በምርመራ ተጣርቷል፡፡ በመሆኑም የመቃወም ተከሳሽ የሟች አቶ ገብሬ ደስታ ልጅ ናቸው በማለት በቀን 09/10/2009 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 360(2) መሰረት ተሰርዟል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡….

 

Read more

አቶ ብርሃኑ ታደሰ እና የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ቤቶች አስተዳደር ፅ-ቤት የሠ-መ-ቁጥር 190440

Thursday, February 4, 2021 18039

ጉዳዩ የመንግስት(የቀበሌ) ቤት የመከራየት መብት የሚተላለፍበትን አግባብ በተመለከተ የተሰጠ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበ አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በተጠሪ ላይ በመሰረቱት ክስ በወ/ሮ ሀረገወይን በላይነህ የማነህ ተከራይተዉ በያዙት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በቤት ቁጥር 222 በሆነው ቤት ዉስጥ ከ1975 ዓ/ም ጀምሮ የስድስት ዓመት ህፃን እያለሁ ጀምሮ  እንደልጅ እያስተማሩኝ ያሳደጉኝ እና እስከአሁን ድረስ በቤት ውስጥ በመኖር ላይ እገኛለሁ፡፡ ነገር ግን አሳዳጊዬ የነበረችው ወ/ሮ ሀረገወይን በላይነህ በ1989 ዓ/ም አብረን ከምንኖርበት ቤት እኔ በማላውቀው ምክንያት ከቤት ከወጣች በኋላ አግኝቻት የማላውቅ መሆኔን በመግለፅ የመጥፋት ውሳኔ እንዲሰጠኝ ለአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርቤ ጉዳዩ እየታየ ይገኛል፡፡ የቤቱን ኪራይ በእሷ ስም እየከፈልኩ የምገኝ በመሆኑ በመመሪያ ቁጥር 4/2009 አንቀፅ 15/1 መሰረት የቤቱን ኪራይ ዉል በስሜ እንዲያዋውለኝ ባመለክትም ተጠሪ ሊያስተናግደኝ ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ስለሆነም ተጠሪ የኪራይ ውል እንዲያዋውለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡……… 

Read more
FirstPrevious22232425262728293031NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions