ይህ ወራሽ የሌለዉ የዉርስ አክስዮን ድርሻ ክርክር የተጀመረዉ በፌዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ
ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.167717 ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ።