Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project

እነ ወ-ሮ ፈይዛ ከማል አወል፣አቶ አብዲ አህመድ መሀመድ እና አቶ ካህሳይ ተስፋዝጊ የሰ-መ-ቁ 184601

Friday, December 4, 2020 16456

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ን/ስ/ላ/ምድብ በኮ.መ.ቁ 88409 በ16/2/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ.መ.ቁ 222352 በ19/11/11ዓ.ም በሰጠው ብይን/ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት በ11/2/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የን/ስ/ላ/ ምድብ 4ኛ ፍ/ብሄር ችሎት በ1ኛ ተጠሪ ላይ ጋብቻቸው በፍ/ቤት በ23/4/07ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ በፍቺ መፍረሱን ተከትሎ ባቀረቡት የጋራ ንብረት ክፍፍል ክስ አከራካሪውን የሰ.ቁ ኮድ A-13872 ያሪስ መኪና ዋጋው ብር 550‚000 የሚያወጣ እና ሌሎች ንብረቶችን የእቁብ ገንዘብን ጨምሮ በመዘርዘር ንብረቶቹ የጋራችን ስለሆኑ እኩል እንድንካፈል እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት መልስ በጋብቻ ውስጥ እያለን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ቀበሌ 13 የቤት ቁጥር 069 በአቶ መሃመድ ይማም ዳኝነት በአቶ እንድሪስ አለሙ ጸሀፊነት በአቶ ወንድሜነህ አለሙ ይሰበሰብ የነበረው እቁብ በ29/4/04ዓ.ም ደርሶኝ ለትዳራችን ጥቅም ያዋልኩት ሲሆን፤ ይህን እቁብ መክፈል ባለመቻሌ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ፍ/ብሄር ችሎት በመ.ቁ 38976 ክስ ቀርቦብኝ ገንዘቡን እንድከፍል በ30/4/05ዓ.ም ተወስኖብኝ ከነወጪና ኪሳራ ብር 149‚365.95 እንድከፍል በመገደዴ አመልካች ያካፍለኝ በማለት ያቀረበችውን የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን መኪና ሸጬ እዳውን ከከፈልኩኝ በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ለትዳር ጥቅም ስለዋልኩት ጥያቄው አግባብ አይደለም በማለት ተከራክረው እንዲሁም በሌሎች ንብረቶችም ላይ መልስ የሰጡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራቀኙን በቃል ካከራከረ በኋላ ግራቀኙ በጋብቻ እያሉ የጋራቸው የሆነ እዳ ነበር ወይስ አልነበረም? አከራካሪውን የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን መኪና ግራቀኙ በትዳር እያሉ ተሸጦ ለጋራ እዳ ክፍያ እና ለትዳር ጥቅም ውሏል ወይንስ አልዋለም? የሚለውን እና ሌሎች ንብረቶችን በተመለከተ የተለያዩ ጭብጦችን በመያዝ፤ አከራካሪውን መኪና በተመለከተ ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ትእዛዝ በመስጠት ምላሽ ከቀረበለት በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የጋራ እዳን በተመለከተ 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በጋብቻ እያለን ለደረሰብኝ እዳ መክፈል ባለመቻሌ በፌ/መ/ደ/ፍቤት አራዳ ምድብ ችሎት በመ.ቁ 38976 በ30/4/05ዓ.ም ከወጪና ኪሳራ ጭምር ብር 149‚365.95 እንድከፍል ተወስኗል ያሉትን በተመለከተ እዳው የመጣው ባልና ሚስት በጋብቻ አብሮ እያሉ ስለመሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ እዳው የጋራቸው ነው በማለት ከወሰነ በኋላ ከላይ የተገለጸውን ገንዘብ እንዲከፈል የተወሰነው በ30/4/05ዓ.ም በመሆኑ ለዚህ እዳ መኪና ተሸጠ የተባለው በ2007ዓ.ም ነው፤ 1ኛ ተጠሪ መኪናው በእዳ ተይዞ ተገዶ ለመሸጡ ሆነ ገንዘቡ ከመኪና ሽያጭ ለመከፈሉ ምንም ማስረጃ አላቀረበም፤ እዳው ከተከፈለም እዳው የመጣው በጋብቻ እያሉ በመሆኑ በጋብቻ አብረው እያሉ እንደተከፈለ የሚቆጠር በመሆኑ መኪና ተሸጦ ተከፈለ በማለት 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክር ባለመቀበል፤ የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን ያሪስ የቤት መኪና አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በጋብቻ እያሉ ያልተሸጠ እና ለጋራ እዳም ሆነ ለትዳር ጥቅም ያለመዋሉ ከመረጋገጡም በላይ 1ኛ ተጠሪ ተሸጧል ሲል ቢከራከርም መኪናው ከመሸጡ በፊት በፍ/ቤት በ13/2/07ዓ.ም የታገደ መሆኑን 1ኛ ተጠሪም የሚያውቀው በመሆኑ፤ ለመሸጡ የንፋስ ስልክ ላፍቶ የመንገድና ትራንስፖርት የሰጠው መረጃ ታማኝነት የሌለው እና ውድቅ የተደረገ በመሆኑ ቢሸጥ እንኳን አስቀድሞ በፍ/ቤቱ የታገደ በመሆኑ ተገቢነት የለውም በማለት፤ በ1ኛ ተጠሪ እጅ የሚገኘው የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን ያሪስ የቤት መኪና የአመልካች እና የ1ኛ ተጠሪ የጋራ ንብረታቸው ነው በማለት፤ ክፍፍሉን በተመለከተ ከተስማሙ አንዱ ለሌላው ግምቱን በመስጠት ያስቀረው፤ በዚህ ካልተስማሙ መኪናው በሀራጅ ተሸጦ ገንዘቡን እኩል እንዲካፈሉ በማለት በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 90 መሰረት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ሌሎች ንብረቶችን በተመለከተም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡………….

Read more

እነ ወ-ሮ ሐመልማል ታመነ ወ-ሮ የምስራች ተካ እና አቶ ክፍሌ ተካ የሰ-መ -ቁ 184335

Tuesday, December 1, 2020 17341

አመልካች ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 07508 ሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችሎት በመዝገብ ቁጥር 07390 ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ፍርድ እና ውሳኔ ማፅናቱ መሠረታዊ የህግ ስህተት ነው በማለት በሰበር ለማሳረም ያቀረቡትን ቅሬታ ለመመርመር መዝገቡ ለችሎት ቀርቧል።ጉዳዩ የውርስ ንብረት እንዲጣራ የቀረበ ክርክር ሆኖ ክርክሩ በተጀመረበት የሼይ ቤንች ወረዳ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች በከሳኝነት ፣ በሰበር ክርክሩ የሌሉት አቶ ፍቃዱ ተካ በተከሳሽነት እና አመልካች እና ሌሎች በሰበር ክርክሩ ተካፋይ ያልሆኑት 3 ሰዎች በጣልቃ ገብነት ተከራክረዋል። 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡት የውርስ ይጣራ አቤቱታ ከሥር ተከሳሽ ጋር ከሟች አቶ ተካ ከበደ የሚወለዱ መሆኑንና አባታቸው ጳጉሜ 1 ቀን 2009 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ገልጸው በህይወት በነበሩበት ወቅት በሚዛን ከተማ ህብረት ቀበሌ ኮንዶሚንዬም ፊት ለፊት ከመንገድ በታች ያለው አንድ ክፍል ቤት ከይዞታው ጭምር እንዲሁም ሌሎች በሟቹ የተፈሩ ናቸው የሚሉትን ንብረቶችን በመዘርዘር የውርስ ንብረቶቹን ሌሎች በእጃቸው ይዘው የሚገለገሉበት መሆኑን ገልፀው ድርሻቸውን ማግኘት እንዲችሉ የውርስ አጣሪ ተሹሞ የውርስ ሀብቱ እንዲጣራ ፣ ወራሾች እንዲለዩ እና ንብረቶቹ በአጣሪው እንድተዳደሩ እንድወሰን አመልክቷዋል። የሥር ተከሳሽ ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ መሆኑን መዝገቡ የሚያስረዳ ሲሆን በአማራጭ በፍሬ ነገሩ ላይ ባቀረቡት መልስም በክሱ ውስጥ መብት እና ጥቅም ያላቸው አመልካች እና ሌሎች ሰዎች ስላሉ በፍርድ ቤቱ ጥር ወደ ክርክሩ እንዲገቡ ፤ የውርስ አጣሪ እንዲሾም ፤ የውርስ ንብረቱ የወራሾች የጋራ ሆኖ በሟች በመታሰቢያነት በቅርስነት እንዲቆይ ፤ ለሟች ተስካር ፣ የሙት ዓመት እና ሌሎች ወጪዎች እንድሁም ዕዳም ካለ እንድጣራ ጠይቋል። አመልካች እና ሌሎች ከውርስ ሀብቱ መብት አለቸው የተባሉትን አራት ሰዎች በፍርድ ቤቱ ጥሪ ወደ ክርክሩ ገብተው ከሥር ተከሳሽ ጋር የሚመሳሰል መልስ መስጠታቸውን ፍርድ ቤቱ  መዝግቧል። ፍርድ ቤቱ የውርስ አጣሪ የሾመ ቢሆንም የሟች ውርስ ሀብት በአግባቡ አልተጣራም በማለት ሪፖርቱ ውድቅ በማድረግ ግራ ቀኙ ወደ ክርክሩ እንድገቡ አድርጓል። የሥር ተከሳሽ በሚዛን ከተማ ህብረት ቀበሌ ኮንዶሚንየም ሰፈር ያለው ቤት በሟች ስም አለመመዝገቡ ፣ የሟች ቀለበቶች በእሱ እጅ አለመኖራቸውን ፣ ለሟች አርባ እና የተለያዩ ወጪዎች ተጣርተው ቀርበው ክፍፍል እንድደረግ ጠይቋል። ጣልቃ ገቢዎችም ተመሳሳይ ክርክር ማቅረባቸው በፍርዱ ላይ የተመላከተ ሲሆን የሥር ከሳሽም በጽሁፍ ክርክራቸው የጠየቁትን ዳኝነት በማንሳት መከራከራቸው ተመላክቷል።……….

Read more

አቶ ግደይ ገ-ጻድቃን ገ-ማርያም እና ወ-ሮ ክንድሀፍቲ ኢታይ የሰ-መ-ቁ 179589

Monday, November 9, 2020 17712

የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 24172 በቀን 08/04/2011 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ እና የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 226191 በቀን 19/07/2011 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው፡፡ ክርክሩ የዕግድ ትዕዛዝ እንዲነሳ በአመልካች የቀረበን አቤቱታ የሚመለከት ነው፡፡በፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በከሳሽ ወ/ሮ ክንድሀፍቲ ኢታይ (የአሁን ተጠሪ) እና በተከሳሽ አቶ ፀጉ ብርሃነ መካከል በነበረው የባልና ሚስት የንብረት ክርክር ጉዳይ የአሁን ተጠሪ ንብረት እየሸሸ በመሆኑ ይታገድልኝ በማለት በፀጉ ብርሃነ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሚታወቁ መኪኖች ላይ የእርድ ትዕዛዝ አሰጥተዋል፡፡በፀጉ ብርሃነ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እግዱ እንዲነሳ ጠይቆም በቅድሚያ ዋስትና እንዲያስይዝ ተጨማሪ ትዕዛዝ ተሰጥቶበታል፡፡…..

Read more

ወ-ሮ ተሚማ ሬድዋን በሽር እናአቶ በድሩ ሰማን፣አቶ ደሊል በድሩ የሰ-መ-ቁ 179231

Saturday, November 7, 2020 16909

ጉዳዩ የባልና ሚስት የጋራ ሀብት በሆነ ንብረት ላይ ይገባኛል የሚለው ሰው በአንደኛው ተጋቢ ላይ ብቻ ክስ አቅርቦ ተከሣሹም  ንብረቱ የከሣሽ ነው ሲል አምኖ መከራካሩን ተክተሎ በክሱ መሰረት ከተወሰነ በኋላ ሌላኛው ተጋቢ የመቃወም አቤቱታ ሲያቀርብ ብቻውን ተከሻስ የነበረው ተጋቢ  ቀደም ሲል ያቀረበውን ክርክር ሣይለውጥ በመቀጠሉ የተወሰነው የንብረቱ ክፍል የተጋቢዎች የጋራ ሃብት መሆኑ ቢረጋገጥም በክርክሩ ያመነው ተጋቢ ድርሻ ለከሣሽ ወገን እንዲተላለፍለት መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ተብሎ እንዲታረም የቀረበን የሰበር አቤቱታ ይመለከታል፡፡……….

Read more

እነ ኡባህ በዲሪ ከ ኡመር ዩሱፍ ዶላል የሰ-መ-ቁጥር 190350

Friday, November 6, 2020 17215

ጉዳዩ የጫት ሽያጭ ውልን መሰረት ያደረገ የእዳ ይከፈለኝ ክስን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፋፈን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካቾች እንደየቅደም ተከተላቸው ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል፡፡

ተጠሪ ባቀረቡት ክስ ከአመልካቾች ጋር ባለን የጫት ንግድ ግንኙነት መነሻነት ጫቱን ቦንባስ አምጥቼ እያስረከብኳቸው ስንሰራ ቆይተናል፡፡ አመልካቾች ውሉን በራሳቸው ያቋረጡ ሲሆን ያለባቸውን የጫት ገንዘብ እዳ ብር 2,088,000 (ሁለት ሚሊዮን ሰማንያ ስምንት ሺ) እንዲከፍሉኝ ሽማግሌዎች ብልክባቸውም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው እና እዳው በሰነድ የተመላከተ ስለሆነ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 284 መሰረት በተፋጠነ ስነ ስርዓት ገንዘቡን እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡

Read more
FirstPrevious25262728293031323334NextLast

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions