15
የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሾች በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ፡- ከተከሳሽ እህትማማች ድርጅት (ሲስተር ካምፓኒ) ከሆነው አስኩ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዉስጥ እንደየቅደም ተከተላቸው በጽዳት ሰራተኛነት፣ በቦትል ኢንስፔክተርነት የስራ መደብ፣ በጽዳት ሰራተኝነት፣ በማቴሪያል ሆልደር የሥራ መደብ እያገለገልን እያለን ሁሉም ከሳሾች በያዙት የሥራ መደብና ደመወዝ ከሐምሌ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተከሳሽ ድርጅት ተዛዉረዉ በመስራት ላይ እያሉ ተከሳሽ በ30/05/2014 ዓ.ም የህግ አካሄድን ሳይከተል በቂ ባልሆነ ምክንያት ከመደበኛ ሥራችን በደብዳቤ አሰናብቶናል፡፡ ስለሆነም ይህ ስንብት ሕገወጥ ስለሆነ ዉዝፍ ደመወዝ ተከፍሎን ወደ ሥራችን እንመለስ ወይም የሥራ ስንብት ክፍያና ከስንብቱ ጋር የተያያዙ ክፍያዎች እንዲከፈለን በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ጥሩ ንባብ…
19
አመልካች ባቀረቡ አቤቱታ በአመልካች እና በሟች አቶ ዴሬሳ ሀንቃሞ መካከል ከጋብቻ ውጪ በነበረ የግብረ ስጋ ግንኙነት ሕጻን ትንሳኤ ደሬሳ ተወልዷል፡፡ አመልካች የልጁ እናት ስለመሆኔ አለታ ጩኮ ወረዳ ፍ/ቤት በፍ/መ/ቁ 19030 አረጋግጫለሁ፡፡ ልጄ ሕጻን ትንሳኤ ደሬሳ የእስፔን ሀገር ዜግነት ባላቸው ባልእና ሚስት በሆኑት አቶ ፍራንሲኮ ጄርኖም እና ወ/ሮ ስለቪያ ፓንስ ኬበዛስ በኩል የትምርት ዕድል እስፔን ሀገር በማግኝቱ ባልና ሚስቱ የሞግዚትነት ስልጣን እዲያገኙ አመልክቼ የሞግዚትነቱ ስልጣን በፌ/መጀመሪያ ደረጃ በፍ/ቤት ጸድቋል፡፡ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የማድሪድ ክልል መንግስት በቀን 19/10/2007 ዓ/ም ለደ/ብ/ብ/ሕ/ ክልል መንግስት በተጻፈ ደብዳቤ ሕጻኑ በሞግዚት በኩል የትምህርት ዕድል እንደሚያገኝ አሳውቋል፡፡ አመልካች የሞግዚትነት ኃላፊነት ለመስጠት የቻልኩት ህፃኑ በምቾት እንዲያድግና የተሻለ የትምህርት ዕድል እንዲያገኝ በማሰብ ነው፡፡ ይሁንና ልጄ ሕጻን ትንሳኤ ዴሬሳ ከእኔ እውቅና ውጪ በተከሳሽ ድርጅት ውስጥ የሚገኝ በመሆኑና ልጄን እንዲሰጡኝ በተደጋጋሚ ብጠይቅም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ህፃኑ በሞግዚት በኩል ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ ትምህርቱን እንዲከታተል ህፃን ልጄን ተከሳሽ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ጥሩ ንባብ…
18
የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው ክስ የወ/ሕ/ቁ. 32(1)(ሀ) እና 671(1)(ሀ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን በቀን 01/12/2010 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 05፡30 ሰዓት አከባቢ በወልቂጤ ከተማ አዲስ ሕይወት ቀበሌ ልዩ ቦታ ጥምቀተ ባህር ተብሎ በሚጠራው መንደር የግል ተበዳይ አቶ መልካሙ ጫላ ቤት ላይ ድንጋይ ሲወረውር ተበዳዩ ምንድነው ብሎ ሲወጣ እኛ አንተ ነው የምንፈልገው ቤቱን ጋዝ አርከፍክፈን ነው ምናቃጥለው ካሉ በኋላ በቀን 02/12/10 በግምት ከቀኑ 06፡00 ሰዓት ላይ የግል ተበዳዩ ቤት በመግባት የግል ተበዳዩ ባለቤት ወ/ሮ ሙሉነሽ ኑሩን አናትሽን ነው ምንበረግድልሽ አንድ ድምጽ እንዳታሰሚ ብለው እንዳትጮህ በማስፈራራት ሳጥን ሰብረው 27000 ብር (ሃያ ሰባት ሺህ ብር) እና 5.2 ግራም ካራቱ 14 የሆነ የእጅ ቀለበት የወሰዱ በመሆኑ ከባድ የውንብድና ወንጀል ፈጽሟል በማለት ነው፡፡ጥሩ ንባብ…
15
ጉዳዩ የእርሻ መሬትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደጋ ዳሞት ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፤ የአሁን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አዋሳኛቸው በክስ አቤቱታው ለይ የተገለጹ በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚገኙ መሬቶች በስሜ የተመዘገቡ ናቸው፤ የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃም አለኝ፤ መሬቶቹን ለአመልካች በእምነት አስጠምጃት ነበር፤ ሆኖም ጥማዶውን አሁን ከልክላኛለች፤ ስለሆነም መሬቱን ለቃ እንድታስረክበኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው፡፡ጥሩ ንባብ…
15
የአቤቱታዉ መሠረታዊ ይዘትም በአጭሩ ተጠሪ በስር ፍርድ ቤቶች ያቀረባቸዉ ምስክሮች በሰጡት ቃል ሟች የእኔ ልጅ ነዉ ሲል ሰምተናል ከማለት ዉጪ የተጠሪ እናት ማን እንደሆነ ወይም ከማን እንደተወለደ፣ የት እንደተወለደ፣ መቼ እንደተወለደ የማያዉቁ መሆናቸዉን እንጂ ከሟች ጋር አብሮ ሲኖር የነበረ ስለመሆኑ ባላስረዱበት እንዲሁም ተጠሪ የሟች ልጅ መሆኑን ሲናገር ሰምተናል ከማለት ዉጪ የሟች ልጅ መሆኑን ባላስረዱበት ሁኔታ ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤት ምስክሮች ያላሉትን በእራሱ ጊዜ በማንሳት የስር የወረዳዉ ፍርድ ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር በዲ ኤን ኤ ምርመራ እንዲረጋገጥ በጠየቅኩት መሠረት ሳያረጋግጥ የሰጠዉ ዉሳኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት ነዉ የሚል ነዉ፡፡ጥሩ ንባብ…