የቀረበው የሲያ/ዋዩ ወረዳ ፍርድ ቤት አመልካች ለአከራካሪው ቤትና ይዞታ በተጠሪ ስም የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰርቶ ሊሰጠው ይገባል በማለት የሰጠው ውሳኔ በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች መፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት አመልካች ስላመለከተ ነው፡፡አመልካች በሲያ/ዋዩ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ ነበሩ፡፡
ተጠሪ ህዳር 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፈው በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስም አቶ ማናዜ መኮንን እና ወ/ሮ እትሞላሽ ደመቀ የነበራቸውን ጋብቻ በፍርድ ቤት አፍርሰው የጋራ ንብረታቸው የሆነውን በደነባ 01 ቀበሌ ሐ ዞን የሚገኘውን ቤትና ቦታቸውን ከተካፈሉ በኋላ ለአቶ ማናዜ የደረሳቸውን 187 ካሜ ቤትና ቦታ በ27/10/2006 ዓም በተደረገ ውል ገዝቼ አመልካችም ውል አዋውሎን፤ውሉን አፅድቆ በስሜ በማዞር የግንባታ ፈቃድ ሰጥቶኝ የነበረውን ቤት አፍርሼ ቤት የሰራሁበት ሲሆን ለይዞታዬ ካርታ እንዲሰጠኝ ስጠይቀው የቀበሌ ቤት አብሮ ስለተሸጠልህ አልሰጥህም ያለ ሲሆን ያሉትን አስተዳደራዊ መንገዶች ሁሉ ተጠቅሜ ጥያቄን ባቀርብም ምላሽ ያላገኘሁ በመሆኑ ለቤትና ለቦታው የባለቤትነት ማስረጃ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡………