Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

እነ ወ-ሮ ባህጃ ሳላህ፣ወ-ሮ ፎዚያ መሀመድ እና ወ-ሪት ምስራ አግዛ የሰ-መ-ቁጥር 184798

Friday, January 1, 2021 16748

ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካቾች ጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 84261 ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ እና የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 239167 ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታቸውን በማቅረባቸው ነው፡፡ ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ በስር ፍ/ቤት ያቀረብነው ክስ ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ የእናቷን ውክልና መሰረት በማድረግ ውርስ እንዲጣራ አድርጋ ያከራከረንን ቤት ወደ እናቷ ስም ያዛወረች በመሆኑ ይሰረዝልን የሚል ሆኖ እያለ በውርስ ህግ በፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1000(1) መሰረት ክሳችንን በይርጋ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን የሚል ነው፡፡………..

Read more

አቶ አሰፋ በላይ፣ የጅማ ከተማ ወረዳ 1 ፖሊስ ጽ/ቤት ዋና ሳጅን ወጋየሁ አሊ እና የጅማ ከተማ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሰ-መ-ቁ 183680

Friday, January 1, 2021 16168

ይህ የጉዳት ካሳ ክርክር የተጀመረዉ በጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር 1ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች፣ እንዲሁም በዚህ ክርክር ተካፋይ ያልሆኑትን ሌሎች ሶስት የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.300905 በ11/10/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ። የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ የአሁን አመልካች ባቀረቡት ክስ አመልካች የቡና አምራችና ነጋዴ በመሆናቸዉ ቡና ከየቡ ከተማ ካለኝ መጋዘን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ስላነሰኝ የወረዳዉን ቡናና ሻይ ባለስልጣን በአፍ በማስፈቀድ 54 ኬሻ ቡና ከጅማ ከተማ 17 ኪ.ሜ ርቅት ላይ ወደ ምትገኘዉ የቡ ከተማ በመጓጓዝ ላይ ሳለሁ የይለፍ ፍቃድና ቡናዉ ቡናዉ በፕሎምፕ መታሸግ በማያስፈልግበት ሁኔታ ያስፈልጋል በማለት የአሁን 1ኛ ተጠሪ አባላት ሲይዙኝ የአሁን 2ኛ ተጠሪ በኮሚቴ ለጉዳዩ በፍጥነት መወሰን ሲገባዉ ባለማድረጉ የያዙትን ቡና ዋጋና በገንዘቡ እስከ አሁን ብሰራበት ኖሮ ትርፉን፣ መኪናዉ ቆሞ ላጣሁት የቀን ገቢና የጠበቃ አበል እንዲከፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል።  የአሁን ተጠሪዎች በዚህ ክስ ላይ ባቀረቡት መልስ በኦሮሚያ ቡና ጥራት ቁጥጥርና ንግድ አዋጅ ቁ.160/2006 አንቀጽ 23 ቡናን ለማጓጓዝ የይለፍ ወረቀት እንደሚያስፈልግ፤ በቡና አዋጅ ቁጥር 602/2000 ህገ ወጥ የሆነን ቡና በመያዝ ለሚመለከተው አካል የቀረበ በመሆኑ፤ በፌደራል ደንብ ቁ.159/2001 አንቀጽ 22 (2) (ለ) ህገ ወጥ ተብሎ ለተያዘ ቡና ቅሬታ ማቅረብ የሚገባው ለሚመለከተው አካል እንጂ ለፍ/ቤት አይደለም፤ በአዋጅ ቁጥር 1051/2009 አንቀጽ 19 (7) ከአቅጣጫ ውጪ እያጓገዘ በመሆኑና በፕሎምፕም ያልታሸገ በመሆኑ በህገ ወጥ የሚጓጓዝን ቡና በህጋዊ መንገድ የያዙ በመሆኑ ልንከሰስ አይገባም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና በአማራጭ ክርክር አቅርበዋል።………….

Read more

እነ አቶ መርጋ ከበደ፣ አቶ አበራ ከበደ እና ጠ/ዮሴፍ አመንቴ የሰ-መ-ቁ-189155

Wednesday, December 30, 2020 16836

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካቾች የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 48351 በቀን 01/09/2011 ዓ.ም የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ 30573 በቀን 06/07/2011 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የሰጠውን ውሳኔ፤ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 313390 በቀን 29/01/2012 ዓ.ም እንዲሁም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ 319820 በቀን 19/02/2012 ዓ.ም በመሻራቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ የተጀመረው በስር የዳዎ ወረዳ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት ክስ ሲሆን ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡……..

Read more

እነ አቶ ኪሮስ መኮንን፣አቶ ዳዊት አማረ እና አቶ ኪሮስ ዳኘው የሰ-መ-ቁ- 188807

Wednesday, December 30, 2020 16959

ጉዳዩ የእግድ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሠሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የሥር ከሳሽ፣ 2ኛ ተጠሪ ተከሳሽ ሲሆኑ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረቡት ክስ 2ኛ ተጠሪ ቤት እንዲገዛልኝ ገንዘብ ልኬለት የንብረቱን ሥመ-ሀብት በስሙ ስላደረገ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የቤት ቁጥሩ TH-14-B-4 የሆነ ቤት ያስረክበኝ ወይም ግምቱን ይክፈለኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር እየተከራከሩ ባለበት ሁኔታ ክርክር ያስነሳው ንብረት ላይ ፍርድ ቤቱ  እግድ ሠጠ፡፡ 1ኛ ተጠሪ ጣልቃ በመግባት ንብረቱን ከ2ኛ ተጠሪ በውል ስለገዛሁ ሊከራከሩበት አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ በክርክሩ መካከል አመልካችና 2ኛ ተጠሪ ሠኔ 29 ቀን 2009 ዓ/ም ባደረጉት የእርቅ ሥምምነት የገንዘብ ዕዳውን 2ኛ ተጠሪ ለአመልካች ሊከፍሉና ተከፍሎ እስከሚያልቅ ድረስ ንብረቱ ላይ የተሠጠው እግድ ሳይነሳ እንዲቆይ የተስማሙ ሲሆን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 190764 ጥቅምት 06 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የእርቅ ሥምምነቱን ተቀብሎ በፍብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 277 መሠረት አጽድቋል፡፡ 1ኛ ተጠሪ በበኩላቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገብ ቁጥር 191057 ክርክር ያስነሳውን ንብረት 1ኛ ተጠሪ ስለገዙት 2ኛ ተጠሪ ለ1ኛ ተጠሪ እንዲያስረክቡ ሕዳር 20 ቀን 2011 ዓ/ም የተሠጠውን ፍርድ በማያያዝ ንብረቱን በፍርድ ስላገኘሁት በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ ክርክር ምክንያት የተሠጠው እግድ እንዲነሳ በማለት አመልክተዋል፡፡ አመልካች ለእግድ ይነሳልኝ ማመልከቻው ያቀረቡት መልስ በእርቅ ስምምነቱ የተመለከተውን ገንዘብ 2ኛ ተጠሪ እስኪከፍሉ ድረስ እግዱ ጸንቶ እንዲቆይ ተስማምተን እርቁ በፍርድ ቤት የጸደቀና ይህንንም 1ኛ ተጠሪ እያወቁ ያልተቃወሙና በይግባኝ ያላስለወጡ በመሆኑ አቤቱታው ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡…………

Read more

ህፃን ሒዳያ አማን መሀመድ እና አመተበል መሃመድ የሰ-መ-ቁ 185175

Wednesday, December 9, 2020 17847

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 86183 በቀን 17/05/2011 ዓ/ም እንዲሁም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 2301172 በቀን 19/02/2012 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው፡፡ ክርክሩ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረው የአሁን አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ ሲሆን የአሁን ተጠሪ 1ኛ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡የአመልካች ሞግዚት በቀን 14/06/2010 ዓ/ም ባቀረቡት ማመልከቻ የህፃን ሒዳያ አማን ወላጅ አባት በቀን 21/05/2010 ዓ/ም በሞት የተለዩ ሲሆን የወራሽነት ውሳኔ በማቅረብ የሟች የውርስ ሀብት እንዲጣራ የውርስ አጣሪ እንዲሾም ጠይቀዋል፡፡ፍ/ቤቱም የሟች ውርስ እንዲጣራ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ የአሁን ተጠሪ እና ሰነያ መሀመድ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ የውርስ አጣሪ ውርሱን አጣርቶ ሪፖርት እንዲያቀርብ ባዘዘው መሰረት በቀን 26/02/2011 ዓ/ም ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ግራቀኙም አስተያየታቸውን አቅርበዋል፡፡በተለይም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-34360 ኦ.ሮ የሆነውን ተሽከርካሪ በተመለከተ የውርስ አጣሪ ባጣራው መሰረት የቀረበው ማስረጃ ተሽከርካሪው በሟች ስም የሚገኝ ቢሆንም ለ1ኛ ጣልቃገብ /የአሁን ተጠሪ/ተሽከርካው ሟችን ጨምሮ ቤተሰባቸውን እንዲረዳ እንዲሁም ለ1ኛ ጣልቃገብም ሀብት እንዲሆን የተገዛ ተሽከርካሪ እንደሆነና ገንዘቡንም ከአረብ ሀገራት በመሰራት ካገኘሁት ገቢ የተገዛ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በበኩላቸው ይህን ክደው ተከራክረዋል፡፡..............

Read more
FirstPrevious24252627282930313233NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions